Saturday, April 9, 2016

ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ በዋስ ተፈታ – ‘ታቦት ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዟል’ የሚል ክስ ቀርቦበታል




engedawork bekle
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዘማሪነት የሚታወቀው ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለ ትናንት ከ እስር መፈታቱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ ዘገቡ::
እንደ ዘጋቢዎቻቸን ገለጻ ከሆነ ላለፉት 2 ሳምንታት እስር ቤት የቆየው ዘማሪው ከታቦት ሽያጭ ጋር የተያያዘ ክስ ቀርቦበታል::
ፖሊስ በዘማሪው ላይ ያስቀመጠው ክስ እንደሚያሳየው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ የሄዱ አባ ገብረወልድ የተባሉ መነኩሴ በሰሜን አሜሪካ ቤተክርስቲያን ለማቋቋም በማቀድ ከእንግዳወርቅ ታቦቱን በ90 ሺህ ብር ሲሸጥ እጅ ከፍንጅ ተይዟል የሚል ነው::
እንግዳወርቅ በተጠረጠረበት ወንጀል አዲስ አበባ ከጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው መዝሙር ቤቱ ቅዳሜ ማርች 26, 2016 ሲያዝ ታቦቱን ከሚነዳት ቭትስ መኪና እንዳወጣው ፖሊስ ባቀረበበት ክስ ላይ ተቀምጧል ተብሏል:: ከዘማሪው ጋር አብሮ የተጠረጠረ አንድ ሰው መታሰሩን የሚገልጹት ምንጮች ታቦቱን ይቀርጻል የተባለው ሰው መሰወሩና ፖሊስም በክትትል ላይ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::
ትናንት ራስ ደስታ አካባቢ ከሚገኘው ፖሊስ በዋስ ከ እስር የተፈታውን ዘማሪ እንግዳወርቅ በቀለን ዘ-ሐበሻ ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም

No comments:

Post a Comment