Friday, April 8, 2016

አቡነ ማትያስ “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” መሆናቸው ተረጋገጠ!

አቡነ ማትያስ “ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” መሆናቸው ተረጋገጠ።
Patriarch Abune Mathias of the Ethiopian Orthodox Church attends the annual Epiphany celebrations called "Timket" in Addis Ababa January 19, 2014. "Timket" commemorates Jesus Christ's baptism in the Jordan River by John the Baptist. REUTERS/Tiksa Negeri (ETHIOPIA - Tags: RELIGION) - RTX17L9F
የ ESAT አቶ ኤፍረም አሸቴ ቅለመጠይቅን ለማዳመጥ የሚቀጥለውን ይጫኑ።

Audio Player
ለ 30 ዓመታት ከኖሩበት ከውጭው ዓለም አቡነ ጳውሎስ በድንገት ሲሞቱ ወያኔ ጠርቶ የሾማቸው አቡነ ማትያስ ኢ.ኦ.ተ.ቤተክርስቲያን እውቋትም። አቡነ ማትያስ ብቃቱም እንደሌላቸው አሁን በይፋ መረጋገጡን ህዝበ ክርስቲያኑም ሆነ  በተሾሙበት ወቅት የደገፏቸውና ምናልባትም ከአቡነ ጳውሎስም ይሻላሉ በሚል ቀቢፀ ተስፋ አሁን እውነቱን እየተረዱት መሆኑን ከአለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ የበለጠ ግልፅ ሆኗል።  
ብዙ የተታለሉና የማይሆን ተስፋ አድርገው የነበሩ ጋዜጠኞች ሳይቀሩ ከአባ ማትያስ የተሻለ ነገር የጠበቁበት ዋና ምክንያት አንዱ አቡነ ማትያስ አቡነ ጳውሎስን ‘ከፋፋይ ናቸው” እያሉ ይወቅሱ ስለነበር ነው። ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ አቡነ ማትያስን ለረጅም ጊዜ የሚያውቋችውና በሰፊው የፃፉ አባት ኢንደሚሉት፤ አቡነ ማትያስ ኢንደሰው ገር ናችው፣ ነገር ግን ጭንቅላታቸው ባዶ ስለሆኑ ከአቡነ ጳውሎስ እጅግ አደገኛ ሁኔታ ይፈጥራሉ በማለት በተደጋጋሚ ፅፈዋል፣ ተናግረዋል።  ታዲያ አቡነ ማትያስ ለምን ነበር አቡነ ጳውሎስን ‘ከፋፋይ ናቸው’ እያሉ ይወቅሱ የነበረው ለሚለው ጉዳዩን ስናጣራ ያገኘነው ምክንያት የሚከተለው ነው።
መለስ ዜናው ጫካ በነበረበት ጊዜ ለአቡነ ጳውሎስና አቡነ ማትያስ “ፓትርያርክነት እሰጥዎታለሁ” ብሎ  በየግላቸው ቃል ገብቶላቸው ነበር።  ነገር ግን መለስ ዜናዊ አቡነ ጳውሎስን መርጦ ሾመ። በዚህ የተናደዱት አቡነ ማትያስ ለብዙ ዓመታት ሲጋጩ  እንደኖሩ ጉዳዩን በደንብ ከሚያቁ ሰዎች ለመረዳት ችለናል። እንደ ማስረጃ የሚሆነው አቡነ ማትያስ አሜሪካን ሊቀ ጳጳስ ተብለው በቆዩበት ወቅት ቁጥራቸው ከ10 የማያንሱ ኢትዮጵያ ባለው ሲኖዶስ የምመሮ በአሜሪካን የሚገኙ ቤተክርስቲያኖች በአቡነ ማትያስ ሳይሆን ቀጥታ በአቡነ ጳውሎስ ይመሩ ነበር። ይህንን ማንም ማረጋገጥ ይችላል።
በመጨረሻም አቡነ ጳውሎስ ሲሞቱ መለስ በገባላቸው ቃል መሰረት ሹመቱን እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
ቀሲስ አስተርአየ ደጋግመው እንደሚሉት የአቡነ ማትያስን ባህርዬ የሚያሳየው አቡነ ማትያስ ገና ከኢየሩሳሌም ሳይነሱ: “ፓትርያርክ ለመሆን ተጠርቼ ወደ ኢትዮጵያ ልሄድ ነው” ብለው የነግሯቸው የገዳሙ መነኮሳት በወቅቱ ተናግረዋል። ነገር ግን በወቅቱ ወያኔ መሾሙን የማስቆም አቅም እንደሌላቸው የተገነዘቡ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ አቡነ ማትያስን ለማግባባት ይቻል ዘንድ መልካም ነገር ስፅፉና በተለይም አቡነ ጳውሎስ ነጭ የለበሱ ነበር ግን ቀጥሎ የሚመጡት ፓትርያርክ (አቡነ ማትያስ መሆናቸው ነው) ጥቁር ነው የሚለብሱት እያሉ የፃፉም ነበሩ

No comments:

Post a Comment