ዘ-ሐበሻ) ትናንት ማምሻውን በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመኝታ ህንፃ ላይ በተነሳ ቃጠሎ በርካታ የተማሪ መኝታ ክፍሎች መውደማቸው ተሰማ::
የአካባቢው ነዋሪም ሆነ መንግስት በቶሎ ሊቆጣጠረው ያልቻለው ይኸው እሳት በዚህ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሄዱ ተማሪዎች ንብረቶች መውደማቸው ታውቋል::
የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሰጡት አስተያየት ከሆነ ይህ የ እሳት ቃጠሎ ለረዥም ሰዓታት የቆየ ሲሆን መንግስት በአፋጣኝ ሊያጠፋው ያልቻለው አንድ ተንኮል ቢኖረው ነው ብሏል:: በተለይ በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እየተነሱ ያሉ የሕዝብ አመጾችን ከሽብርተኝነት ጋር ለማያያዝና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን ማሳየት የሚፈልገው ሕወሃት መራሹ መንግስት ሆን ብሎ እንዲህ ያለውን ጥፋት አይፈጽምም ማለት አይቻልም የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::
በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ መኝታቸው እና ንብረቶቻቸውን ያጡ ተማሪዎች በችግር ላይ እንደሆኑ የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች ከክፍለሃገር የመጡ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመጣል ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋር መሄድ መጀመራቸውንም ዘግበዋል
ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አሉ፤ አሁንስ በዛ እሣቱንም በመንግስት ጎርፉንም በመንግስት ስታመካኙ ለመሆኑ እናንተ ምን ሰራችሁ?????
ReplyDelete