Sunday, April 10, 2016

የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ውስጥ 2 ወጣቶች ለማምለጥ ሲሞክሩ ሞተዋል፣ 11 ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተባለ – VOA



አስመራ ውስጥ ሁለት በብሄራዊ አገልግሎት ላይ የነበሩ ወጣቶች ባለፈው እሁድ ከተጫኑባቸው መኪኖች ዘለው ለማምለጥ ሲሞክሩ በደረሰባቸው ጉዳት ሞተዋል ሲሉ የኤርትራ ማስታወቅያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገልጸዋል። ሌሎች ከመኪኖቹ ዘለው ለማምለጥ የሞከሩ 11 ወጣቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ገብተዋል ብለዋል። ፖሊሶች ጥቂት ጥይቶች ወደ ሰማይ በመተኩስ እንዲረጋጉ አድርገዋል ሲሉም አቶ የማነ አክለዋል።
የተለያዩ የኤርትራውያን ተቃዋሚዎች ሬድዮዎችና ድረ-ገጾች ግን የሞቱት ወጣቶች ብዛት ከአራት እስከ 11 ነው ይላሉ።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ከኤርትራ ባለስልጣኖች ምላሽ ለማግኘ ያደረገው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካለትም

No comments:

Post a Comment