በኦሮሚያ ክልል ያለው ጉዳይ እስካሁን በቁጥጥር ስር ማዋል ያቃተው ወያኔ ያሰለጠናቸውን ኬንያዊ ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ የደህንነት አባላትን ደጋግሞ ቢያሰማራ በፍጹም ሊሳካለት እንዳልቻለ እና የኦሕዴድ አባላት ራሳቸው ለተግባራዊ ስራ ታማኝነት ሊያሳዩ ባለመቻላቸው በተለያየ መልኩ የታቀዱ ግቦች ሁሉ እንዲጠመዘዙ በመደረጉ አጣብቂኙ እየጨመረ እንደሄደ የውስጥ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::በትግሪኛ ተናጋሪ የሕወሓት ሰዎች ሰንሰለትነት የተያዘው የደህንነት ተቋሙ ታማኝ ይሆኑኛል ያላቸውን በርካታ የድህነት አባላት እያጣ ሲሆን በዙሪያው የተኮለኮሉ ሆዳም አባላትም በጥርጣሬ ቀለበት ውስጥ መግባታቸውን ምንጮቹ አጠንክረው ይናገራሉ::
ክዚህ ቀደም ወደ ተለያዩ ክፍለጦሮች የተላኩ እና ከሲቭል ወደ ወታደራዊ ደህንነት የተዛወሩ አባላትን መልሶ አምጥቶ አዳዲስ ወታደራዊ የደህንነት ምልምሎችን በየክፍለጦሩ የመመደብ እቅድ መኖሩንም ለተቋሙ ሹሞች ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲናገሩ በኢሚግሬሽን አከባቢ ያሉ የብኣዴን አባላትን አጣርቶ ለማባረር እንደታሰበም ተናግረዋል::እንዲሁም በባህርዳር ጎንደር ደሴ ደብረብርሃን የሚገኙ የደህንነትን አባላት ላይ ተጨማሪ ሃይል ለማድረግ መታቀዱ በአማራ ክልል ይነሳል ተብሎ የተሰጋውን የሕዝብ ተቃውሞ ለመቆጣጠር ከወዲሁ መታለሙን ምንጮቹ ገልጸዋል::#ምንሊክሳልሳዊ

No comments:
Post a Comment