ስንታየሁ ከሚኒሶታ
“አልችልም” የሚል ነጠላ ዜማ ነበር በቅድሚያ የለቀቀችው:: በዚህ ዘፈን እንደተዋወቀች “ጋሜ” የተሰኘ በስታይል የተሰራ ዘፈኗን አስከትላ ስታበቃ “ናማ” በሚለው ዘፈኗ ሰቀለች – ዲና አንተነህ:: ሰሞኑን ደግሞ ‘በዴ’ የተሰኘና በአማርኛ እና በኦሮሚኛ ቋንቋ የተሰራውን ዘፈኗን ለቀቀችልን:: ይህ ዘፈን ዘ-ሐበሻን ጨምሮ በተለያዩ ድረገጾች ላይ የተለቀቀ ሲሆን እነዚህን ሳይጨምር በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ላይ በሁለት ቀናት ብቻ ከ78 ሺህ በላይ ተመልካቾችን በማግኘት ሪከርዱን ይዟል::
እንደ እኔ አስተያየት ዲና በዚሁ አዲሱ ነጠላ ዜማዋ እጇቿን ወደላይ በማጣመር ከኦሮሞ ተማሪዎች ሰሞኑን ካነሱት ሕዝባዊ ቁጣ ጋር ያላትን አጋርነት አሳይታለች ማለት ይቻላል:: :: በተለይም በክሊፑ ላይ እጆቿን ወደ ላይ ያጣመረችበት ቦታ ላይ ከጀርባ ያለው ቦታ የመቃብር ቦታዎች ይመስላሉ:: ይህም በኦሮሚያ ክልል በሕወሓት መንግስት ለተገደሉት ንጹሃን መታሰቢያ ለማድረግ የታሰበ ያስመስለዋል:: እንዲህ ነው ጥበብ መል ዕክት ማስተላለፊያ ሲሆን::
ይህን የዲናን ሁኔታ አይተው መንግስታዊ ሚዲያዎች እንደለመዱት ዘፈኑን በሚድያዎቻቸው እንደማያስተላለፉት ይጠበቃል:: በድጋሚ ዘፈኑን ተመልከቱት::
No comments:
Post a Comment