በደቡብ ክልል ሀድያ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የኤልኒኖ ክስተት በሆነው የአየር መዛባት ምክንያት፣ በድንገት በሚፈጠር ቃጠሎ ከ300 በላይ የሚሆኑ ቤቶች መውደማቸው ተጠቆመ፡፡በተለይ ጊቤ፣ ሰሮ፣ ገምቦራና ሸሸጐ ወረዳዎች ላይ በተደጋጋሚ ባልታሰበ ቀንና ሰዓት በተፈጠረ ድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ፣ የበርካታ ቤተሰቦች ቤቶች በመቃጠላቸው ለከፋ ጉዳት መዳረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡በነዋሪዎቹ መኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ጉዳት በአካባቢው ከተፈጠረው ድርቅ ጋር ተያይዞ ችግራቸውን እንዳባባሰባቸው የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ የክልሉ መንግሥት ከዞኑና ከወረዳ ኃላፊዎች ጋር በመተባበር ዕርዳታ ባያደርግላቸው የከፋ ችግር ይደርስባቸው እንደነበር አስረድተዋል፡፡
ለጊዜው መጠለያ አጥተው ከአካባቢያቸው ርቀው በመጓዝ ጊዜያዊ መጠለያ ለመጠቀም መሞከራቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ቤታቸውን ግን መልሶ መገንባት እንዲችሉ ዕርዳታ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment