Wednesday, August 2, 2017

ማለቂያ የሌለውና፣ አሰልቺው የህወሃት/ኢህአዴግ ‘ጸረ-ሙስና’ ዘመቻ -አበጋዝ ወንድሙ



  
August 1, 2017      
 

ህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት አንደከዚህ ቀደሙ፣ ዘንድሮም የጸረ- ሙስና ዘመቻ በሚል  በትልቅ ጭጫታ አጅቦ አዲሱን ዘመቻውን  ይዞ  ብቅ ብሏል። የህወሃት/ኢህአዴግን ምንነት በቅጡ ያልተረዱ ወይንም የዘነጉ ወገኖች፣ እከሌ ታሰረ፣እከሌ ቀረ፣ እከሌማ ካልታሰረ ዘመቻው የምር አይደለም… ወዘተ የሚል አላስፈላጊ ውይይት ውስጥ ገብተው ሳይ ፣ ጎበዝ አንዘናጋ ለማለት እፈልጋለሁ።
ሙስና፣ የህውሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት መሰረታዊ  መገለጫ ባህሪው በመሆኑ፣ ይሄ ቡድን  ከስልጣን አስካልወረደ ድረስ አብሮን የሚኖር ፣ በሂደትም አየባሰበት በመሄድ ሀገራችንን  አጅግ በጣም አስቸጋሪ ወይንም ልንወጣው ወደማንችለው አዘቅት ውስጥ ሊከት አንድሚችል መገንዘብ የግድ ይላል።
ዛሬ አርባና  ሃምሳ ሰዎች በቁጥጥር ስር አድርጎ  የኢትዮጵያ  አራት ቢልዮን ብር ሊደርስ የሚችል ገንዘብ (እርግጥ ለኛ አይነት ደሃ ሃገር ገንዘቡ ብዙ ነው፣ መምዝበሩም ያሳዝናል ) ባክኗል ወይንም መንግስት እንዲያጣ ተደርጓል በሚል ቡራ ከረዩ የሚለው መንግስት፣ የዛሬ አምስት ዓመት የአውሮፓ ድርጅቶች ባወጡት ጥናት ከኢትዮጵያ በሕገ-ወጥ መንገድ 11 ቢልዮን የአሜሪካ ዶላር ወደውጭ መውጣቱን ይፋ ሲያደርጉ አይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ማለፉን ስናስታውስ፣  የዘንድሮው ዘመቻም ሙስናን ከመዋጋት ጋር ቀጥተኛ  ግንኙነት እንደሌለው እንረዳለን።
የህወሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት የሚጠቀምባቸውን ማደናገሪያ ተረቶችና በየጊዜው የሚታወጁ ዘመቻዎችን  ወደጎን ስናደርግ፣በሀገራችን የሙስናው ምንጭ ሌላ ነገር ሳይሆን፣ ከመሬትና ከመሬት ባለቤትነት ጋር የተቆራኘ መሆኑን አንገነዘባለን። ይሄንን መሬትንና የመሬት ባለቤትነትን በሚመለከት የጠራ አመለካከት አስካልያዝን ድረስም በሀገሪቱ የተንሰራፋውን የሙስና ስርዓት ለማወቅ፣ አውቆም ለመታገል ያዳግተናል።
አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት አንቀጽ 40 ቁ 3 ‘የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት መብት የመንግሥትና የህዝብ ብቻ ነው። መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ንብረት ነው።‘ ቢልም፣ በመሬት ላይ ያለው ገሃድ ሀቅ ግን፣ ላለፉት 26 ዓመታት መሬት በህውሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ከችርቻሮ አስከ  ጅምላ የሚቸበቸብ ተራ ሸቀጥ መሆኑ በማያወላዳ መንገድ ይታወቃል ።
 በስም፣ ባለቤት ተብለው በዚሁ ሀገ-መንግስት የተንቆለጳጰሱት ‘ብሔር  ብሔረሰቦችና ህዝቦች’ የደረሳቸው እጣ ፈንታ ደግሞ ከተማ ያሉት ከሶስትና አራት ትውልድ ወይንም ከዛ በላይ ከኖሩባቸው ቤቶችና ሰፈሮች በልማት ስም በጅምላ ተፈናቅሎ ወደ ከተማ ዳርቻ መወርወር፣ በአዲስ አበባ አካባቢ የሚኖሩ አርሶአደሮችንም አንዲሁ ጭብርብርና ጉልበት የታከለበት ያለበቂ ካሳ መፈናቀል፣ በበርካታ የሀገሪቱ  ግዛት የሚኖሩ አርሶ አደሮች ደግሞ፣ ለውጭ ባለሀብት በልማት ስም ‘የሚሰጥ’  መለስተኛ የአውሮፓ ሀገር የሚያህል መሬት ለማመቻቸት  ሺዎች በጉልበት መፈናቀልና ለስደትም መዳረግ ነው።
ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት ስር ነቀል  ጸረ-ሙስና ዘመቻ አያካሄድኩ ነው ብሎ ሲያውጅ የዘንድሮው ሶስተኛ ወይንም አራተኛ ጊዜው ነው። ከባለፉት ዘመቻዎች የተረዳናቸው ነገሮች ቢኖሩ ፣ሙስናን መዋጋት የሚሉ ዘመቻዎች መንስኤ በጥቅሉ  ሶስት ሲሆኑ፣ አንዳቸውም ግን በቅንነት ሙስናን የመዋጋት አላማ የላቸውም።
አንደኛው ምክንያት የህዝብ ብሶት ጠንክሮ ወደ እንቅስቃሴ ሲያመራ፣ ለማስተንፈስ ወይንም አቅጣጫ ለማስቀየስ ፣ ሁለተኛ በውስጣቸው ያለው የስልጣን ወይንም የበላይነትን  የማስፈን ሽኩቻን መቋጫ፣ የተወሰኑ ሰዎችን ወህኒ የሚወረውሩበት ወይንም ከስልጣን ገሽሽ  የሚያደርጉበትና፣ ሶስተኛው ቅጥ ያጣ ዘረፋ አንደሚካሄድ በማየት እየደገፍናችሁ አታሳጡን፣ ለሚለው የምዕራብ ሀገሮች ተማጽኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረግን ነው ለማለት የሚካሄዱ የይስሙላ ዘመቻዎች ናቸው።
ህወሓት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት መሬትና የመሬት ባለቤትነት በሀገሪቱ የተንሰራፋው የሙስና ስርዓት ዋና ምንጭ መሆኑን ስለሚያውቅ በየጊዜው ማደናገሪያ ለመፍጠር ቢሞክርም፣ ይሄንን ተገንዝበውና ተረድተው ግን  የህወሓት/ኢህአዴግ መንግስትን የሚያጋልጡና የሚታገሉ ወገኖችን  እንደ ደመኛ  ጠላቶቹ እንደሚያይ የበቀለ ገርባ ምሳሌ ያሳየናል ።
የኦፌኮና የመድረክ መሪ የነበረው በቀለ ገርባ የዛሬ ሰባት ዓመት ለምርጫ በተደረገ ክርክር ወቅት ይሄንን ሃቅ፣ ማለትም የሙስና ምንጭ የህውሃት መራሹ የኢህአዴግ መንግስት መሬትን አንዴ ግል ሃብት በመቁጠር ፣ከሱ ጋር ለተጣቡት ሽልማት ፣የተወሰኑትን ለማማለልና ድጋፍ ለማግኘት ለጥቂቶች የቁርጥ ቀን ልጆቹ ደግሞ ‘በብርሃን ፍጥነት ተዝቆ ወደማያልቅ ሀብት የተመነጠቁበት መንኮራኩር ‘ አንደሆነ በማጋለጡ ይሄው አስከዛሬ ምክንያት አየተፈለገ በአስር አንዲማቅቅ ተደርጓል ።
ዛሬ ከህዝብ ተዘርፎ በተቸበችበ መሬት የህወሃት ቁንጮ ባለስልጣናት፣ወታደሮችና የጥቅም ተጋሪ በመሆን፣ በፍጥነት በመመስረትና በማደግ ላይ ያለው አዲስ የገዥ መደብ አባላት የሆኑ፣ ከልዩልዩ ብሄረሰብ የተውጣጡ ባለጊዜዎች በሚልዮንና በቢሊዮን ስለሚቆጠር ሃብት አንዱ ከአንዱ የሚፎካከሩበት ዘመን ደርሰናል።
የተቃዋሚ ሃይሎችና ህዝብም መንግስት የሚያካሂደውን ውዥንብር ፈጠራ ወደጎን በማድረግ ፣ትግሉን በቀጥታ የሙስና ምንጭ የሆነው መሬትና የመሬት ባለቤትነት ጉዳይ መሆኑን አጽንዖት በመስጠት ፣ የዚህ አቀነባባርና መሪ ተዋናይ ደግሞ በስልጣን ላይ ያለው ህወሓት መራሹ ኢህአዴግ መሆኑን በመገንዘብ የመታገያ አጀንዳ
በማድረግ ሊታገሉት ይገባል።

Thursday, July 27, 2017

Ethiopia: Public Participation Is Essential to Realize the Country’s Visio

       


 





The government frequently made vivid that Ethiopia not only has been registering a double-digit growth, but also undergoing a democratization process anchored in a federal system that guaranteed the respect for the rights of nations, nationalities and peoples in the country.
In doing so, there are efforts to enhance fair benefits among the people. Although Ethiopia was under dire poverty some two decades ago, the efforts exerted to pull it out of the quagmire of poverty have brought hope through better economic performances from year to year.
That has been happening through the concerted efforts made to first invest in the agricultural sector where the country has ample resources of land farming land and a large number of manpower and then integrated with the industrial sector which is believed to be the ultimate goal of any country for development.
The transition from agriculture to an industry led economy has now on its way to become a reality as it corresponds to the facts on the ground. This is becoming a reality because of the full and adequate public participation either directly or through representatives.
The encouraging results are due to fact that the public has empowered to exercise the decisive say vested in it by the Constitution, its sense of belongingness with the deepening of the government’s credibility.
The other positive side of raising public participation is the free political participation and the far sighted development agendas of the government. Besides, this strong collaboration between the government and the people has become tangible due to the passing of decisions by the government to benefit the people and realize sustainable economic growth, an enduring peace and thriving democracy.
Consequently the public raised faith in the government as the decisions are participatory in any majority government agendas. That is why the country has managed not only to develop its economy, but also to ensure its peace and security in the volatile Horn region. Now that the public is involved at every stage of the decision making processes of the government that enhanced the relationship between the two and that relation is based on the principle that the public is the master and the government is its servant.
Citizens are perennially leading a better life and existence find it easier to accept the assertion that Ethiopia is one of the fastest growing economies in the world. They are liable to view the growth as benefiting all of them at various levels.
The country’s development efforts are focused on both material and human aspects that the government and the people it rules are bound to be at better understanding and cooperation in all aspects. It is possible to take public participation in contributing to the construction of the Grand Ethiopian Renaissance Dam and other development projects.
Although some extremist groups have attempted to create cracks that could bring terrible effects among the people and the government, the empowering public have been fighting against such mess and ascertain their peace. That is what we witness from the past few years. The attempts persistently made by anti-peace elements and extremist groups have foiled with full participation of the Ethiopian people and government.
It is a real witness indicating how the government and the people listen to each other. How they could cooperate to build the new Ethiopia where all nations, nationalities and peoples enjoy equal benefits and rights in the country’s wealth.
It has been ascertained time and again over the past twenty six years that Ethiopia’s federal system is anchored in the will of the people. The regional states of the country have for some time now been able to self-administer, use their own language and develop their culture as they see fit.
The constitution affirms that the Nations, Nationalities and Peoples of Ethiopia are strongly committed, in full and free exercise of their right to self-determination, to building a political community founded on the rule of law and capable of ensuring a lasting peace, guaranteeing a democratic order, and advancing their economic and social development. Despite what some anti-Ethiopian unity have been propagating these ideals have been faithfully implemented since the constitution’s enactment.
The ruling Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front has been viewing inward with the deep renewal exercise in which it is supposed to evaluate critically its performance over the past two decades so as to enhance what is good and avoid what is retarding with hones inward looking of its shortcomings.
Public participation could be manifested through the organizing forums where people of all segments or their elect representatives work in collaboration with the government to ensure public benefit in all aspects.
Capacitating the public to have a stake in the affairs of the nation contributed a lot to the growth of the country particularly in the past ten years where the first and the second Growth and Transformation plans have executed. As the foundation of Ethiopian democratic order and economic development is the public it is certain that what has already planed will be a reality and the country will certainly meet its vision of becoming one of the middle income countries in the coming few years. If there is solidarity and public ownership, there is nothing that could be out of the hands of the people.
Due to the strong public participation it won’t be difficult for Ethiopia to provide safe and secure environment at home, continental and global level.
With the strong participation of the people, the country will certainly execute its second Growth and Transformation Plan effectively that could lead it to a middle income economy. With the strong participation of the people, Ethiopia will remain united and strong.
It would be possible to scale up even to take the development to greater heights if the strong participation of people has been maintained. The strong bond existing between the people and government of Ethiopia rendered their differences irrelevant. Consequently, frequent attempts by parochial groups attempted to aggravate ethnic conflicts have failed.
Even in the future, such attempts will not function as the Ethiopian people have learnt a lot from the past twenty five years’ experience that they could be benefited if they work together to realize the Renaissance of the country.

ሰበር ዜና —- ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ የተጠረጠሩ ባለሥልጣናትና ነጋዴዎች ስም ዝርዝር


By ሳተናው July 27, 2017 12:26



በታምሩ ጽጌ
ማክሰኞ ሐምሌ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. መንግሥት እምነት በማጉደልና ሥልጣንን ያላግባብ በመገልገል በአገር ላይ ከ1.15 ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል ያላቸው ተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን
  1. ኢንጂነር ፍቃዱ ኃይሌ
  2. ኢንጂነር ዋሲሁን
  3. ኢንጂነር አህመዲን
  4. ሚስተር ሚናሽ ሌቪ (ትህዳር ኮንስትራክሽን ኩባንያ)
(ከ198 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን
  1. አቶ አብዶ መሐመድ
  2. አቶ በቀለ ንጉሤ
  3. አቶ ገላና ቦሪ
  4. አቶ የኔነህ አሰፋ
  5. አቶ በቀለ ባልቻ
  6. አቶ ገብረ አናንያ ፃዲቅ
(ከ646 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)
መተሐራ ስኳር ፋብሪካ
  1. አቶ እንዳልካቸው ግርማ
  2. ወ/ሮ ሰናይት ወርቁ
  3. አቶ አየነው አሰፋ
  4. አቶ በለጠ ዘለለው
(ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)
ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር
  1. አቶ ሙሳ መሐመድ
  2. አቶ መስፍን ወርቅነህ
  3. አቶ ዋሲሁን አባተ
  4. አቶ ሥዩም ጎበና
  5. አቶ ታምራት አማረ
  6. አቶ አክሎግ ደምሴ
  7. አቶ ጌታቸው ነገራ
  8. ዶ/ር ወርቁ አብነት (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)
  9. አቶ ታመነ ደባልቄ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)
  10. አቶ ዮናስ መርአዊ (የሚኒስቴሩ ባልደረባ ያልሆኑ)
(2.2 ሚሊዮን ዶላር ወይም 51.2 ሚሊዮን ብር ጉዳት በማድረስ)
ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ
  1. አቶ አበበ ተስፋዬ
  2. አቶ ቢልልኝ ጣሰው
(ከ31 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)
  1. አቶ አበበ ተስፋዬ
  2. አቶ የማነ ግርማይ (ጂዋይቢ ኮንስትራክሽን ኩባንያ)
  3. አቶ ዳንኤል አበበ
(ከ20 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)
  1. አቶ ፈለቀ ታደሰ
  2. አቶ ኤፍሬም ታደሰ
(ከ10 ሚሊዮን በላይ ጉዳት በማድረስ)
ኦሞ ኩራዝ ስኳር ቁጥር ፋብሪካ
  1. አቶ መስፍን መልካሙ
  2. አቶ ሰለሞን ከበደ
  3. ሚስተር ሊዮ (የቻይና ጁጂአይሺኢ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ)
  4. አቶ ፀጋዬ ገብረ እግዚአብሔር ብርሃነ
  5. ወ/ሮ ሳሌም ከበደ
(ከ184 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ)

Wednesday, July 26, 2017

በሲያትል የኢትዮጵያዊው አሟሟት እንቆቅልሽ አልተፈታም


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 


አድማስ ዜና፦ ከሲያትል የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው። ባለፈው እሁድ፣ ጁላይ 23 ንጋት ላይ ነው፣ የ 36 ዓመቱ ይትባረክ ደሞዝ፣ ለባለቤቱ፣ “ጓደኞቼን አንድ ቦታ ማድረስ አለብኝ” ይላትና ይወጣል። በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም፣ የጠቀሳቸው ሰዎችና እሱ፣ 25 ጫማ ርዝመት ባለው የይትባረክ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ዩኒየን በተባለ ሐይቅ ላይ ነበሩ።
በመካከል ድንገት ለፖሊስ አንድ ጥሪ ይደርሳል፣ ጥሪውም ከንጋቱ 7 ሰአት አካባቢ ሲሆን፣ በዚህ በዩኒየን ሐይቅ አካባቢ ከሚገኝ ጀልባ አካባቢ ጩኸትና ግርግር ይሰማል የሚል ነበር። ፖሊስ ከስፍራው ሲደርስ፣ በርካታ ሰዎች ጀልባው ላይ ነበሩ፣ እየተጯጯሁም ከመካከላቸው አንዱ ሐይቁ ውስጥ መግባቱንና ሳይወጣ መቅረቱን ይናገራሉ። ፖሊስም ልዩ መሳሪያ በመጠቀም ገባ የተባለውን ሰው ፣ ህይወቱ አልፎ ሊያገኘው ችሏል። ያ ሰው ይትባረክ ደሞዝ ነበር።
ይትባረክ ደሞዝ የሲያትል ከተማ የረዥም ጊዜ ነዋሪ ሲሆን፣ በትራክ ኩባንያ ለረዥም ጊዜ ሰርቷል። የሁለት ልጆች አባትም ነው። በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ አሟሟቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። ፖሊስ አስከሬኑን እየመረመርኩ ነው፣ የምርመራውን ውጤትም በቅርቡ አሳውቃለሁ ብሏል። ዘልሎ ገብቶ ይሁን ሆን ተብሎ፣ ወይም ሌላ ምክንያት ይኑር ከምርመራው በኋላ የሚታወቅ ይሆናል። አድማስ ሬዲዮ በቅዳሜ ፕሮግራሙ የምርመራውን ውጤት ጨምሮ የሚያውቁትንም ሰዎች በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ ለመቅረብ ይሞክራል።
(komo news)

Monday, July 24, 2017

አቶ አርከበ እቁባይ ለህክምና ጀርመን መግባታቸው ተሰማ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |




(ዘ-ሐበሻ) የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከፍራንክፈርት እንደገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አርከበ እቁባይ ታመው ጀርመን ፍራንክፈርት በህክምና ላይ ይገኛሉ::
አቶ አርከበ እቁባይ የህመማቸው ምንነት ያልታወቀ ሲሆን ፍራንክፈርት ኤርፖርት የሚሰሩ ወገኖች በዊልቸር ሲሄዱ እንዳዩዋቸውና ህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸውልናል::
አንዳንድ ምንጮች አቶ አርከበ የደረሰባቸው አደጋ ከደረጃ ወድቀው ነው ሲሉ ይናገራሉ::

መርካቶ አድማ ላይ ነው

መርካቶ አድማ ላይ ነው #Ethiopia #TaxHikeProtests #Miniliksalsawi
መርካቶ የሀገሪቱ ዋናዉ የገበያ ማዕከል ሁሉም ነጋዴ የቀን ገቢ ግምቱን በመቃወም የስራ ማቆም አድማዉን ጀምሮታል
ህዝብ ሲቆጣ ስራዉ ሁሉ ያስደነግጣል ያ በሰዉ ብዛት...
የሚጨናነቀዉ መርካቶ ጭር ብሏል እስካሁን ሚሊተሪ
ተራ፡ ሸማ ተራ፡ ሞሰብ ተራ፡ ጣሳ ተራ ፡ ሸራ ተራ ፡ ሰባተኛ
አብዶበረዳ፡ ሲዳሞ ተራ : ምናለሽ ተራ፡ ጣና የገበያ
አዳራሽ አዳራሽ የገበያጠማዕከል ፡ምዕራብ አካባቢ
.....ሁሉም ዝግ ናቸዉ ፡፡

ካድሬዎችና ፖሊሶች በግድ ለማስከፈት ሙከራ እያረጉ
ነዉ ፡፡ህዝብን የጠላ መንግስት ራሱም የተጠላ ነዉ !!








Saturday, July 22, 2017

ወያኔዎች የሰላሌ ዞን የፊቼ ከተማን የመብራት ሀይል ጣብያ ፈትተው ሲዘርፉ ነግቶባቸው ህዝቡ ደርሶባቸው

ባለፈው የአማራ ክልል መንግስት ወያኔ ስልጣን ከያዘ ምንም አዲስ የኤለክትሪክ ማስፋፊያ አልተሰራም ብሎ ሲያማርር ነበር። በኦሮሚያ ደግሞ ወያኔዎች የተተከለውን መንቀል ጀምረዋል::
#Ethiopiandj.com
ወያኔዎች የሰላሌ ዞን የፊቼ ከተማን የመብራት ሀይል ጣብያ ፈትተው ሲዘርፉ ነግቶባቸው ህዝቡ ደርሶባቸው አስጥሏል ይላል ከታች ያለው ዘገባ

በሰሜን ሸዋ ዞን በሰላሌ በፊቼ ከተማ...
የሚገኘውን የዞኑ እና የፊቼ መብራት ሀይል ጣቢያ በ12/11/2009 ምሽት ላይ የትግረኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ሰዎች ፈታተው በማወላለቅ በእንጨት አንድ ላይ አድርገው በማሰር በመኪና ለመጫን ዝግጅት ላይ እንዳሉ ስለነጋባቸው ህዝቡ በጩኽት ደርሶ አስጥሏል:: የተዘረፈውን የመብራት ሀይል እቃዎች ሊጭኑባቸው የነበሩት መኪናዎች የመንግስት ሲሆኑ የፌደራል ታርጋ የለጠፉ ሲሆኑ የተወሰኑት ሲያዙ ሌሎቹ አምልጠዋል::

በዚህ ዝርፊያ ላይ እያሉ በህዝቡ ርብርብ እጅ ከፈንጅ የተያዙት ሰዎች የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ሲሆኑ ከሁለት ሰዎች በስተቀር ሌሎቹ ትግርኛ ቋንቋ እንጂ አይሰሙም:: በእጃቸው የያዙት ደብዳቤ ከፌደራል የተፃፈ እና የዚው ዞን አስተዳደር እና ከንቲባ ፊርማ ብቻ ያለው ነው:: እነዚህ ሰዎች ለግዜው ቁጥጥር ስር ቢውሉም የአጋዚ ጦር ሀይል ከፖሊስ እጅ ምሽት ላይ አስለቅቋቸዋል::
ከዚህ በፊትም በደርግ ዘመን ከተማዋን ሲያገለግል የነበረ ጀነሬተር በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ወደ ትግራይ በውሰት ተብሎ ተወስዶ በዛው ደብዛው ጠፍቶ ቀርቷል::"
ምንጭ: ጅዋር Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ sitt bilde.Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ sitt bilde.ሙሃመድ