Tuesday, December 27, 2016

የሺዓ ጥምር ኃይል የሶርያን ሱኒዎች እየተዋጋ ነዉ ተባለ | ሊደመጥ የሚገባው ዜና ትንታኔ በሳዲቅ አህመድ

ችግሩ የሱኒና የሺአ እንዳይመስል የሱኒ አገራት በፖለቲካዊ ተአርሞ ለጉዳዩ ተገቢ አትኩሮት ሳይሰጡት፤ ኢራናዊዉ የሺአ አብዮት ናይጄሪያ ደርሶል። አህባሽ በሚባል ጭምብል ኢትዮጵያ የገባዉ የሒዝቡላህና የኢራን ቀመር ኢትዮጵያን መረጋጋት ነፍጓል። አህባሽ የሚለዉ መጠሪያ በህዝብ ጥረት በመክሰሙ በህገመንግስታዊ ከለላ ስር የኢራኑ ስሌት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሺአ መጠሪያን ይዞ አንገቱን ቀና እያደረገ ነዉ። በኢራን የሚደገፉትን የየመን የሺአ አማጽያን ስምሪት ለመግታት በሚያስመስል መልኩ የአረብና የሙስሊም አገራት የአስብ ወደብን ተከራይተዉ ሰፍረዋል። ወደ ኢትዮጵያ እየመጣ ያለዉን ፖለቲካዊ ማራቶን ምንጭ ለመቃኘት ወደ ሶር ያ ተጉዘናል።
***
ቢቢኤን ታኅሣሥ 16/2009 
አለዋት በመባል የሚታወቀዉ የሺዓ ቅርንጫፍ እምነት ተከታይና የቃልብያ ጎሳ አባላት የሆኑት የአል አሳድ ቤተሰቦችና የሶርያ ገዥዎች የተነሳባቸዉን ህዝባዊ አመጽ ለመደምሰስ ሁሉም የሺዓ ሐይላት ሶርያ ዉስጥ በመሰባሰብ ሲኒዎችን እየተዋጉ መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ።
ፈረንሳይ ሶርያን ቅኝ ትገዛ በነበት ወቅት ከቅኝ አገዛዙ ሐይሉ ጋር ወግነዋል ተብለዉ መገለል የደረሰባቸዉ የአለዋት እምነት ተከታዮች በአሁኑ የሶርያ የፕሬዝዳንት አባት ሐፊዝ አል አሳድ አማካኘት ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና መፈንቅለ መንግስትን ተከትሎ በመጋቢት 3/1963  በጃቸዉ የገባዉን ስልጣን ለማስቀጠል ኢራን በበላይነት በምትመራዉ የሺዓ ሐይልና በሩስያ እየተደገፍፉ በሶርያ ሱኒዎች ላይ የሚያደርሱት እልቂት እየከፋ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።
ሒዝቡላህ፡
ለሶሪያ መንግስትና ለኢራን ቅርበት ያለዉ በሐሰን ነስራህ የሚመራዉ ሒዝቡላህ በተለያዩ መንግስታትና በአረብ ሊግ አሸባሪ ተብሎ ይፋዊ መገለል የደረሰብት ቢሆንም፤ በሶሪያ መሬት ላይ በመንቀሳቀስ የሶርያ ሱኒዎች ላይ የከፋ ጭፍጨፋ እያከናወነ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ። ሒዝቡላህ በሊባኖስ ዉስጥ እንደፖለቲካ ፓርቲ በህጋዊነት የሚንቀሳቀስ ቢሆንም የጂሃድ መማክርት የሚል የራሱ የሺዓ የጦር ሰራዊት ያለዉና በሊባኖስ መንግስት ላይ እራሱን የጫነ ሌላ መንግስት መሆኑን ተንታኞች ያስረዳሉ።
ሒዝቡላህ ከኢራን ሌላ ከፍተኛና ታላቅ ወታደራዊ ልምምድ ያለዉ የሺአ ሐይልና ከኢራኑ ልዩ ጦር  ቀጥሎ በሺዓዎች ዘንድ ተምሳሊታዊ የሆነ ቦታ ያለዉ መሆኑ ይታወቃል።ሒዝቡላህ 65ሺ ተዋጊ ወታደሮች ያሉት ሲሆን በብቃትና በልምድ ከሊባኖስ የመከላከያ ሰራዊት በተሽሻለ መልኩ ጠንካራ እንደሆነ ይነገራል።በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮቹን ወደ ሶሪያ የላከዉ ሒዝቡላህ ከ1500 በላይ የሚሆኑት ሚሊሻዎቹ ሶርያ ዉስጥ በሱኒ አማጽያን እንደተገደሉበት ቢዘገብም፤ ሒዝቡላህ በሶርያ መሬት ላይ ከሌሎች የሺዓ ሐይላት ጋር ጠንክሮ እየሰራ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።
ጀይሸል መህዲ፡
ዝርያቸዉ ከሊባኖስ እንደሆነ የሚነገረዉ በኢራቁ የሺዓ አስተማሪ ሙቅተዳ አልሳደር የሚመሩት የጀይሸል መህዲ ሚሊሻዎች በሶርያ ዉስጥ የሰፈሩ ሲሆን የሶርያ ሱኒዎችን እንደሚዋጉም በአረብ የመገናኛ ብዙሗን በስፋት ይዘገባል። ሙቅተዳ አልሳደር ተሰሚነት ያላቸዉ የሺዓ መሪ ናቸዉ። የአላሳደር ንቅናቄ በኢራቅ ፖለቲካ ዉስጥ ስር የሰደደ ሲሆን፤ ንቅናቄ የኢራቅን መንግስት ከጀርባ ሆኖ ይሾፍራል ሲሉም ክስ የሚያቀርቡ አሉ።የሙቅተዳ አልሳደር የሺዓ ሚሊሻዎች በኢራቅ ፓርላማ እዉቅናና ደሞዝ የተመበላቸዉና እዉቅና ያላቸዉ የሺዓን የበላይነት ለማስረጽ በገሃድ እንደሚቀሳቀሱ ኢራቃዉያን ሱኒዎች ያስረዳሉ።የሙቅተዳ አልሳደር ሚሊሻዎች ማእከላዊ የሆነ የሺዓ የጦር ሐይልን በሶርያ ዉስጥ እንዲደራጅ ከፍተኛ ሚና ያላቸዉ መሆኑን በመስኩ ጥናት የሚያከናዉኑ አካላት ያስረዳሉ። 
የአብዱል ፋድል አል አባስ ብርጌድ፡
አብዱል ፋድል አል አባስ በመባል የሚታወቀዉ የሺዓ ብርጌድ ሶርያ ዉስጥ ባሉ የሺዓ ሐይላት በግል የተቋቋመ ሲሆን፤ ብርጌዱ ከኢራቅ ወደዉ የተቀላቀሉትን የሺዓ ሚሊሻዎችና ሶርያዉያንን በማሰላፍ ሱኒዎችን እየተዋጋ መሆኑ ይታወቃል።
የሊዋ አል ፋጢሚዩን የጦር ብርጌድ
በኢራን የሚደገፈዉና ኢራን ያስታጠቀቸዉ ሊዋ አልፋጢሚዩን የተባለዉ የአፍጋኒስታን ሺዓዎች የጦር ብርጌድ ሶርያ ዉስጥ የገባ ሲሆን ይኸው ብርጌድ ከሌሎች የሺዓ ሐይላት ጋር በመጣመር የሶርያን ሱኒዎች ይዋጋል። 
የአፍጋኒስታኑ ሊዋ አልፋጢሚዩን ብርጌድ የፕርሺያን ቋንቋ በሚናገሩ አፍጋኒስታዉያን የተዋቀረ ሲሆን፤ አፍጋኒስታን ከሩስያ ጋር ባደረገቸዉ ጦርነት ሳቢያ ወደ ኢራን ተሰደዉ የገቡት ስደተኞች ለብርጌዱ የጀርባ አጥንት እንደሆኑት ይነገራል።በኢራን አልረዳም ሲል የሚክደዉ ሊዋ አልፋጢሚዩን የሰይዳ ዘይነብን መቃብር እንጥብቃለን በሚል የሺዓ ተልእኮ ሁለት ሺ ሚሊሻዎቹን ቀደም ሲል ሶሪያ ዉስጥ ማስፈሩ ይታወቃል። የሊዋ አልፋጢሚዩን ብርጌድ በኢራቅና በኢራን ጦርነት ወቅት ከኢራን ጋር አብሮ የተዋጋ ሲሆን ሶሪያ ዉስጥ በትጋት እንደሚምቀሳቀስም ይታወቃል። 
የዙል ፈቅር ሚሊሻዎች
እራሳቸዉን ዙል ፈቅር የሚል መጠሪያ የሰጡትና በግል የተደራጁት የኢራቅ ሺዓዎች ሶሪያ ዉስጥ ሱኒዎችን ለመዋጋት ሰፍረዋል። ከአቡ ፋድል አል አባስ ብርጌድ ጋር በመተባበር ሰይዳ ዘይነብ በመባል በሚታወቀዉ አካባቢ ሰፍረዋል።
የኢራቁ በድር ማህበር፡
የኢራቁን የቀድሞ ፕሬዝዳንት በመቃወም የተቋመዉ ሺዓዉ የኢራቁ በድር ማህበር ሁለት ሺ የሚደርሱ ሚሊሻዎቹን ወደ ሶርያ ልኳል።የሶርያ ሱኒዎችንም እየተዋጋ ነዉ።
ከፊል ዘይነብ፡
በኢራቁ ሙቅተዳ አልሳደር ከሚመራዉ የመህዲ ጦር የተገነጠለዉ ከፊል ዘይነብ የሰኘዉ ጦርም ሶርያ ዉስጥ ሰፍሯል።አቅሙ በቻለዉ መጠንም የሶር ያን የበሻር አል አሳድ መንግስት ይደግፋል። የአዋቱን የሶር ያ መንግስት ለመደገፍ ሐሉን ይዞ ሶር ያ ዉስጥ ከትሟል።
አል ሰይብ አልሐቅ 
ከኢራቁ የመህዲ ጦር የተገነጠለዉ አል ሰይብ አል ሐቅ በኢራን የሚደገፍ ነዉ። ከሒዝቡላህ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳለዉ ይታወቃል። ነዉጠኛ፣አሽባሪ፣የማህበራዊ ግልጋሎት ሰጭ፣የፖለቲካ ሐይል እንደሆነ የሚታወቀዉ አልሰይብ አል ሐቅ በጣም አደገኛ የሆነ የሺአ ሐይል መሆኑ በመዛግብት ላይ ሰፍሯል።አደገኛነቱን በተግባር ለማሳየት ሶር ያ ዉስጥ ይገኛል።
*****
መሰረቱን ኢራን ዉስጥ አድርጎ በመካከለኛዉ ምስራቅ ዉስጥ የሚቀሳቀሰዉ የሺዓ አብዮታዊ ጥምር ሐይል በኢራቅ፣በባህሬን፣በየመን፣በሊባኖስ፣ በሶርያና በአፍጋኒስታን ዉስጥ የሚያደርገዉ ወታደራዊ መስፋፋት በምእራቡም ይሁን በምስራቁ አለም ባሉ የመገናኛ ብዙሗን እምብዛም አትኩሮትን አላገኘም። 
ይህንን ቀዉስ ሱኒ ሙስሊሞች የሺዓና የሱኒ ክፍፍል እንዳይመስል እራሳቸዉን በፖለቲካዊ ተዓርሞ ዉስጥ አስገብተዉ ከእዉነታዉ ይሸሻሉ የሚሉት አስተያየት ሰጪዎች፤ የሺዓ የጦር ሐይሎች ሐይማኖትን መሰረት ያደረገ ጦርነት ላይ መሆናቸዉን ግን አይክዱም። የሺዓ ቡድናዊ ሚሊሻዎችና መንግስታዊ መዋቅር ያላቸዉ የጦር ሐይሎቻቸዉ በአመራር የተለያዩ ቢመስሉም የአላማ መስተጻምር ያላቸዉና ግባቸዉ አንድ መሆኑን የመካከለኛዉ ምስራቅ የፖለቲካ ሒደትን የሚያጠኑ አካላቶች ይገልጻሉ።
ሶሪያ ዉስጥ ጥምር የሺዓ ሐይል ሱኒዎችን እየተዋጋ ነዉ የሚሉት ተንታኞች፤ የየመኖቹ የሺዓ የሁቲ አማጽያን መካን ወይም ጅዳን ኢላማ ያደረገ ሚሳኤል ተኩሰዉ በሳኡዲ ጸረ-ሚሳኤል ተመቶ መውደቁን እያስታወሱ፤ የመገናኛ ብዙሗን ቸልታንና የመንግስታትን ዝምታን በመገምገም ወደፊት ሊከሰት የሚችለዉን አሻግረዉ በማየት ስጋታቸዉን ያስረዳሉ።

የ21ኛው ክፍለ – ዘመን የአማራ ይሁዲ (ማተቤ መለሰ ተሰማ) (ማተቤ መለሰ ተሰማ)

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ ከጀርመኑ ናዚ ሺህ ጊዜ የከፋና በዚህ ዘመን ሰው ያደርገዋል ተብሎ የማይታስብ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።
ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን ህዋሃት ገና ከመነሻው በማንፌስቶው አማራ የትግራይ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው። በማለት አስፍሮና እቅድ ነድፎ እየሰራበት የመጣ ከመሆኑም በላይ ህዝብን ሳያፍሩ መለስ ዜናዊ ፣ ስብሃት ነጋ፣ ሳሞራ የኑስና ተፈራ ዋልዋ በአግኙት አጋጣሚ ሁሉ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃየማኖት ተከታዩን ላይነሳ አርቀን ቀብረነዋል በማለት ሲነግሩን ኖረዋል። የጥፋት መልዕክተኛው ቡድን ህዋሃት ከደደቢት ተነስቶ እየተስፋፋ ሲሄድ በትግራይ ውስጥ ብቻ በሚነቀሣቀስበት ወቅት ቀዳሚ የዘር ማፅዳት ሠለባ ያደረገው እዚያው ትግራይ ውስጥ በሥራም ሆነ በሌላ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ምክንያት ይኖሩ የነበሩትን ዐማሮች ነበር። ከእነዚያ ዐማሮች መካከል አንዳንዶቹ ከትግሬዎች የተጋቡ እና የተዋለዱ ነበሩ። ለወያኔዎች ግን ዐማሮች ሰለሆኑ መወገድ ነበረባቸው። ስለዚህ አንድ በአንድ በወረንጦ በመልቀም ጨፈጨፋቸው።
ህጻንና ሽማግሌ እንኳን ሳይመርጥ በጅምላ እየርሽነ በመቅበር የቀጠለው። በውጊያ ወቅት የሚማርከውን ወታደርም ዘሩን በመጠየቅ አማራ ነኝ ያለውን በመግደል ሌላውን ግን ፍላጎቱን እየጠየቀ ወደቤቱ ይልከው፣ ወይንም ከጎኑ ያሰልፈው ነበር። ይህን እንድል የመንፈው ጉልበት የሆነኝ በአይኑ ያየ ሰው ስላረጋገጠልኝ ነው። ማስረጃየ አሁንም በህይወት ስላለ ቀን ሲወጣ ወይንም እንደኔ ከሃገር ሲሰደድ ምስክርነቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ ስለሚናገር ለደህንነቱ ስል በስም አልጠቅሰውም። ታሪኩ እርጅም ነው ግን በአጭሩ ላቅርበው።
ነገሩ እንዲህ ነው በደርግ ዘመን በዚያኔ አጠራር ነው የምጠቀመው። በጎጃም ክፍለሃገር፣ በቆላ ደጋዳሞት አውራጃ ውስጥ ከሚገኙ 7 ወረዳዎች መካከል ቡሪ ሽህኩዳድና ጓጉሳ ወንበርማ ወረዳ። ነዋሪ የሆኑ ኦሮሞኛን ከአማርኛው እኩል የሚናገሩ ሰዎች በርካታ ናቸው። ከዚህ ማህበረስብ መካከል 2 ወንድም አማቾች ታፍሰው ወደ ብሄራዊ ውትድርና ይገባሉ። የወጣቶቹ ግዳጅም ትግራይ ክፍለሃገር ይሆናል። በአንድ የተረገመች ቀን ግን ሁለቱም ይማርኩና በሺ ከሚቆጠር ሌላ ምርኮኛ ጋር ይቀላቀላሉ። ዋል አደር እንዳሉም የህዋሃት ባለስልጣናት ምርኮኛው ወደስፈረበት በመሄድ።
ዘሩን እየጠየቁ አማራ ነኝ ያለውን ለብቻ ከሌላ ብሄርስብ ነኝ ያለውን ለብቻ ሲያሰልፉ። ከጎጃም ለሄዱት ወንድም አማቾች ተራ ይደርስና መጀመሪያ የተጠየቀው ታናሹ አማራንኝ ስላለ የአማራው ምርኮኛ ወዳለብት እንዲስልፍ የደርጋል። ታላቁ ሲጠየቅ ኦሮሞ ነኝ በማለቱ ቋንቋን እንዲያወራበት ተደርጎ አቅላጥፎ ስለሚናገር ሰልፉ ከሌሎች ጋር ይሆናል። በዚህ ሁኔታ ማጣራቱ እንዳለቀ አማራነኝ ያለው መርኮኛ እንዲገደል ተወሰነበትና በመትረየስ ተረፈረፈ። ሌላው ግን ቅድም እንዳልሁት ፍላጎቱ እየተጥየቀ ተስናበተም አብሮ ለመታገል የወሰነም ተስለፈ። ወንድሙ አማራነኝ በማለቱ ሲገደል እሱ ኦሮሞነኝ በማለቱ የተረፈው ከተስናባቾቹ አንዱ ሆንና በወሎ አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲሄድ እኔ ያኔ ደብረብርሃን ስለነበርሁ ተቀብየው የተወሰኑ ቀናት እኔጋ አርፎ ስለነበር ነው ድርጊቱን ያጫወተኝ። ሌላው ህዋሀት ከተማራኪ ወታደሩ ውስጥ አማራውን እየመረጠ በመግደል እንደመጣ የሚያሳየው መረጃ አንድም የአማራ ምርኮኛ ወታደር እንደ እነ አባዱላ ገመዳ፣እንደነ ኩማ ደመቅሳ፣እንደነ ባጫ ደበሌ፣ እንደነ አለማየሁ አቶምሳ ወዘተ አብሮት እየስራ ያለ አንድም አማራ አለመኖሩ ነው።ምክናያቱም የተማረከውን አማራ ሁሉንም እየግደለ ነው የመጣውና። ህዋሃት በትግል ላይ ሳለ በትግራይ ክፍለሃገር ይኖሩ የነበሩ አማራወችን ብቻም አልነበርም እይገደለ የመጣው።
የወልቃይት፣ ጠገዴና የአርማጭሆ ነዋሪ የሆነውንና ይህንን ለም ቦታ ወደትግራይ ስንከልለው እኛ ጎንደሬ እንጅ ትግራይ አይደለንም በማለት ተቃውሞ ሊያስነሳብኝ ይችል ይሆናል ብሎ የገመተውን ሁሉ በስውር እየገደለ በመቅበር ነው የምጣው። ታምራት ላይኔ እንዳለው ህዋሃት በጦርነቱ ወቅት የአማራ ክልልን ውሱን መሰርተልማት እያፈራረስ፣ ንብረቱን ጠረጴዛና ወንበር ሳይቀር እየዘረፈ ወደትግራይ በማጋዝ ነው አዲስ አበባ የገባው። ወያኔ በምዕራባውያን ሃአገሮች ሙሉድጋፍ የኢትዮጵያን መንግስትነት በትረ ስልጣን ከጨበጠ በኋላም የመጀመሪያ ስራው ያደረገው። ሌላው ኢትዮጵያውያን በአማራው ሕዝብ ላይ እንዲነሳ መቀስቀስ ነበር። ለዚህም አመች ሆነው የተገኙት በአማራው ስም ሲነግዱና ደሙን ሲመጡ አጥንቱን ሲግጡ ሲያስግጡ የኖሩት ሁለቱ ባንዳዎች ማለትም ታምራት ላይኔና ዳዊይት ዩሃንስ ነበሩ። ያኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበረው ታምራት ላይኔ በሃረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሴ፣ በአፋርና በሶማሌ ከልሎች። አፈጉባኤ የነበረው ዳዊይት ዮሀንስ ደግሞ በጅማ፣ በወለጋ፣ በኢሉባቦር ወ.ዘ.ተ. እየተዘዋወሩ። ይህ አማራ የተባለ ነፍጠኛ ለመቶ አመታት ሲዘርፍህ፣ ሲገፍህ ሲያሰቃይህ ኖሯል። ኦሮሞውን ከብት፣ ሱማሌና አፋሩን ሽርጣምና ግመል ጎታች እያለ ሲያሸማቅቅህ ኖሯል። አሁን ሜዳውም ፈረሱም እነሆ አማራው ከናንተ መሃል ምን ይሰራል፣ በማለት ቀስቀስው እንደተመለሱ። በአሰቦት ገዳም፣ በበደኖ፣በወተር፣ በጋራሙለታ፣ በገለምሶ፣ በአንጫር፣ በዳኖለቡ፣ በወፌ ዳንሴ፣በዳጉ፣ በጨሪቻ፣ በበዴሳ፣ በድሮባ፣ በአሬሌ፣ በደደር፣ ወዘተ። እንዲሁም ኢሰመጎ ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው በአርሲ በአርባጉጉ፣ አውራጃ በአስኮ፣ በጉና፣ በጮሌ ወረዳዎች አማራው እየተመረጠ ህጻናትና ነፍስጡር ሴቶች ሳይቀር። አነገቱ በሰይፍ እየተቆረጠ፣ እራሱ በፋስ እየተፈለጠ፣ ሆዱ በሳንጃ እየተዘነጠለ፣ ከእነ ህይወቱ በገደል እየተጣለ፣ ከሁለት መቶሺህ በላይ አማራ ያለ እርህራሄ አልቋል። በዚህ ወቅት አሶሳ ውስጥ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠር አማራ ከያለበት ተሰብስቦ በሳርቤት ውስጥ እንዲገባ ተደርጎና በር ተዘግቶበት በእሳት ተቃጥሏል።
በጣም ዘግናኙ ደግሞ ከተጨፈጨፈው አማራ ውስጥ ከአካሉ የተቆረጠውን ስጋ እንዲበላ መደረጉ ነው። የገዛ ስጋውን (የእራሱን ስጋ) እንዲመገብ ከተደረጉት መካከል ጋራ ሙለታ ውስጥ በእህል ንግድ ትተዳደር የነበረችዋና ጡቷን ቆርጠው ካበሏት በኋላ የገደሏት እታፈራሁ ዳኘ ተጠቃሽ ናት። በመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትዕዛዝ። በደቡብ ክልል ከጉራ ፈረዳ 75000። ከቤንሻጉል ክልል በመተከልና ከማሽ ዞኖች 25000 በድምሩ 100000 መቶሺህ አማራ በመብራት እየተፈለገ ለዘመናት ለፍቶ ያጠራቀመውን ሃብት ንብረቱን ተዘርፎ እንዲባረር ተደርጓል አሁንም ማፈናቀሉ እንደቀጠለ ነው። ታምራት ላይኔ ጠቅላይ ሚኒስቴር በነበረበት ባንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር። “የትምክተኛውንና ነፍጠኛውን የአማራ ስርዓት እንዳይመለስ አድርገን አሰናብተነዋል። ምናልባት እኛ በህይወት እያለን፣ በታምር እንደሚመለስ ከተረዳን ግን ቅድሚያ “መሰረቴ ነው የሚለውን ክልል” ውስን መሰረተ ልማቱን ዶጋ አመድ አድርገን ተጨማሪ ሊማሊሞ ገደል እናስረክበዋለን። ገደል ላይ ደግሞ ምን ያህል ሊቆይ እንደሚችል እድሜ ካለን የምናየው ይሆናል። ሌላዉ አለ ታምራት ቀጠለና፣ ሌላዉ ነፍጠኛው የአማራ ተመልሶ አንገቱን እንዳያቀና ጭራቅነቱን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ ልጆች ለማሳወቅ በመደበኛ ትምህርት መስጠት መንግስታዊ ግዴታችን ነው።”በማለት ነበር የዛተው። ጸረ አማራው ታምራት ላይኔ በአማራው ላይ ያለመውን ጥፋት የመተግበር እድሉን ቢያጣም።
የምግባር ጓዶቹ እራዩን አሳክተውለታል። ማለትም በልማትና በሃብት ክፍፍል አምስት ሚሊዮን የማይሞላው የትግራይ ህዝብና ከሃያ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የአማራ ህዝብ ልዩነት የሰማይና የምደር ያህል የተራራቀ ነው።ባሳለፍነው እሩብ ምህተ አመት ውስጥ በአማራው ክልል ከዳሽን ቢራ በቅር እዚህ ግባ የሚባል ዘመናዊ ኢንዱስትሪ አልተተከለም። ትግራይ ክልል ግን ኢንዱስትሪ በኢንዱስትሪ የተጥለቀለቅች ናት። ለማዕከላዊ መንግስት ምንም አይነት ፈሰስ የማያደርገውና ለትግራይ ልማት ብቻ የሚስራው የ53 ቢሊዮን ብር ሃብት ያካበተውና 70 የተለያዩ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎ የሚገኘው ኢፈርት። ግዙፎቹን ኢንዱስትሪዎች ማለትም ሞሶቦ ስሚንቶ ፋብሪካን፣ መስፍን ኢንጅነሪንግን፣ ሱር ኮንስትራክሽንን፣ አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካን፣ ጉና ቢዝነስን፣ ኢዛና ወርቅ፣ ሜጋ ኔት ኮርፖሪሽን ወዘተ በሃገሪቷ ገንዘብ ተቋቁሞ ጥቅሙ ግን ለትግራይ ብቻ ከመሆኑም በላይ እንኝህ ድርጅቶች ከባንክ የተበደሩት በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ በተበላሽ ብድር እንዲመዘገብ ይደረጋል እንጅ አንድ ሳንቲም እንኳን ለአበዳሪው ባንክ ተመልሶ አያውቅም። ሌላው የፌዴራሉ መንግስት አመታዌ በጀት ሲመድብ በህዝብ ብዛት አራትና አምስት እጥፍ ከሚበልጡት ከአማራና ኦሮምያ ክልሎች በእጥፍ የሚበልጥ ገንዝብ ነው ለትግራይ ክልል የሚመደበው።
እዚህ ላይ እንዲታወቅልኝ የምፈልገው ትግራይን በማንጻጸሪያነት ሳነሳ የትግራይን ህዝብ በመጥላት አይደለም። የህዋሃትን ክፋትና ጥፋት ለማሳየት እንጅ። ለነገሩ ወያኔ ጥቂት የማይባል የትግራይ ነዋሪን። አማራ ጠላትህ ነው በማለት አሳምኖታል። ምክናያቱም በአቶ አለም ሰገድ አባይ ጥናታዊ ጽሁፍ ወይንም መጻፍ ላይ የትግራይ ህዝብ ጠላትህ ማነው ሲባል 81% አማራ ነው እንዳለ ተመዝግቧል። አማራው ግን የትግራይን ህዝብ ጠላት ብሎ አያውቅም። አማራው በጅምላ የሚታረደው፣ በገፍ የሚፈናቀለውና ከምር የተገፋው በሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያዊና አካባቢ በቻ አይደለም። ክልልህ ነው በተባለውም በከፋ ሁኔታ የቀጠለ ነው እንጅ። የአማራ ክልል መሪ ሆኖ ለረጅም አመት የገደለው ያስገደለው ያሰደደው አዲሱ ለገሰ ። የስራ መጀመሬያ ያደረገው። አማራው በማንንቱ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ፣ አንገቱን እንዲደፋ ሞራሉ፣ ምግባራዊ ድፍረቱና ሰባዊመብቱ ከውስጡ እንደጭስ እየተነነ እንዲጠፋ ለማድረግ በአንድ ወይንም በሌላ መንገድ ከማህበረሰቡ የተገለሉ፣ እንደነ አለምነው መኮንን አይነት ታሪካቸውን ለጥቅማቸው፣ ሰብናቸውን ለሆዳችው አሳልፈው የሸጡ ባንዳ ዎችን በመመልመል በዘለፋና በስድብ አሰልጥኖ በማሰማራት ህዝብን በጀምላ ነፍጠኛ፣ ትምክተኛ፣ ጥገኛ፣ ቢሮክራት ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ውርጀብኞችን በስፋት ማሰራጨትን ነበር።
በቀጣይ በአመት ሁለት ጊዜ እርጭት በማካሄድ ላይ ያለውን በአማራ ክልል ከረጅም አመታት ጀምሮ የነበረውን የወባ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጠቅላላ በመዝጋት ከ1984 እስከ 1987 ድረስ የወባ ወረርሸኝ ገብቶ ከአንድ ቀበሌ በቀን ከ10 እስከ 15 የሚደርስ ሰው እየሞተ ቀባሪ እንኳን ያጣበት ሁኔታ ሲከሰት በአዲሱ ለገሰ የሚመራው የአማራ ክልል መንግስት እንደ መንግስት አንድም የመከላከል ሙከራ አላደረገም። በወባና ሌሎች ሰው ሰራሽ በሸታወች ያለቀው አማራ ሳያንስ ቀሪው ደግሞ እንዳይወልድ በጤና ተዋልዶ ፕሮግራም ሰበብ አሁንም በየትኛውም አካባቢ ያልተሞከረውን፡ የአማራ ወንድ አርሶ አደሩን በገንዘብ በማባበል፣ እንቢሲል መሪትህን እንነጥቅሃለን እያሉ በማስፈራራትና በማስገደድ ወደፊት ዘር እንዳይተካ የዘር ብልቱን በሀኪሞች እንዲነኮላሽ በማድረግ። ሴቱ እንዲመክን መርፌ በመውጋት የዘር ማጥፋት ዘመቻውን በከፍተኛ ደረጃ አካሂደውበታል። ዛሪም ይህ እኩይ ድርጊት ተጠናክሮ ቀጥሏል። በተለይም በሰሜን ጎንደር ወልቃይት ጠገዴን ለትግራይ ለማድረግ ነባሩን ህዝብ ማጥፋት፣ የሚተርፍ ካለም ማዳቅል የሚል መሪ ፕሮግራም በመንደፍ ማምከኑም ሆነ መግደሉ በከፋ ሁኔታ ቀጥሏ። ከሞትም ሆነ ከመምከን የምትተርፍ ሴት ካለች ተገድዳ ከትግራይ ተወስዶ ለሰፍረው ወንድ ሶስተኛም ሆነ አራተኛ ቅምጥ ሆና እንድትወልድ በመደረግ ላይ ነው። በሌላ በኩል ነግዶ አደሩን በዝባዥ፣ ጥገኛ ባለሀብት በማለት።
እንደ ዶሮ ከጉልበቱ በላይ ለብሶ ያለመጫሚያ የሚኳትነውን አርሶአደር ደግሞ ቢሮክራት፣ ንክኪ በማለት፡ ንብረትና መሪቱን በመንጠቅ፡ ቅዬውን እየለቀቀ እንዲሰደድ፡ በማድረጋቸው 1993 ዓ.ም ህግና መንግስት ያለ መስሎት፡ አዲስ አበባ ድረስ ተጉዞ ፒያሳ ከሚገኜው ጊወርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመስፈር የቀን ሀሩር የሌሊት ቁር እየተፈራረቀበት እራብና ጥም እያሰቃየው ፍትህ ቢለምንና ቢማጸን ከወያኔ መንግስት ያገኘው መልስ ድብደባ እስራትና ግድያ ነበር። በዚህ ወቅት ከ80 የማያንሱ ሰዎች ለአቤቱታ እንደወጡ በወያኔ ደህንነቶች ታፈነው የት እንደደረሱ እስካሁን አይታወቅም። የተረፈው ሕይወቱን ለማሰንበት ሲል ወደወለጋ በመሄድ ጦማደር መሪት መርጦ ስፍሮ መኖር ሲጀምር ደገሞ የወያኔ ካድሪዎች ወራሪ ጠላት የመጣበት በማስመሰል የአካባቢ ኗሪ የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነውን ማህበረሰብ ቀስቅሰው በማስነሳት ከአማራ ክልል ሄዶ በሰፈረው ህዝብ ላይ ጦርነት አስከፍተው ሴትና ሕጻናትን እንኳን ሳይተው በጅምላ በመጨፍጨፍ ከ6000 ያላነሰ የአማራ ህዝብ እንዲያልቅ ተደርጓል። ከዚህ ተርፎ ምንም ንብረት ሳያንጠለጥል ሚስት የባሏን፣ ባል የሚስቱን፣ወላጅ የልጁን፣ ልጅ የወላጁን፣ እሪሳ እየተራመደ አባይን ተሻግሮ ጎጃም ቡሪ ከተማ ሲሰፍር የማስተናገድ ሃላፊነት የነበረባቸው የአማራ ክልል ባለስልጣናት ዞር ብለው አለማያት ብቻ ሳይሆን ግብርሰናይ ድርጅቶች የሚሰጡት እርዳታ ፈጥኖ እንዳይደርስ ቢሮክራሴያዌ መሰናክል በመፍጠር በርካታ መዳን የሚችሉ ቁስለኞች እንዲሞቱ አድርገዋል።
በእነዚህና የመሳሰሉ የረቀቁ የዘር ማጥፋት ዘዴዎች ያለቀውን አማራ በተመለከተ ከዛሪ አምስት አመት ገደማ በፊት በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ሪፖርት 2.4 ሚሊዮን የአማራ ህዝብ እንደተወገደ ለፓርላማው በኩራት ተገልጿል። በተዘዋዋሪ የአማራን ዘር የማጥፋት ዘመቻችን በእቅዱ መሰረት ግቡን እየመታ ነው የሚል ሪፖርት እንደሆነ ነው ለእኔ የሚሰማኝ። እውነቱ ግን በወያኔ የተገደለውና
የተሰደደው፣ በእየ እስር ቤቱ የታጎረው ቢደመር 2.4 ብቻ ሳይሆን 5 ሚሊዩን ይደርሳል። ወንዱ የዘር ብሉቱ በመኮላሽቱ፣ ሴቷ አምካኝ ክትባት መርፌ በመወጋቷ የመከነው 10 ሚሊዮን በድምሩ በዚህ 26 አመት ውስጥ 15 ሚሊዮን አማራ አልቋል ማለት ይቻላል። አማራው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ባይከፈትበት ኖሮ በአሁኑ ወቅት ከ35 እስከ40 ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። በአኳያው በደርግ መንግስት ኤርትራን ጨምሮ የትግራይ ህዝብ ብዛት 5 ሚሊዮን እንኳን አይሞላም ነበር። ዛሪ ግን የትግራይ ህዝብ ብዛት ብቻውን 4,316,988 ደርሷል። የአማራው ህዝብ በወያኔም ሆነ በሌላ ቋንቋ ተናጋሪ ወገኑ እንዲህ እስከመጨረሻው ዳር ድረስ ሊገፋ የቻለበት ምክናያት ምንድን ነው? እንደዚህ በእየቦታው የሚሳደደው፣ የሚገደለው፣ የሚዘረፈው፣ የሚገፈፈው፣ የሚዋረደው ለምንድን ነው? ምን ስለአጠፋ ነው? አስቀድሞ የተሰራ በደል ካለስ? ያሁኑ ትውልድ የቅድመ አያቱን እዳ መክፈል አለበት ወይ? ደግሞስ የትኛው መሪ ነበር አማራና ዛሪ አማራ እዳ ከፋይ የሚሆነው። ፕሮፌስር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ በሚል እርዕስ ባሳተሙት መጽሃፋቸው። አማራው በወታደርነት ለእናት አገሩ አጥንቱን ከመከስከስ፣ ደሙን ከማፍሰሥ በቀር ገዥ ሆኖ እንደማያውቅ ሲያስረግጡ እንዲህ ብለዋል።
አማራው ከሰለሞናዊው ስርወ.መንግስት ጀምሮ ዋናው የስልጣን ባለቤት እንደነበር ተቆጥሮ ከሲቪልም ሆነ ከወታደራዊ ስልጣን ተገልሎ 40 አመት ሙሉ ለዘር ጥቃት ሲጋለጥ፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰቃይና ሲገደል ኖሯል። እውነቱ ግን አማራው ኢትዮጵያን እንደ ስርወ.መንግስት አልገዛም እንዲያውም ባለፉት 700 አመታት ከአማራው ይልቅ ኦሮሞው የስልጣን ባለቤት ነበር። ወዘተ እያሉ አማራው የሚወነጀልበትን አግባብ የሞግታሉ። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ የአማራው ባልበላው ሲወገዝ፣ ባልስራው ሲኮነን፣ ከየአቅጣጫው ይህ ሁሉ ማት ሲወርድበት ለምንድን ነው ዝም ብሎ የተቀመጠው? በእውነት ወያኔ እንደሚለው ፈሪና ሽንታም ስለሆነ ነው? በእውነት አማራ እራሱን መከላከልና ቃታመከፈት፣ ምላጭ መሳብና አልሞ መተኮስ የማይቸል ደካማ ፍጡር ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ዘወትር እንደ ስራት አልባ የጉንዳን ሰራዊት በአእምሮዬ እንደተተራመሱ መልስ ሳያገኙ ቀንን ቀን፣ እየተካው የማያቋርጠው የወራት ጎርፍ እያጋፈለ አልፎ ጊዜ በነበር ጢሻውስጥ በመስረግ ላይ ነው።
እዚህ ላይ ከሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ ግጥም አንድ ስንኝ ልዋስ አትንኩኝ ባይ ነበር እስከ ትናንትና እረ እግዚወ በሉ ወዴት ሄደ ጀግና እንዳሉት እኔን እንደሚገባኝና በታሪክ እንደማውቀውም አማራው ኢትዮጵያዊ። ትናንት ከእራሱ አልፎ ሀገር ሲወረር ድንበር ሲደፈር ቀድሞ ደርሶ ከአእምሮ፣ ከጉልበት፣ ከጊዜና ከገንዘብ ባሻገር የአካልና የህይወት መሷእትነት ሲከፍል የኖረ ነበር። ባለፉት 42 አመታት ግን ቀኝህን ሲመታህ ግራህን አቅርብለት እንደሚለው ስብከተ ሃይማኖት አይነት አቋም በማራመዱ ተፈርቶ ሲከበርባት በኖረባት አገሩ ተንቆ ከመጠላትና እራሱን መከላከል ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሷል። ለምን? ካልን ይህነን ጥያቄ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሊመልሰው የሚገባ ነው ብዬ አስባለሁ። ጥንት አባቶቻችን አነበሶች ነበሩ እኛስ ድመት ሆነ ምንድን ነው ነገሩ እንደተባለው ከእያቅጣጫው እንደዚህ ሲገፋና ይህ ሁሉ የግፍ አዝመራ ሲወቃበት ዝም ብሎ እንዲቀበል ያደረገውን ነገር አንጥሮ በማወቅ ለምን ማለትን መጀመርና ተደራጅቶ ዘሩን ጭርሶ ከመጥፋት መከላከል በአማራነቱ የሚያምን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ተገዶ የሚገባበት ሃቅ ይመስለኛል።
የከፋው ሲያለቅስ ደስ ያለው ሲዘፍን ያለው ሞልቶት ሲያፈስ የሌለው ሲለምን እንዳሉት ከቡር ዶ/ር አዲስ ዓለማየሁ ወያኔዎች ሲዘፍኑ ሞለቷቸው የውጭ ሃገር ባንክን በገንዘብ ሲያጨናንቁ አማራው ግን 26 አመት ሙሉ በርሀብ፣ በእርዛት፣ በሰው ሰራሽ በሽታ፣ በዱላ፣ በጎራዴ፣ በሳንጃ፣ በጥይት በገደል፣ በእሳት ወ.ዘ.ተ እንደቅጠል እረግፏል። የተረፈውም ነገ ምን ይደርስብኝ ይሆን በማለት ስጋው በስጋት አልቆ።
ያለምንም በህይወት የመቆየት ዋስትና ቀጣይ መጻቱን በመጠባበቅ ላይ ነው። ዛሪ ዘርቶ መቃሚያ፣ የሚሆነውን መሬቱን ተነጥቆ፣ ወልዶ መሳሚያው፣ ዘሩ መክኖ፣ ፊትም መኖሪያ በኋላም መቀበሪያ ሃገር ተነፍጎና እስከመጨረሻው ተገፍቶ በገዛ ሀገሩ ላይ ስደተኛ ሆኖ ነው ያለው አማራው። እንግዴህ ከዚህ የከፋ ምን እስኪመጣ እንዲጠብቅ ይሆን አማራው በዘሩ መደራጀት የለበተም የሚባለው።???? ነገሩ በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት አያምም ነው። አማራው እኮ የሚደራጀው የፖለቲካ ስልጣን መቆናጠጥ  እፈልጋለሁ፣ የዲሞክራሴ መብት አጥቻለሁ፣ ወይንም እገነጠላለሁ ብሎ አይደለም። እነዚህ በአሁኑ ወቅት ለአማራው ኢትዮጵያዊ ቅንጦቶች ናቸው። የአማራው ትግል የህልውና ትግል ነው፣ የአማራው ትግል ዘርን ጨርሶ ከመጥፋት የመከላከል ትግል ነው፣ የአማራው ትግል በህይወት የመኖርና ያለመኖር ትግል ነው።
ይሁዲዎች ልክ እንደ አማራው ህዝብ በሁሉም ሲገፉ፡ እራሽያና ኢትዮጵያ ከለላ ሰጥተዋቸው ነበር። አማራውን ግን በወደቀ እንጨት ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ። ቤተክርስቲያን ወይንም መስጅድ እንደገባች ውሻ የሁሉም ክንድ መሞከሪያና አፍ መፍቻ ነው የሆነው፡፡ ይሁዲዎች ዘራቸው ሳይጠፋ ለዛሪው ደረጃ የደረሱት በዝምታ ሳይሆን እራሳቸውን በመከላከላቸው ነው። አማራውስ ዘሩ እንደ ዳይኖሰር ከምድረ ገጽ ጨርሶ ሳይጠፋ ተደራጅቶ መታገል የለበትም ወይ????? ሃገሩን አልከዳ ወገን አልበደለ፣ ምነ እንዲህ ተገፋ ኢትዮጵያን ባለ። እንዲህ ተነገረ በድፍረት ተወራ፣ ሽንታም ነህ ተባለ ዝም ሲል አማራ። አዎ! ሽንታም ነበር እጅግ ዘረ ብዙ፣ አገር አስከባሪ በደሙ በወዙ። በእርግጥ የአማራው ማህበረሰብ ማንነቱ ኢትዮጵያዊነቱ ነው። የዘር፣ የሃይማኖት የቋንቋ ልዩነትንም አያውቅም።
አማራውና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ደምና ስጋ ናቸው። አንዱ ካለ አንዱ የማይኖሩ። ወያኔ በድርጊት ፕሮግራም ነድፎ እየሰራበት ያለውም ትልቁ ስራው ኢትዮጵያን ለማጥፋት በመጅመሪያ አማራንና የኦርቶዶክስ እምነትን ማጥፋትን ነው። ከላይ እንዳልሁት እነመለስ፣ ሳሞራ፣ ሰብሀትና ተፈራም ሲነግሩን የኖሩትና ከመለስ እልፈት በኋላም ቀሪዎቹ እያቀነቀኑት ያሉት ይኸንኑ ሃቅ ነው። አውቃለሁ መራር ነው መራብ መጠማት፣ ቁስሉ አይጸናም እንጅ እንደመጠቃት። አይደል ያለው አበባው በክራሩ። መናቅና መጥቃት አጥንት ድረስ ሰርስቶ በመግባት ያማል፣ ይጠዘጥዛል። ደግነቱ ፈዋሹ መዳህኒት ያለው በታማሚው እጅ መሆኑ ነው። እሱም አሜን ብሎ አለመቀበልና እንቢ ማለት።
አሁን በአማራው ነገድ እጅ ላይ ያለው አማራጭ 2 ብቻ ነው። እሱም 1ኛው ወያኔ የጀመረውን የአማራውን ዘር በማጥፋት እቅዱን ይፈጽም ዘንድ ከፊሉ በምን ቸገርኝ ገመድ ታብቶ እጁን አጣጥፎ መቀመጥ። ከፊሉ ደግሞ እንደስራወር ግንበኛ በአምልካክት ተለያይቶ በሃሳብ ተራርቆ በመቆም ዘርም፣ ሃይማኖትም፣ ሃገርም ሲጠፉ መመልከት ሲሆን። 2ኛው ደግሞ የሌላውን አማራ ለምን ይደራጃል ጫጫታ ጆሮ ሳይሰጥ። የጎንዮሽም ሳይራገጥ። ጥቃቅን ልዩነቶችን ወደጎን በመተው መነሻውን ነገዱና ዘሩን ከጨርሶ መጥፋት መከላከል። መድረሻው የኢትዮጵያ አንድነትን አድርጎ በመደራጀት ፈርጣማ ክንድ ፍጥሮ ዘርንም፣ ሃይማኖትንም ኢትዮጵያንም ከጥፋት መታደግ የሚሉት ናቸው። አዎ!!! አማራው እስካሁን አርቆ በማሰቡ፣ በመታገሱ፣ በመለሳለሱ በሁሉም ወገኑ በሁሉም አቅጣጫ እስከመጨረሻው ጠርዝ ድረስ ተገፋ። ከወገኑ ተለይቶ እንደበግ ታረደ፣ ስደት፣ ውርደት፣ ሞት ተፈረደበት። ሽንታም ነህም ተባለ አጥንት የሚሰብር ስድብና ሞራልን የሚገድል ውርደት ደረሰበት፡ በአገሩ ላይ ስደተኛ ሆነ። በየሄደበት ተናቀ ተደቀደቀም። አይበቃም ወይ፡????
ኢሜል matebemelese@yahoo.com

ከዲሲ ግብረ-ኃይል የተሰጠ ማሳሰቢያ: “አሁንም የወያኔ ባለስልጣናትን ባረፉበትም ሆነ በረገጡበት ቦታ እየተከታተልን ማጋለጣችንን እንቀጥላለን”

ከዲሲ ግብረ-ኃይል የተሰጠ ማሳሰቢያ
የዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሐይል በሰሜን አሜሪካ በወያኔ አጀንዳ ላይ ተጽዕኖውን አጠናክሮ ይቀጥላል እንጂ በወያኔ የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳ ቅንጣት ብዥታ ውስጥ እንደማይገባ ለኢትዮጵያውያን ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል።አሁንም የህወኅት ባለስልጣኖችም ሆኑ ተላላኪዎቻቸው ባረፉበትም ሆነ በረገጡበት ቦታ የዲሲ ግብረሐይል እግር በግር ተከታትሎ እያከናወኑ ያሉትን ወንጀል ለዓለም ህዝብ ለማጋለጥ በትጋት ስራውን እንደሚፈጽም ቡድኑንም ብዛት ባላቸውና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በማጠናከር ላይ እንደሚገኝ ለነጻነት ናፋቂው ህዝባችን ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።
ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ “ላሜ ቦራ” ብለው እንደሚጠሩት ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ያም ማለት በፈለጋቸው ጊዜ የሚያልቡት “ጥገት” ማለት ነው ፤ይህ ደግሞ የዲሲ ግብረሐይል በአሜሪካን አገር እስከተንቀሳቀሰ ድረስ ፈጽሞ የሚታሰብ እንደማይሆን ከወዲሁ ግልጽ ማድረግ እንፈልጋለን።ድል ለነጻነት ሃይሎች።
ነጻነት ለተጠማው ህዝባችን።
በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን የጋራ ግብረሐይል።

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 16 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያ በአገዛዙ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን ችግር ከሕግ አንጻር ለመተንተን ያስቸግራል ዝም ብሎ ሕገ ወጥ ነው ማለት ብቻ ያለውን የሰብኣዊ መብት ጥሰት የስርኣቱን በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን ግፍ አይገልጽም ሁኔታው ግራ የሚአጋባ ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ነው …በውጭ ያለው ወገን የሚያደርገው እንቅስቃሴ በአገር ውስጥ ባለው ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ለውጥ የምንፈልግ ከሆነ በውጭ ያለነውም ልዩነትን አቻችሎ ለውጡን የሚያግዝ እርምጃ ካልወሰድን በተዘዋዋሪ የእና ድክመት የስርኣቱ ጥንካሬ እየሆነ የሚቀጥልበት ሁኔታ ይፈጠራል ባቻ ሳይሆን…> የሕግ ባለሙያና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ በለንደን ኪል ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ክፍል አንድ)
<…በአገር ቤት የታሰሩት መስዋዕትነቱን ለመቀበል ወስነው ሲታገሉ እና ደግሞ ችግር ላይ አሉትን እስረኞችና ቤተሰቦቻቸውን በኣልን አስታከን እንድናስብ ነው ጥሪ ያደረግነው። ይሄ በዚህ ብቻ አያበቃም ሌሎችንም ለመደገፍ መነሳት አለብን…> እናት እናትዬ ከዳላስ  ለእስረኞች በጎ ፈንድ ለጀመሩት ገንዘብ የማሰባሰብ ጥረት ከሰጠችን ማብራሪያ
<…ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት እየተደበደቡ ቶርች እየተደረጉ እነሱና ቤተሰቦቻቸው ስለተሰቃዩ ቶርች ያደርጋቸው ስርኣት ምስክር ወረቀት እየሰጣቸው ነው።ቶርች አድርጎ ምስክር ወረቀት የሚሰጥ ነው። በአገር ቤት ይሄን ጭካኔ ተቋቁመው እየታገሉ ነው ። እኛ እዚህ በአሜሪካና በአውሮፓ ያለን ኢትዮጵያውያን በዚህ ወቅት እንኳን ተገቢውን ድጋፍ ልናደርግ እስረኞችን ልናስባቸው ይገባል የእኛ ጥረት 20 ዶላር ለ አራት መቶ  በሚል ስምንት ሺህ ለመሰብሰብ ነው ይሄ ጥረት በሌሎችም መቀጠል ስርኣቱ ድምጻቸውን ለሚያፍናቸው መደገፍ አለብን…> ናትናኤል አስመላሽ ከኦክላሆማ ለእነ ዳንኤል ሺበሺ በጎ ፈንድ ዕርዳታ ለማሰባሰብ ለጀመሩት ጥረት

የማርሽ ቀያሪው ፥ለበርካታ አትሌቶች መንገድ ጠራጊው እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የጀግናው አትሌት ሻምበል ምሩጽ ይፍጠር እሳዛኝ እና አስገራሚ ገድሎች(ዝክረ ምሩጽ ይፍጠር)
ኮማንድ ፖስቱና ግፉን እንዳይናገሩ ያሰራቸው ንጹሃን ጉዳይ ሲዳሰስ (ልዩ ጥንቅር)
ከጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ጋር ያደረግነው ቃለ መተይቅ ተከታይ ክፍል(ያድምጡት)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የአማራ ገበሬዎች በሕወሓት አገዛዝ የተከፈተባቸውን የጦርነት ጥቃት እየመከቱ ድል እየተቀዳጁ ነው
ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ በማንኛውም ሰዓት አፍኖ ለመወሰድ ከሌሎች እስረኞች ተነጥሏል
የእንግሊዝ መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ያሳየው ችልተኝነት ቤተስቦቻቸውን አስቆጣ
“ያለ ወላጅ አባት የገና በዓልን ለሶስተኛ ጊዜ ማክበር በጣም ይስማል”የታዳጊ ልጃቸው ምናቤ አንዳርጋቸው ብሶት
አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ግብጽ ተቃዋሚዎችን አደራጅታ እያስጠቃችን ነው በማለት ካይሮን ዳግም ወነጀሉ
“እኛ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አንገባም”የግብጽ የው/ጉ/ሚ/ር መግለጫ
በቨርጂኒያ የሞቱት ሁለት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አገዳደል ግንኙነት እንደሚኖረው ፖሊስ አስታወቀ
ድርጊቱን ፈጸመውን ለማወቅ ምርመራው ቀጥሏል
የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህሩ ስዩም ተሾመ  እና ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው ከተፈቱ በሁዋላ ስለ እስሩ በመጠኑ ገለጹ
ኤርትራዊው ሚሊየነር በተደራጁ የኡጋንዳ መኮንኖች ታፍነው ተገደሉ
የሕወሃት/ኢሕአዲግ መንግስት ቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ ላይ ያባረራቸው የደ/ሱዳኑ ም/ል ፕ/ት ዶ/ር ሪክ ማቻር ደ/አፍሪካ ውስጥ የቁም እስረኛ ሆኑ ተባለ
“ማቻር ስልካቸው ይበረበራል፥ወደ መጸዳጃ ቤት ሲሄዱ ይነጠቃሉ”ምንጮች
ሌሎችም 
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠርከምሽቱ 630 ሰዓትእስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ01405770140 በስልክ ማዳመጥይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻእንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

የትግል አቅጣጫ አመላካች መግለጫ – ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

ንገተኛ ጎርፍ አምጥቷቸው የጀግንነት ከበሮ ሲደልቁ የቆዩት ወያኔዎች እራሳቸው ተደልቀው የታሪክ ትቢያ የመሆናቸው ጊዜ  ብዙ ያዘግማል የሚል ግምት የለም። እነዚህ ጎጠኞች የዘሩት የጎጥ ዘር እራሱ ሊጠራርጋቸው አፉን ከፍቷል። ወትሮውንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦች ባሉበት አገር እንኳን እንደወያኔ ያለው የለየለት ዘረኛ ጉጅሌ ይቅርና አናሳዎች ፤ስልጣን ላይ ሲወጡ እምነት በማጣት ሌሊት ተቀን ሲባንኑ ፣ሲገድሉ ፣ ንጹሃንን ወደ ወህኒ ማጋዝ ስራቸው እንደሆነ ይታወቃል።
በቅርብ የተቀጣጠለው ጠንካራ የሕዝብ አመጽ ወያኔዎችን እንደልብ እንዳይቦርቁ ገትቷቸዋል። ይሁን እንጂ ወጣቶች በሰሜኑም ሆነ በምዕራቡ ኢትዮጵያ ያሳዩት የዐማራውና የኦሮሞው የደምና የትስስር አንድነት መፈክር የአናሳዎችን የቁም ቅዠት እጅግ አባብሶታል። አመጹ ወያኔን እየከበበውና እየዋጠው ቢሆንም ባንድ ሌሊት ይተናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ይህ የሁለቱ ብሄረሰቦች የተባበረ እንቅስቃሴ ቀድሞውንም ለኢትዮጵያ መሰረት መሆኑ ግልጽ ነው። አሁንም ለጸናች ኢትዮጵያ መቀጠል ወሳኝነት አለው ።
ይሁን እንጂ በወጣቱ መካከል የሚታየው ይህ ተስፈኝነትና ትግል በሁለቱ ብሄረሰቦች ምሁራንና ፓለቲከኞች ስልታዊ ሕብረት ሲታገዝ አይታይም። የተጠናከረና የተቀናጀ ተግባራዊ የትግል ስልት ባጭር ጊዜ ውስጥ ምድር ላይ ሊታይ በተገባውም ነበር። የተያዘው ድል ቀላል ባይሆንም ቀጣዩ ትግል ነው የመጨረሻውን ምዕራፍ ለመደምደም የሚያበቃው። የጦርነት አበቃ ድል እወጃ ቅርብ አለመሆኑን መረዳት መዘናጋትን ያስቀራል። ባንዳንድ ወገኖች የሚታይ የድል ባለቤትነት ይገባኛል ሽሚያም  ወቅቱ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ትግሉን አያግዝም ። በዚያውም ላይ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማም እንዳይሆን ያሰጋል።
ወያኔዎችና እነሱ የቀፈቀፏቸው ሌሎች መንደረተኛ ጽንፈኞች ዐማራውን ቃል መግለጽ በማይችለው መንገድ አሰቃይተው ፈጅተውታል። የችግሩ ክፋት የዐማሮችን ትዕግስት ገደብ ጥሶት፤ ቢያረፍድም ባነናል።ከዚህ ወዲህ ወደ ኋላ ላንመለስ መነሳታችን ብቻ ሳይሆን አቅላቻው የከዳቸውን ነፍሰ ገዳዮች የወይራ ዝንጣፊ ይዘን እንደማንጠብቃቸው ጠንቅቀው ሊረዱ ይገባል።
በሌላ በኩልም በዘር መደራጀት ወያኔ በቀደደው ቦይ መፍሰስ ነው የሚሉ ወግ አራቂዎች አሁንም አደብ አልገዙም። የኢሃዴግ የዘር ፓለቲካ እና የዐማራው መደራጀት ጭራሽ አይገናኙም ። ዱባና ቅል ለየቅል አሉ። እነዚህ የቅቤ አንጓቾች የማይመልሱት፣  መሰረታዊ ጥያቄ ለሚሞት፣ለሚሰደድ፣ለሚፈናቀለው፣በሃገሪቱ ዳርቻ ለሚዋከበውዐማራ ማን ይቁምለትእጣ ፋንታውስ ምን ይሁን ? የሚለው ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነየሁላችንም የሆነችውን ኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ማስጠበቅ ለዐማራው ብቻ የሚሰጥሃላፊነት አድርጎ የማሰቡ ነገር ልክ ካለመሆኑም ባሻገር ለኢትዮጵያብሄርተኝነት መለምለም ሲባል ዐማራው ሲሞት ዝም ብሎ መታየት አለበት ለማለት የሚቃጣው ነው፡፡
የዐማራውን ሰቆቃ ለዘነጉት ወይንም አውቀው ለሚያድበሰብሱት በጥቂቱ እናስታውሳቸው። በዘመን የተለያዩ ፤በስፍራ የተራራቁ አያሌ ውጣ ውረዶች ዐማራውን ገጥሞታል። ይሁን እንጂ አሁን የገጠመው በአይነቱም ሆነ በይዘቱ የታሪክ አቻ የለውም። ሕይወትን ማቆየት ሕይወትን የሚያስከፍል ግጥምጥም የሆነበት ቀን የከዳው ሕዝብ ሆኗል።  ማንነታቸውን ሳይመርጡ አፍቅረውና ተፈቅረው በኖሩበት አካባቢ በጠራራ ፀሃይ ሕይወታቸውን እንደዋዛ አጥተዋል። ዐማራው መከራን በፀጋ መቀበል እጣ ፋንታው ይመስል ስጋው በእዋፋትና አራዊት ከርስ ውስጥ አዳሪ እንዲሆኑ ተደርጓል።የጃን አሞራው ጀግና ልጅ ለጥምብ አንሳ ግብር እንዲውል አድርገውታል። የባህልን አጥር ጥሶ ለዘመናት ሁሉም ቤቴ ብሎ የኖረው ዐማራ እንደጸጉረ ልውጥ ተቆጥሮ ባይተዋር ሆነ።የሰርክ ማንነቱን እንዲጥል ዐይኑን ባይኑ እንዳያይ አመከኑት። በዘረኞች እኩይ ቅስቀሳ የተነሳ በያካባቢው  ሕዝቡ በ«እንኳን ደህና መጣህ»ልቡን ከፍቶ ፤ፊቱን ፈትቶ፤እጁን ዘርግቶ መቀበሉ ቀርቶ የእንሰሳ እንኳን ማዕረግ ነፈገው። ይህ መከራ የተጫነው ሕዝብ ለዘመናት ለሁሉም እንዳልሞተ ሁሉም ዘመቱበት። የእርጥብ ፓለቲከኞች መሳለቂያ ሆነ። ብላቴና እህቶቻችን ወደ የአረቡ አለም እየተጋዙ የዝሙታን ርኳቤ ማስታገሻ ሆኑ።
 እነዚህ ጉብል ወጣቶች በተናጥልና በስውር የሚገጥማቸውን መሪር መከራ መጋፈጥ የአዘቦት የኑሮ እጣፋንታ ሆናቸው። ልዕለ ተፈጥራዊና-ልእለ ሰብአዊ መብታቸው ተገሰሰ። የዛሬዋ የወያኔ ኢትዮጵያ ለዐማራው ጓጉቶና ጎምዥቶ ዳሩ ግን ፈርቶና ሸሽቶ የሚኖርባት እንግዳ ምድር ሆነችበት።
ይህን ሁሉ ወደጎን በመተው ለአገራችንና ለሕዝባችን ቅድሚያ በመስጠት በብሔራዊ አጀንዳ ዙሪያ ለመስራት ፈቃደኝነታችንን አሳይተናል። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ቀደም ሲል የትግል የጋራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በኢትዮጵያዊነታቸው ለሚያምኑ ወገኖች ሁሉ የትብብር ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። የተናጥልና የፊና ትግል ውጤቱ የወያኔን መንግስት ዕድሜ ርዝማን እገዛ ነው። ኦሮሞና ዐማራ ትግሉን ማጦዝ ይዟል። ሁሉም በታየውና በተቻለው መንገድ ትንንቁን ቀጥሏል። አሁን የምንዘናጋበትና የየራስ ሚናችንን እና ያስከተለውን ውጤት የምናውጅበት ወቅት ሳይሆን በጋራ የወያኔን ሃይል ማዋከብ የምንቀጥልበት ወቅት ነው። ዐማራ ዘንድ ጋብ አለ ሲባል ኦሮሞ ውስጥ ሲጦፍ ኦሮሞ ዘንድ ጋብ አለ ሲባል ዐማራ ትግሉን ሲያጋግለው የዘረኛውን መንግስት ጉልበት እየተብረከረከና ብሎም መንኮታኮት ይይዛል። ዳሩ ግን ሁኔታውን ሁነኛ በሆነ መንገድ ያልገመገሙ አንዳንድ ጽንፈኞች ይህንን የተጀመረ የጋራ ትግል አዳክመውና ለግላቸው ሚና የተጋነነ ድርሻ ገምድለው በመስጠት ሰልፉን ያበላሹ እለት የባሰ የትግል አቀበት የመግጠሙ ጉዳይ አያጠራጥርም። አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ዐማራው ሞቷል። ተባሯል ተግዟል። ይህ ግን ይቆማል። ዐማራው ከዚህ በኋላ ዝምብሎ መሞት እንደለሌለ እቅጩን ተናግሯል። ስለሆነም ሁኔታው ያታለላቸው አንዳንድ የዋህ ወገኖች ሌላ ቅዠት ውስጥ እንዳይገቡ በጽኑ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።
ይህ ፳፭ ዓመት ለማንም ህሊና ላለው ሁሉ የሚያስተምረው ነገር አለ። ይሀውም ማንም ብቻውን ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በኋላ ስልጣን መፈናጠጥ እንደማይችል። «ጦርነት እንሰራለን» እያሉ ሲመጻደቁ የነበሩት የትግራይ ሽፍቶች ሳይቀሩ በወጣቶች ድንጋይ እየተፍረከረኩና መላው እየጠፋቸው ነው። ዱሮውንስ የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም ተብሎስ የለ።
በየጊዜው የሚነሱ የፓለቲካ አለመረጋጋቶችንና ግብግቦችን  እያጀቡ የወጀብ አጃቢ ከመሆን በተቀናጀ መንገድ የፓለቲካውን ወጀብ ፈጣሪ ሃይል መሆንን የፓለቲካው ጉዞ የሚጠይቀው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ደግሞስ እስከመቼ ነው ንቁና ብቁ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለሞት፤ለእስራት፤ ለስደት እየገበርን የምንቀጥለው? እስከመቼ ነው ወያኔ አንድ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሌላ ጊዜ ኮማንድ ፓስት እያቋቋመ ዐማሮችንና ኦሮሞዎችን የሚጨፈጭፈው? ወያኔ የምርጫ ኮሮጆ በገለበጠበት የ1997 ምርጫ ማግስት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ገብረናል።ብዙ አካለስንኩላንን አፍርተናል። ወደ አረቡ አለም ተሰደው የበረሃ ሲሳይ ሆነዋል። አሁንም እየሆነ ያለው ይሀው ነው።
ያለፈው ታሪክ ለትምህርታችን ያሁኑ ለጋራ ሕይወታችን ቀጣዩ ለመጪው ትውልድ መሆኑን ተረድተን በብልሃትና በጋራ አገራችንን ልንመራ ነባራዊው ሁኔታ ግድ ይለናል። ይህ ካልሆነ መሪነትን ለራስና ጽንፈኝነትን እንደግብና መታገያ ስልት አድርገን ከያዝን ነገም በተራችን አመጽ ጊዜውን ጠብቆ የምናገፈጠው ጭራቅ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።ላንዴና ለመጨረሻ የዲሞክራሲን ስርአት ተክለን ሕዝባችንን ቀጣይነት ያለው እፎይታ እናጎናጽፈው።
የድርጅቶች የነጠላ ፓለቲካ ጉዞ የሰለቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በ 1997 ምርጫ ወቅት «ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ» ማለቱን እናስታውሳለን። አሁንም ያልተመለሰው ጥያቄ ይሀው የተባበሩ ጉዳይ ነው። በውስጥ ያሉት የፓለቲካ ድርጅቶች በወያኔ ደህንነትና ፍርፋሬ ተቋዳሾች ለትብብር ስንክሳር ቢበዛባቸው አይገርምም። ከውጭ ያለነውን ወደ ሃላ የጎተተን ምን ይሆን? በሰለጠነው አለም እየኖርን በጠረፔዛ ዙሪያ ሆነን መነጋገርን ማን? ምን? ከለከለን። ለመሆኑ የባቢሎን ግንብ የሆነብን ቅጥር ምን ይሆን?
ለትብብርና አገርን ለማዳን በጋራ ለመስራት የተዘጋጀነውን ያህል ዐማራውን ካፈናቀሉ ፤ዘመን ሊቀየር እንደሚችል ዘንግተው ከወያኔዎች ጋር ወግነው ዐማራውን ካጠፉት ጋር መተባበር ሳይሆን ሁኔታዎች በሚፈቅዱ ወቅት ለፍርድ የምናቀርባቸው መሆኑ መታወቅ ያለበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ ከውዲሁ ያስገንዝባል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

“ከወያኔ ጋር ወግነው አማራውን የገደሉትን ለፍርድ እናቀርባለን” – የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት መግለጫ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ታኅሳስ ፲፯ ቀን ፪ሺህ፱ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፴
ከዚህ ወዴት? እንዴት?
ድንገተኛ ጎርፍ አምጥቷቸው የጀግንነት ከበሮ ሲደልቁ የቆዩት ወያኔዎች እራሳቸው ተደልቀው የታሪክ ትቢያ የመሆናቸው ጊዜ ብዙ ያዘግማል የሚል ግምት የለም። እነዚህ ጎጠኞች የዘሩት የጎጥ ዘር እራሱ ሊጠራርጋቸው አፉን ከፍቷል። ወትሮውንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ብሄረሰቦች ባሉበት አገር እንኳን እንደወያኔ ያለው የለየለት ዘረኛ ጉጅሌ ይቅርና አናሳዎች ፤ስልጣን ላይ ሲወጡ እምነት በማጣት ሌሊት ተቀን ሲባንኑ ፣ሲገድሉ ፣ ንጹሃንን ወደ ወህኒ ማጋዝ ስራቸው እንደሆነ ይታወቃል።
በቅርብ የተቀጣጠለው ጠንካራ የሕዝብ አመጽ ወያኔዎችን እንደልብ እንዳይቦርቁ ገትቷቸዋል። ይሁን እንጂ ወጣቶች በሰሜኑም ሆነ በምዕራቡ ኢትዮጵያ ያሳዩት የዐማራውና የኦሮሞው የደምና የትስስር አንድነት መፈክር የአናሳዎችን የቁም ቅዠት እጅግ አባብሶታል። አመጹ ወያኔን እየከበበውና እየዋጠው ቢሆንም ባንድ ሌሊት ይተናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ይህ የሁለቱ ብሄረሰቦች የተባበረ እንቅስቃሴ ቀድሞውንም ለኢትዮጵያ መሰረት መሆኑ ግልጽ ነው። አሁንም ለጸናች ኢትዮጵያ መቀጠል ወሳኝነት አለው ።
ይሁን እንጂ በወጣቱ መካከል የሚታየው ይህ ተስፈኝነትና ትግል በሁለቱ ብሄረሰቦች ምሁራንና ፓለቲከኞች ስልታዊ ሕብረት ሲታገዝ አይታይም። የተጠናከረና የተቀናጀ ተግባራዊ የትግል ስልት ባጭር ጊዜ ውስጥ ምድር ላይ ሊታይ በተገባውም ነበር። የተያዘው ድል ቀላል ባይሆንም ቀጣዩ ትግል ነው የመጨረሻውን ምዕራፍ ለመደምደም የሚያበቃው። የጦርነት አበቃ ድል እወጃ ቅርብ አለመሆኑን መረዳት መዘናጋትን ያስቀራል። ባንዳንድ ወገኖች የሚታይ የድል ባለቤትነት ይገባኛል ሽሚያም ወቅቱ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ትግሉን አያግዝም ። በዚያውም ላይ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማም እንዳይሆን ያሰጋል።
ወያኔዎችና እነሱ የቀፈቀፏቸው ሌሎች መንደረተኛ ጽንፈኞች ዐማራውን ቃል መግለጽ በማይችለው መንገድ አሰቃይተው ፈጅተውታል። የችግሩ ክፋት የዐማሮችን ትዕግስት ገደብ ጥሶት፤ ቢያረፍድም ባነናል።ከዚህ ወዲህ ወደ ኋላ ላንመለስ መነሳታችን ብቻ ሳይሆን አቅላቻው የከዳቸውን ነፍሰ ገዳዮች የወይራ ዝንጣፊ ይዘን እንደማንጠብቃቸው ጠንቅቀው ሊረዱ ይገባል።
በሌላ በኩልም በዘር መደራጀት ወያኔ በቀደደው ቦይ መፍሰስ ነው የሚሉ ወግ አራቂዎች አሁንም አደብ አልገዙም። የኢሃዴግ የዘር ፓለቲካ እና የዐማራው መደራጀት ጭራሽ አይገናኙም ። ዱባና ቅል ለየቅል አሉ። እነዚህ የቅቤ አንጓቾች የማይመልሱት፣ መሰረታዊ ጥያቄ ለሚሞት፣ ለሚሰደድ፣ለሚፈናቀለው፣በሃገሪቱ ዳርቻ ለሚዋከበው ዐማራ ማን ይቁምለት? እጣ ፋንታውስ ምን ይሁን ? የሚለው ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ የሁላችንም የሆነችውን ኢትዮጵያ ብሄርተኝነት ማስጠበቅ ለዐማራው ብቻ የሚሰጥ ሃላፊነት አድርጎ የማሰቡ ነገር ልክ ካለመሆኑም ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሄርተኝነት መለምለም ሲባል ዐማራው ሲሞት ዝም ብሎ መታየት አለበት ለማለት የሚቃጣው ነው፡፡
የዐማራውን ሰቆቃ ለዘነጉት ወይንም አውቀው ለሚያድበሰብሱት በጥቂቱ እናስታውሳቸው። በዘመን የተለያዩ ፤በስፍራ የተራራቁ አያሌ ውጣ ውረዶች ዐማራውን ገጥሞታል። ይሁን እንጂ አሁን የገጠመው በአይነቱም ሆነ በይዘቱ የታሪክ አቻ የለውም። ሕይወትን ማቆየት ሕይወትን የሚያስከፍል ግጥምጥም የሆነበት ቀን የከዳው ሕዝብ ሆኗል። ማንነታቸውን ሳይመርጡ አፍቅረውና ተፈቅረው በኖሩበት አካባቢ በጠራራ ፀሃይ ሕይወታቸውን እንደዋዛ አጥተዋል። ዐማራው መከራን በፀጋ መቀበል እጣ ፋንታው ይመስል ስጋው በእዋፋትና አራዊት ከርስ ውስጥ አዳሪ እንዲሆኑ ተደርጓል።የጃን አሞራው ጀግና ልጅ ለጥምብ አንሳ ግብር እንዲውል አድርገውታል። የባህልን አጥር ጥሶ ለዘመናት ሁሉም ቤቴ ብሎ የኖረው ዐማራ እንደጸጉረ ልውጥ ተቆጥሮ ባይተዋር ሆነ።የሰርክ ማንነቱን እንዲጥል ዐይኑን ባይኑ እንዳያይ አመከኑት። በዘረኞች እኩይ ቅስቀሳ የተነሳ በያካባቢው ሕዝቡ በ«እንኳን ደህና መጣህ»ልቡን ከፍቶ ፤ፊቱን ፈትቶ፤እጁን ዘርግቶ መቀበሉ ቀርቶ የእንሰሳ እንኳን ማዕረግ ነፈገው። ይህ መከራ የተጫነው ሕዝብ ለዘመናት ለሁሉም እንዳልሞተ ሁሉም ዘመቱበት። የእርጥብ ፓለቲከኞች መሳለቂያ ሆነ። ብላቴና እህቶቻችን ወደ የአረቡ አለም እየተጋዙ የዝሙታን ርኳቤ ማስታገሻ ሆኑ።
እነዚህ ጉብል ወጣቶች በተናጥልና በስውር የሚገጥማቸውን መሪር መከራ መጋፈጥ የአዘቦት የኑሮ እጣፋንታ ሆናቸው። ልዕለ ተፈጥራዊና-ልእለ ሰብአዊ መብታቸው ተገሰሰ። የዛሬዋ የወያኔ ኢትዮጵያ ለዐማራው ጓጉቶና ጎምዥቶ ዳሩ ግን ፈርቶና ሸሽቶ የሚኖርባት እንግዳ ምድር ሆነችበት።
ይህን ሁሉ ወደጎን በመተው ለአገራችንና ለሕዝባችን ቅድሚያ በመስጠት በብሔራዊ አጀንዳ ዙሪያ ለመስራት ፈቃደኝነታችንን አሳይተናል። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ቀደም ሲል የትግል የጋራ ትብብር አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ በኢትዮጵያዊነታቸው ለሚያምኑ ወገኖች ሁሉ የትብብር ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል። የተናጥልና የፊና ትግል ውጤቱ የወያኔን መንግስት ዕድሜ ርዝማን እገዛ ነው። ኦሮሞና ዐማራ ትግሉን ማጦዝ ይዟል። ሁሉም በታየውና በተቻለው መንገድ ትንንቁን ቀጥሏል። አሁን የምንዘናጋበትና የየራስ ሚናችንን እና ያስከተለውን ውጤት የምናውጅበት ወቅት ሳይሆን በጋራ የወያኔን ሃይል ማዋከብ የምንቀጥልበት ወቅት ነው። ዐማራ ዘንድ ጋብ አለ ሲባል ኦሮሞ ውስጥ ሲጦፍ ኦሮሞ ዘንድ ጋብ አለ ሲባል ዐማራ ትግሉን ሲያጋግለው የዘረኛውን መንግስት ጉልበት እየተብረከረከና ብሎም መንኮታኮት ይይዛል። ዳሩ ግን ሁኔታውን ሁነኛ በሆነ መንገድ ያልገመገሙ አንዳንድ ጽንፈኞች ይህንን የተጀመረ የጋራ ትግል አዳክመውና ለግላቸው ሚና የተጋነነ ድርሻ ገምድለው በመስጠት ሰልፉን ያበላሹ እለት የባሰ የትግል አቀበት የመግጠሙ ጉዳይ አያጠራጥርም። አንድ ግልጽ መሆን ያለበት ዐማራው ሞቷል። ተባሯል ተግዟል። ይህ ግን ይቆማል። ዐማራው ከዚህ በኋላ ዝምብሎ መሞት እንደለሌለ እቅጩን ተናግሯል። ስለሆነም ሁኔታው ያታለላቸው አንዳንድ የዋህ ወገኖች ሌላ ቅዠት ውስጥ እንዳይገቡ በጽኑ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን።
ይህ ፳፭ ዓመት ለማንም ህሊና ላለው ሁሉ የሚያስተምረው ነገር አለ። ይሀውም ማንም ብቻውን ኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ በኋላ ስልጣን መፈናጠጥ እንደማይችል። «ጦርነት እንሰራለን» እያሉ ሲመጻደቁ የነበሩት የትግራይ ሽፍቶች ሳይቀሩ በወጣቶች ድንጋይ እየተፍረከረኩና መላው እየጠፋቸው ነው። ዱሮውንስ የጊዜ እንጂ የሰው ጀግና የለውም ተብሎስ የለ።
በየጊዜው የሚነሱ የፓለቲካ አለመረጋጋቶችንና ግብግቦችን እያጀቡ የወጀብ አጃቢ ከመሆን በተቀናጀ መንገድ የፓለቲካውን ወጀብ ፈጣሪ ሃይል መሆንን የፓለቲካው ጉዞ የሚጠይቀው መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ደግሞስ እስከመቼ ነው ንቁና ብቁ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለሞት፤ለእስራት፤ ለስደት እየገበርን የምንቀጥለው? እስከመቼ ነው ወያኔ አንድ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሌላ ጊዜ ኮማንድ ፓስት እያቋቋመ ዐማሮችንና ኦሮሞዎችን የሚጨፈጭፈው? ወያኔ የምርጫ ኮሮጆ በገለበጠበት የ1997 ምርጫ ማግስት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ገብረናል።ብዙ አካለስንኩላንን አፍርተናል። ወደ አረቡ አለም ተሰደው የበረሃ ሲሳይ ሆነዋል። አሁንም እየሆነ ያለው ይሀው ነው።
ያለፈው ታሪክ ለትምህርታችን ያሁኑ ለጋራ ሕይወታችን ቀጣዩ ለመጪው ትውልድ መሆኑን ተረድተን በብልሃትና በጋራ አገራችንን ልንመራ ነባራዊው ሁኔታ ግድ ይለናል። ይህ ካልሆነ መሪነትን ለራስና ጽንፈኝነትን እንደግብና መታገያ ስልት አድርገን ከያዝን ነገም በተራችን አመጽ ጊዜውን ጠብቆ የምናገፈጠው ጭራቅ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።ላንዴና ለመጨረሻ የዲሞክራሲን ስርአት ተክለን ሕዝባችንን ቀጣይነት ያለው እፎይታ እናጎናጽፈው።
የድርጅቶች የነጠላ ፓለቲካ ጉዞ የሰለቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ በ 1997 ምርጫ ወቅት «ተባበሩ ወይም ተሰባበሩ» ማለቱን እናስታውሳለን። አሁንም ያልተመለሰው ጥያቄ ይሀው የተባበሩ ጉዳይ ነው። በውስጥ ያሉት የፓለቲካ ድርጅቶች በወያኔ ደህንነትና ፍርፋሬ ተቋዳሾች ለትብብር ስንክሳር ቢበዛባቸው አይገርምም። ከውጭ ያለነውን ወደ ሃላ የጎተተን ምን ይሆን? በሰለጠነው አለም እየኖርን በጠረፔዛ ዙሪያ ሆነን መነጋገርን ማን? ምን? ከለከለን። ለመሆኑ የባቢሎን ግንብ የሆነብን ቅጥር ምን ይሆን?
ለትብብርና አገርን ለማዳን በጋራ ለመስራት የተዘጋጀነውን ያህል ዐማራውን ካፈናቀሉ ፤ ዘመን ሊቀየር እንደሚችል ዘንግተው ከወያኔዎች ጋር ወግነው ዐማራውን ካጠፉት ጋር መተባበር ሳይሆን ሁኔታዎች በሚፈቅዱ ወቅት ለፍርድ የምናቀርባቸው መሆኑ መታወቅ ያለበት መሆኑን ሞረሽ ወገኔ ከውዲሁ ያስገንዝባል።
ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ድል ምንጊዜም የሕዝብ ነው!

ግልጽ ደብዳቤ ለጀዋር መሐመድ: እየተከፈተ ያለውን የአንድነት በር ጨርሰህ ክፈተው

በአንድ ወቅት አሜሪካ ሶቬት ህብረትን ለማፈራረስ አፍጋኒስታን ውስጥ የአፍጋን ኃይሎች በሚል ወጣቶችን ከዛው መልምላ በሚሊቴሪና በፖለቲካ አሰለጠነች፡፡ ተጠቀማቸው የፈለገችውንም አደረገች፡፡ እነዚህ ወታደሮች ከጊዜ በኋላ የራሳቸውን ዓላማ ቀርፀው ከአሜሪካ ተለይተው አልቃይዳን ወለዱ፡፡ አልቃይዳም እግረ-መንገዱን የአሜሪካንን ድብቅ ፀረ-ኢስላማዊ ዓላማ ገባው፡፡ ቀጥሎም ሁለቱን የአሜሪካ የአለም ንግድ ማዕከላት ለማጥቃት ደረሰ፡፡ ይህን ተከትሎም አሜሪካ አፍጋኒስታንና ኢራንን ለማፈራረስ ምክንያት አገኘችበት፡፡ አሜሪካ ባደረሰችው ዘግናኝ በደል ብዙ የአሸባሪ ቡድኖች በዓረብ ሀገራት ፈንጥቀው ወጡ፡፡ አይሲስ፣ አይሲል፣ ታክፊሪ፣ አልቃይዳ፣..…ሁሉም ዓላማቸው ኢስላማዊ ግዛትን ለመመስረትና አሜሪካና ምዕራባዊያን በሙስሊሞች ላይ በሰሩት ግፍ፣ ባላቸው ጭፍን ጥላቻና እያደረጉ ባሉት የሥም ማጥፋት የተነሳ ነው፡፡ እነዚህ የአሸባሪ ቡድኖች በምዕራባዊያን ሀገራት ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ወደፊት አብዛኛው ሙስሊሞች ህብረት መሥርተው ፀረ-ምዕራባዊ ሆነው ቀጣይ ስጋት ሊሆኑ እንደሚችሉ የፖለቲካ ተመራማሪዎች ይተነብያሉ፡፡ ከዚህ አልፎም የከረረ የክርስትናና የእስልምና የሀይማኖት ጦርነት ይጠበቃል፡፡ አንዱ አንዱን እየወለደ….የማያበቃ የበቀል ሰንሰለትም ይሆናል፡፡
ሁለተኛ የታሪክ አጋጣሚ ላጫውትህ
በ2006 ግ.ካ. በዴንማርክ አንድ ይላንድስ ፖስተን የሚባል የጋዜጣ ድርጅት በ2014 በፈረንጆች አዲስ ዓመት ዋዜማ 12 የነብዩ መሐመድ ምስሎችን በጋዜጣው አቀረበ፡፡ በምስሎቹ ነብዩ መሣሪያ ታጥቆና አሸባሪ መስሎ የታየበት ነበር፡፡ ሌላው የኖርዌይ የጋዜጣ ድርጅት ለዴንማርኩ ጋዜጣ ድጋፍ በማሳየት ምስሎቹን በራሱ ጋዜጣ አትሞት ነበር፡፡ ይህ ተከትሎም በብዙ ዓረብ ሀገራት የሚገኙ የኖርዌይና የዴንማርክ ኢምባሲዎች ላይ ዓረቦች ጥቃት አደረሱ፡፡ አሁን ላይም ኖርዌይና ዴንማርክ በዓረቦች በጥቁር ዓይን እየታዩ ይገኛል፡፡
ሦሥተኛ የታሪክ አጋጣሚ ላጫውትህ
አንድ አሜሪካዊ ቅዱስ ቁርዓንን በይፋ ማቃጠሉን ተከትሎ በብዙ ዓረብ ሀገራት የሚገኙ የአሜሪካ ኢምባሲዎች ላይ ዓረቦች ጥቃት አደረሱ፡፡ አሜሪካ የመናገር ነፃነት ነው ብላ በህግ ሳትጠይቀው በመቅረቷ አሜሪካ ሙሉ ለሙሉ ፀረ-ኢስላማዊ ተደርጋ በሙስሊሞች መታየች ጀመረች፡፡ በኮሎራዶ ምሽት ክበብ የደረሰውም አደጋ ከዚህ የመነጨ ነው፡፡ ቀጣይ አደጋዎችም ይጠበቃሉ፡፡
ስለሀገራችን
ወደ ሀገራችን እንምጣና ደርግ በነበረው ጭፍን አምባገንነት ሁለተኛውን አምባገነንን ወለደ፡፡ ደርግ በሥልጣኑ ዘመን ለተቃዋሚዎች መፈናፈኛና አብሮ የመስራት ዕድል ቢሰጥ ኖሮ ወያኔ አይወለድም ነበር፡፡ ወያኔ ያጣውን የፖለቲካ ተሣትፎ ወደ ትጥቅ ትግል በመቀየር በጫካ ከከፈለው የመሠዋትነት ጫፍ አምባገነን ለመሆን ተዳረገ፡፡ አሁንም በህልሙ ሥልጣን ላይ እንዳለ የሚሰማው ወያኔ ሥልጣኑን ላለመልቀቅ የግፍ ጫፍ እየፈፀመ ይገኛለል፡፡ የወያኔ ግፍ ማንን ሊወልድ ይሆን???
ለ25 ዓመታት ቅጥቅጡ ወያኔ በሰራው የብሄር ለብሄር ማጥላላት ሥራ ጭፍን ፖለቲከኞች መወለዳቸው አይገርምም፡፡ ታሪክ ታሪክን አጋጣሚ አጋጣሚን ይወልዳል እንደሚባል ይሄ መከሰቱ የሚጠበቅ ነበር፡፡ ኦሮሚያን ብቸኛ የአፍሪካ ሀገርና የእስልምና ግዛት ለማድረግ ቆርጠህ መነሳትህ ከዚህ ውጥን የመነጨ ለመሆኑ መስካሪ አያስፈልገውም፡፡ በግሌ እኔ ክርስቲያንና 50% ኦሮሞና 50% አማራ ነኝ፡፡ ለእኔ ዓይነቱ ዜጋ ምን አዘጋጅተህ ነው እንዲህ ዓይነት ትግል የመረጥከው? ግብዓተ-ሲኦልን??? የኦሮሚያ ህዝብ 36.7% ፐርሰንት ከሌሎች ብሄሮች ጋር በጋብቻ መተሳሰሩ ችላ ብለህ ነው? እነዚህ ከሌሎች ብሄሮች ጋር የተዳቀሉና ዘር ማንዘራችው የተወራረደ የት እንዲገቡ ነው??? ከ50% በላዩ የኦሮሚያ ህዝብ ክርስትናና የባህል አምልኮ ተከታይ ነው፡፡ ለእነዚህስ ቦታ የለህም? ያንተ ኦሮሚያ የትኛው ነውን? Oromic Islamization ልትጠቀም ይሆን? በግሌ እስከዛሬ የተደረገው ትግል ኦሮሚያ ዕውቅና እንድታገኝ በቂ ይመስለኛል፡፡ ዛሬ ላይ ያለኦሮሞዎች የፖለቲካ ተሣትፎ ኢትዮጵያ እንደማትታሰብ በቂ ትግል መደረጉን ነው፡፡ ይሄም በአብሮነት ለመታገል የሚገፋፋ ጊዜ ላይ ስላለን ግትርነትን በመተው ሁላችንም አንድነት የማይታለም ላሉ የማሳፈሪያ አጋጣሚ የምንፈጥርበት ጊዜ ይመስለኛል፡፡
በተጨማሪ ወያኔ የሠራውን ሴራ ሁሉም ተረድቷል በሚባል ወቅት እራስን ማግለል የሚጠቅም አይመስለኝም፡፡ የኦሮሚያ ህዝብ በሚታወቀው የዋህነት ዛሬ ላይ ተነስተህ አብሮነትን እናጠናክር ብትል ህዝቡ ሙሉ ለሙሉ ፍቃደኛና በራሱ እያደረገውም ነው፡፡ ይሄንም እውነታ 50% ብሄሬ ስለሆነ አውቀዋለሁ፡፡ ያለፈ አልፏል ብለን በጋራ መታገል ይበጀናል፡፡ ጠንካራ የፖለቲካ አቅም ስላለህ ለአብሮነት ብትታገል በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉን ያማከለች ህዝባዊ ኢትዮጵያን መመስረት ይቻላል፡፡ እንደ ወንድሜ ስለማይህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን፡፡ ፅናቱንም ይስጥህ፡፡ ትግልህንም ይባርክልህ፡፡