Sunday, October 30, 2016

የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። (ቆንጂት ስጦታው)


የዘረኝነት ወረርሽን ከአመት አመት እየተባባሰ፣ አገሪቱ እየተንሸራተተች ናት። (ቆንጂት ስጦታው)
የዘረኝነት ወረርሽኝ፣ ተስፋ አስቆራጭና አስፈሪ የጨለማ ጉዞ የሚሆነው፤ ነገሩ ያን ያህል ውስብስብ ጉዳይ ስለሆነ አይደለም። የዘኝነትን አባዜ በቀላሉ አሽቀንጥረን ለማስወገድ አልቻልንም አስገራሚ ነገር ነው። ጭራሽ፣ በዝምድና የሚገናኙ መሆን አለመሆናቸው የማይታወቁ ሰዎችን (የአንድ ብሔረሰብ ተወላጆችን) በጅምላ እንፈርጃለን። ይሄም አልበቃም። ጭራሽ፣ ከመቶ ዓመት በፊት፣ … ከአምስት መቶ ዓመት በፊት፣ ከሚሌኒዬም በፊት የነበረ ንጉስና አልጋ ወራሽ፣ ወይም ደጃዝማቾችና ፊታውራሪ፣ አልያም ሰባኪና ፀሃፊ፣ ሽፍታና ዘራፊ… እየጠቀስን፣ አሁን በሕይወት ያሉ ሰዎችን፣ የጥፋትና የበደል ወራሽ እንዲሆኑ በዘር እየፈርጅንና እያቧደንን፣ አገሩን ቀውጢ ስናደርግ ይታያችሁ? እብደቱ፣ በሽታውና ወረርሽኙ የዚህን ያህል ከፍቷል።
 
ኢትዮጵያ በብዙ አይነት የጥፋት ፈተናዎች ውስጥ፣ ህልውናዋን ሙሉ ለሙሉ ሳታጣ ያለፈች አገር ብትሆንም፣ የበርካታ ፓርቲዎችና ፖለቲከኞች ዝንባሌን ስትታዘቡ፣ የበርካታ ምሁራንና ዜጎች አዝማሚያ ስትመለከቱ… ሁሌም ባይሆን አንዳንዴ፣ የዚህች አገር ነገር፣ተስፋ ያስቆርጣል። ከአመት አመት፣ የዘረኝነት ወረርሽኙ እየባሰበት፣ አገሪቱ ወደለየለት የጥፋት አዘቅት እንዳትሰምጥ አትሰጉም? በእርግጥ፣ አልፎ አልፎ፣ የዘረኝነት በሽታው፣ ለአፍታ ጋብ ሲልለት… እሳቱም ትንሽ ሲበርድለት እያየን፣ የእፎይታና የተስፋ ስሜት እናገኛለን። ግን፣ እፎይታው ብዙም አይቆይም።
 
እንደገና በሽታው ያገረሸበታል። ማገርሸት ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ እፎይታ በኋላ፣ ወረርሽኙ ባገረሸ ቁጥር፣ ከቀድሞው እጅጉን ብሶበት እናገኘዋለን። ተስፋ አስቆራጩና አስፈሪው ነገር ደግሞ ምን መሰላችሁ? የዘረኝነት ወረርሽኙን ለማስቆም የሚያስችል፣ አስተማማኝ መላ ምን እንደሆነ በግልፅ ጎልቶ አለመታየቱ ነው። ዙሪያው ሁሉ በጨለማ የተዋጠ ጉዞ ይመስላል። (ቆንጂት ስጦታው)

ለስር ነቀል ለውጥ በሃገር ውስጥም በውጪም ተጠናክሮ ትግሉ ቀጥሏል።


ለስር ነቀል ለውጥ በሃገር ውስጥም በውጪም ተጠናክሮ ትግሉ ቀጥሏል።
 – በኣማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡን የማስተባበር ሂደቶች በተሳካ መልኩ የቀጠለ ሲሆን በደቡብ ክልል እና በኣዲስ ኣበባ ጥሩ የሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ታውቋል፤ ሕዝቡ በራሱ ኣነሳሽነት ከኣብራኩ በወጡ ሃይሎች ለውጥ መፈለጉን በመተባበር እየገለጸ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።ኢትዮጵያ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋታል ሕዝቦች በእኩልነት በሃገራቸው ጠቃሚና ተጠቃሚ የሚሆኑበት መስመር መዘርጋት ያስፈልጋል የሚሉ ብዙሃን ሕዝቦች ኣደባባይ በመውጣት በኣራቱም የሃገሪቱ ማእዘናት ከመንግስት ጋር ከመጋፈጥ ኣልፈው በቤት ውስጥ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ይህ ማለት ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ሕዝብ ከስደት ይልቅ በሃገሩ ሰርቶና ተከብሮ መኖር ይፈልጋል የመንግስትን ኣመራር የያዘው ኣገዛዝ ኢትዮጵያውያንን የመኖር ሕለናቸውን ስለገፈፈ በየሰው ሃገር ለብሄራዊ ውርደት ተዳርገዋል። በዘር ላይ የተመረኮዘ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክፍፍል ኣንድን ዘር የበላይ እንዲሆን በማድረግ ሌሎችን የበይ ተመልካች ኣድርጎ ሃገርን ለድህነት ሕዝብን ለደሃ ደሃ ሰንሰለት ኣቀባብሎ ሰጥቷል።
በእናት ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የሕወሓት አምባገነን ቡድናዊ አገዛዝ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመው የፖለቲካና የኢኮኖሚ በደል ገደቡት አልፎ ዜጎች በገዛ አገራቸው መኖር እንዳይችለ ሆነዋል፥ በሃገራችን ተከስትው ይሚገኙ የፖለቲካ ጫናዎች የኑሮ ውድነት የድርቅ የእስር የግድያ እና የተለያዩ ችግሮች አገዛዙ በሚፈጽመው በደል ላይ ተደራርበው ወገኖቻችንን እጅግ ለከፋ አደጋ አሳልፎ ሰጧቸዋል፤ይህ ከፍተኛ የሆነ ብሄራዊ ውርደት እየታየ ያለው አገዛዙ ለዜጎች ያለውን ንቀት እብሪት እና መንግስታዊ ሃሰተኝነት ከሽብርተኝነቱ ጋር ተቀላቅለው ሕዝቡን አንገፍግፈውታል፥፥የአገዛዙ ግፎች ተዘርዝረው የማያልቁ ሲሆን ለዚህ ደሞ መፍትሄው አገዛዙን አስወግዶ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው። 

Thursday, October 27, 2016

አዲሱ የራናይሰንስ ኔትወርክ ቴሌቪዥን፤ በሳሞራ የኑስ ከፍተኛ ሸር ሆልደርነት እና በአፍቃሪ ኢህአዴግ ዲያስፖራዎች ትብብር ሊቋቋም ነው


እነ ሳሙራ አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሊከፍቱ ነው፤
አዲሱ የራናይሰንስ ኔትወርክ ቴሌቪዥን፤ በሳሞራ የኑስ ከፍተኛ ሸር ሆልደርነት እና በአፍቃሪ ኢህአዴግ ዲያስፖራዎች ትብብር ሊቋቋም መሆኑን ሰማን።
ይህ የወያኔን ከፍተኛ ባለስልጣናት የገንዘብ እና ፈቃድ ድጋፍ ያገኝው የቴሌቪዥን ጣቢያ ሌላው ድብቁ በዓመት ኢቢሲ ሳይሰራ የሚያግብሰውን 112 ሚልየን ብር ገቢ ለመንጠቅ ያለመ ነው፡፡
ሌላው የፕሮፓጋንዳ ጣቢያ በአንድ ጥያቄ ከብሮድካስት ባለስልጣን ፈቃድ ያገኝ ሲሆን፡ አንዳንድ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ከገበያ ለማስወጣት እና ስልታዊ የወያኔ አላማን ለማራመድ የተነደፈ እቅድ ነው፡፡፡
ወያኔዎች በዐማራ ስም አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመያዝ መከፋፈል እና መረጃ መቋጣጠር ድብቁ አዲሱ አጀንዳቸው እንደሆነም ሰምተናል።

በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ትለምልም።



Image may contain: text– የጋራ ጠላትን ለማጥፋት መስማማት መንገዱ ኣዳላጭ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ለኢትዮጵያ የጋራ ጠላትን የማጥፋት ኣጀንዳ በሁለተኛነት እንጂ በመጀመሪያ የሚያስፈልገው በእኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ዲሞክራሲያዊ ኣድርጎ ለመገንባት ኣገራዊ ኣጀንዳ ነው። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ልጆቿን ሰብስባ እስካሁን በመደጋገፍ በስሯ አድርጋ ይዛለች፥ሁሉም ስለ ኢትዮጵያ ስለ ሃገር አንድ ሆኖ ቢከፋም ቢለማም እየጮኸ ይገኛል::ኢትዮጵያ ገዳይ አይደለችም ኢትዮጵያ አሳሪ አይደለችም ኢትዮጵያ ገራፊ ዘራፊ አይደለችም ወ.ዘ.ተ. ገራፊው ገዳዩ ዘራፊው አሳዳጁ በየስርዓቱ ራሳቸው እያፈራረቁ ሕዝብ በመንከስ ላይ የሚገኙት የገዢ መደቦች ናቸው፥ሃገር እንደ ሃገር ሕዝብ እንደ ሕዝብ በልላው ላይ የፈጠረው አሊያም የደረተው አደጋ የለም፥የሁሉ ችግሮች መነሻ እና መድረሻ ጬቋኝ እና አምባገነን አረመኔ አገዛዞች እና መሪዎቹ ናቸው ::
የኢትዮጵያ የለውጥ ፖለቲካ ኣብዛኛው የተከበበው በማግለል በመፈረጅ በኢሌ ኣውቅልሃለሁ በምቀኝነት በድብቅ የሴራ ፖለቲካና ተመሳሳይ ጉዳዮች ነው። ፖአቲካውን እንደ ግል ዘርፍ ኢንቨስትመት ለመቆጣጠር የሚፈልጉት ባለቅያሪ ማሊያዎች ለባሾች የሆኑ የስድሳዎቹ ፖለቲከኞችና በወያኔ የእሬት የዘር ፖለቲካ የተጋቱ የማያቅራቸው ዘረኞች የሆኑ የወያኔ ስርዓት ሹምባሾች ሲሆኑ እነዚህ ኣካላት ዘጠና ኣምስት በመቶ የዲያስፖራው ኣካል ሲሆኑ ትተውት የሄዱትን ሕዝብ በኣሁኑ ወቅት ያለውን ስነ ልቦና የማያውቁ ናቸው። ትንሹን ትልቅ ኣድርገው የሚጋግሩ የፖለቲካ ድሪቶ የሚያለብሱ ስለሆኡ ለኢትዮጵያ መፍትሔ ኣያመጡም። በስሜት እየተነዱ የኣምባገነኖችን እድሜ ማስረዘም ኣሊያም የርስ በርስ ጦርነት ለመፈብረክ መሮጥ ብቻ ስለሆነ ስራቸው ኣይረቡም።
ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን መፍትሄው በሕዝቦች የጋራ ትግል የሕዝቦች እኩልነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን መመስረት ዋናው ግብ መሆን ኣለበት ለዚህ ደግሞ ከሕዝብ መሃል ከትግሉ ኣብራክ ውስጥ ያሉ ዜጎች እንጅ በፈረንጅ ኣገሩ የተመቸው ዲያስፖራ በፍጹም መፍትሄ ሊያመጣ ኣይችልም። የጋራ ሃገራዊ ኣጀንዳ ባሌለበት ኣብሮ ለመስራት በመዋዋል ብቻ ለውጥ ኣይመጣም። የጋራ ማኒፌስቶ ለሕዝብ ይፋ ባልሆነበት ውህደትና የትግል ፉጨት ለሕዝብ የሚፈይደው ነገር የለም። የሆያ ሆይ የቅፈላና የወረት ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ኣይበጅም። #ምንሊክሳልሳዊ

መርሳ ከተማ በርካታ ቤቶችን (ከ500 ቤቶች በላይ) ህገወጥ ናቸው በሚል ፈረሱ፡፡


በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የምትገኘው የመርሳ ከተማ በርካታ ቤቶችን (ከ500 ቤቶች በላይ) ህገወጥ ናቸው በሚል ፈረሱ፡፡ ቤታቸው የፈረሰባቸው ያለመጠለያ መቅረታቸውን እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት መድረሱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
No automatic alt text available.

ስድስት የኬንያ ፖሊሶች በኢትዮጵያ ፖሊሶች ታስረዋል።


የኬንያ ጋዜጣ ዴይሊ ኔሽንን እንደዘገበው ስድስት የኬንያ ፖሊሶች በኢትዮጵያ ፖሊሶች ታስረዋል። ኬኒያ ሞያሌ ላይ በሚገኘው ሊያዞን ኦፊሰር አማካኝነት ፖሊሶቹን ለማስፈታት ጥረት እያደረገች ነው ተብሏል።

Monday, October 24, 2016

‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው›› – አስጎብኚ ድርጅቶች


‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው›› – አስጎብኚ ድርጅቶች
‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በቱሪዝም ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው››  - አስጎብኚ ድርጅቶች
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ተከትሎ የውጭ አገር ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ የመጓዝ ፍላጎታቸው በእጅጉ መቀነሱን የገለፁ አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ለችግሩ መላ ካልተገኘ አዋጁ በቱሪዝም ኢንዱስትሪ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያደርስ ተናገሩ፡፡ ‹‹አገር የማስጎብኘት ሥራ እንደ ማኑፋክቸሪንግ አይደለም፤ አንድ ፋብሪካ ቢቃጠል ወይም ሌላ ጉዳት ቢደርስበት በዓይን ይታያል። የቱር ኦፕሬሽን ሥራ፣ አገልግሎት ስለሆነ ጉዳት ሲደርስበት በዓይን አይታይም፡፡ አሁን በአገሪቱ በተፈጠረው ችግር ሳቢያ ዘርፉ ጉዳት ደርሶበታል›› ብለዋል፤ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ፕሬዚዳንት፤ አቶ ያዕቆብ መላኩ፡፡
አስጎብኚ ድርጅቶች ከመስከረም ጀምሮ እስከ ታህሳስ፣ ጥርና የካቲት ያሏቸውን ገበያዎች ሸጠው እንደጨረሱና ደንበኞችም ክፍያ መፈጸማቸውን ጠቅሰው፣ ለሆቴሎችና ለሌላ አገልግሎት አቅራቢያዎችም ክፍያ መፈፀማቸውን ይገልፃሉ። ሆኖም በተፈጠረው ችግር ምክንያት ቱሪስቶች ወደ አገራችን  ለመምጣት  ፍላጎት አላሳዩም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አንዳንድ ቱሪስቶች የከፈሉት እንዲመለስላቸው እየጠየቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ የጉዞ አማካሪዎችና ኤምባሲዎች የሚያሰራጩት ወደ ክልከላ ያደገ ማስጠንቀቂያ፣ ለጉብኝት ፕሮግራሞች መሰረዝ ዋነኛ ምክንያት እንደሆኑ የጠቀሱት አቶ ያዕቆብ፣ ‹‹አንዴ ፕሮግራም አድርጌአለሁ፤ ሄጄ ያለውን ነገር አያለሁ›› ብለው የሚመጡ ጥቂት ቱሪስቶች ቢኖሩም አብዛኞቹ ግን ‹‹እኔ እዚህ ዓይነት ችግር ውስጥ ራሴን አልከትም›› በማለት የኢትዮጵያን ጉዞ ሰርዘው፣ ወደ ሌላ አገር እንደሚሄዱ ገልጸዋል፡፡
ድርጅታቸው ሥራ ሲጀምር ጥቂት የነበረው የጎብኚዎች ቁጥር፣ በአሁኑ ወቅት አድጎ በዓመት ከአንድ ሺህ በላይ ቱሪስቶች እንደሚያስተናግድ የገለፁት የሞንፔይ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት አቶ ያሬድ ሙሉጌታ፤ ከኢሬቻ አደጋ በኋላ ፕሮግራሞችን እንደተሰረዙባቸው ተናግረዋል፡፡
መጀመሪያ አካባቢ በዓመት 40 ሺህ ብር ግብር ይከፍሉ እንደነበርና በአሁኑ ወቅት እስከ 1.4 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ግብር እንደሚያስገቡ የጠቀሱት አቶ ያሬድ፤ ይህ ውጤታማ ሥራ አሁን አገሪቱ ላይ በተፈጠረው አለመረጋጋት እክል እየገጠመው ነው ይላሉ፡፡
‹‹የጎብኚዎች ፍሰት ያለው ከመስከረም አጋማሽ እስከ ግንቦት አጋማሽ ነው፤ በተለይ ታህሳስና ጥር ከፍተኛ የቱሪስት ወቅቶች በመባል ይታወቃሉ›› ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ በአገሪቱ በተከሰተው ብጥብጥተስፋ ሰጪ የነበረው የቱሪስት ፍሰት አደጋ ላይ እንደወደቀ ጠቁመው፤ መንግሥት ያወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ጎብኚዎችን ፍርሃትና ጥርጣሬ ውስጥ እንደከተታቸው ያስረዳሉ፡፡  የተለያዩ አገራትም ዜጎቻቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዳይሄዱ መከልከል መጀመራቸውም ለዘርፉ ትልቅ አደጋ ነው ብለዋል፡፡
በታህሳስና በጥር ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ያቀዱ በርካታ ጎብኚዎች ጉዟቸውን እንዳይሰርዙ መንግሥት ከፍተኛ ሥራ መሥራት እንዳለበት የመከሩት የኢትዮ ቱርና ትራቭል መሥራችና ባለቤት አቶ ብሥራት ወልዱ፣ እሳቸው በድርጅታቸውም ሆነ በማኅበራቸው በኩል የሚቻላቸውን ሁሉ እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ቱሪስት ወደ ኢትዮጵያ ሲጎርፍ የነበረው አገሪቷ ራሷን ስላስተዋወቀች ሳይሆን እዚህ መጥተው በአገሪቱ መስተንግዶ ረክተው የሚመለሱ ጎብኚዎች በሚያሰራጩት መረጃ ነው ያሉት አቶ ብሥራት፤ አሁንም ቢሆን አገር ውስጥ የነበሩ ጎብኚዎች ይህን ሥራ መሥራታቸው እንደማይቀርና ችግሮች በቅርቡ ተስተካክለው ሁሉም ነገር ወደ ቀድሞው እንደሚመለስ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
አገሪቱን ለማረጋጋትና ሰላም ለማስፈን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ ብዙዎቹ አስጎብኚዎች አልሸሸጉም፡፡