Sunday, May 29, 2016

ጎንደር ህብረት አስቸኳይ መግለጫ – “የወልቃይት ጠገዴ፣ ቃፍቲያ፣ ሁመራና ጠለምት ህዝብ ፈጥኖ ደራሽ አጋር ይሻል”

ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ፤ አገር ሸንሽኖ፤ ህዝብን ከፋፍሎ፤ ለዘለዓለም የሥልጣን ዘመኑን ለማራዘም አለሞ እና ሸርቦ የተነሳውን ህልሙን ለማሳካት፤ የመጀመርያ የጥቃት ኢላማው ያደረጋት የጎንደር ክ/ሀገርን ነው። የዚም የመጀመርያው የግፍ ሰቆቃን እየተጋቱ ያሉት፤ ደግሞ ሰሜን ምዕራብ ክ/ሀገራችን ኗሪ የሆኑት የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ፀለምት ወገኖቻችን ናቸው።
ይሁን እንጂ፤ ከሰላሳ ዓመት በላይ የአካባቢዋን እና የዘር መሰረታቸውን ታሪክ ነጋሪ እንኳ እንዳይኖር፤ አንድ በዓንድ ለቅሜ አጥፍቻለሁ፤ ብሎ ያስብ የነበረውን ከንቱ የወያኔ ቅዠት አዲሱ ትውልድ፤ ለማንነቱ፤ ፍርሃትን ሰብሮ ወደ ትግል ከወጣ ውሎ ቢያድርም፤ አሁን ግን የነዚህ ወገኖቻችን የትግል ምዕራፍ የመጨረሻው የሞት ሽረት ደረጃ ላይ ደርሷል።                                        የዚህም አንዱ እና ዋንው ሀቅ፤ ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ በጉልበት የጫነዉ የመስፋፋት እና የመሬት ቅርምት አባዜን ለመገደብ፤ በሁሉም የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነት ድጋፍ ማግኘቱ ነው። ከእንግዲህ በኋላ፤ የቃፍቲያ ሁመራ፤ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ህዝብ የወያኔን የዘር አጥፊ በደል መሸከም ከሚችለዉ በላይ በመሆኑ፤ ትግስቱን ጨርሶ በአንድ ድምጽ ተማምሎ “የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር ተከዜን ተሻግሮ አያስተዳድረንም” ከሚል ዉሳኔ ላይ ደርሶ፤ የራሱን መሪና የጎበዝ አለቃ መርጧል። በጎንደሬነቱ፤ በአማራነቱ፤ በባህሉ፤ ለዘመናት በኖረበት መሬቱና በጠቅላላ ማንነቱ ላይ ግፍና መከራ ስለተፈጸመበት፤ በአንድ ድምጽ በቃለ መሃላ ነጻነቱን አዉጇል። ተወደደም፤ ተጠላም፤ ይህ የቃፍቲያ ሁመራ ወልቃይት፤ ጠገዴ፤ እና የጠለምት ህዝብ “ጎንደሬም አማራም ነን” በሚል መፈክር ለነፃነቱ ያቀጣጠለውን ትግል፤ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቅንነት መቀበል ሰባአዊነት ነው። በተለይ ደግሞ፤ ለዘመናት የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ፤ በጉርብትና ሲኖሩ፤ ተዋደው እና ተፈቃቅረው ያጋኙትን ተካፍለው ከመኖር ባሻገር፤ አንድም ቀን እንኳ፤ የመሬት ይገባኛል ግጭት አድርገው እንደማያውቁ እየታወቀ፤ በአሁኑ ሰዓት፤ የትግራይ ወገኖቻችን፤ ዘመን ካሳበጣቸው፤ ጥቂት ከውሥጣቸው በወጡ ቡድኖች ምክንያት፤ የተጠነሰሰውን፤ ታሪክን መሰረት ያላደረገ፤ የመሬት ሥግብግብነት፤ ተንኮል፤ በዝምታ፤ መመልከት፤ እጅግ አሳዛኝ የሆነ፤ የታሪክ ስህተት መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ስለሆነም፤ የትግራን እና የጎንደርን ሕዝብ የወደፊት አብሮነት ታሪክ ለማስቀጠል ሲባል፤ ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ፤ ወገኖቻችን ይዘው የተነሱበትን የማንነት ጥያቄ፤ የታሪክ እውነት መሆኑን፤ ማክበር እና መቀበል እንዳለበት ከወዲሁ ልናሳስብ እንወዳለን። አፈጣጠሩ እና ባህሪው አይፈቅድለትም እንጂ፤ ልብ ሰጥቶት የገዥዉ መደብም ቢሆን፤ ይህን የሕዝብ ውሳኔ ማከበር የጎንደርን ህዝብ ማክበር ነዉ የሚል እምነት አለን። ለዓመታት የጠዬቀዉ የጎንደሬነት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ ጭቆናዉ በዝቶበት እራሱ በመረጣቸዉ መሪወች ለመተዳደር መወሰኑ ፍህታዊ እና ህዝባዊ እርምጃ ነዉ። መከበር ይገባዋል!!
ከእንግዲህ ይህንን ህሊናዉ የቆሰለ እንግዳ ተቀባይ ደግ ህዝባቸን ላይ፤ ተከዜን ተሻግሮ ከአድዋ በመጣ ፀረ ሽምቅ ሰራዊት ተኩሶ በመግደል፤ የበለጠ ሕዝባችንን ወደከፋ መተላለቅ የሚገፋ መሆኑን ተገንዝቦ፤ ጣቱን ከመሳሪያ ምላጭ አንስቶ፤ የወገኖቻችን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲሰጥ እናሳስባለን።
ይህ ግፍ እና በደል የወለደውን፤ የጎንደሬ/የአማራ ማንነት ጥያቄ፤ ቆመንለታል ብላችሁ፤ ለ25 ዓመት በወያኔ፤ እየተሽከረከራችሁ ያላችሁ፤ የብ.አ.ዴን አባላት እና ካድሬዎች፤ የማንነታችሁ መፈተኛ ወቅት ላይ በመሆናችሁ እና፤ የመጨረሻ እጣ ፈንታችሁ ወቅት ላይ በመድረሳችሁ፤ ከእንቅልፋችሁ የምትነቁበት ደወል፤ እየተደወለ ነው። በዚያው እንዳታሸልቡ፤ ከወገኖቻችሁ ጋር ለማንነታችሁ አብራችሁ በመቆም እስካሁን የበደላችሁትን ወገናችሁን ልትክሱ የግድ ነው። እንዲሁም፤ የሰባቱ አዉራጃ የጎንደር ህዝብ፤ ጥያቄው፤ የራሱ ማንነት ጭምር መሆኑን በማመን፤ በአስቸኳይ፤ በሚፈለገው ሁሉ ትብብሩን ማሳየት፤ የግድ እሚልበት ደረጃ ላይ በመሆኑ፤ እስቸኳይ ታሪካዊ ምላሽ፤ ለወልቃይት ጠገዴ፤ ጠለምት ወገኖቻችን እንዲያሳይ የጎንደር ሕብረት ታሪካዊ እና ወቅታዊ ጥሪያችንን ለማስተላለፍ እንወዳልንለን። የጎንደር ሕብረት የተመሰረተበት ቋሚ ዓላማም፤ ሁላችንም በሰላም እና በፍቅር ታሪካዊ፤ መልካዓ ምድራችንን ጠብቀን በጋራ እንድንኖር የሚያስችለንን ታሪክ ለማስጠበቅ ነው። በመሆኑም፤ ስማችን ጎንደር ነክ ይሁን እንጅ፤ ለትግራይም ሆነ፤ ለመላ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን እኩል ፍቅር፤ እኩል፤ ተቆርቋሪነት እና ኃላፊነት ይሰማናል።
ሌላዉ ሳንጠቅስ የማናልፈዉ እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ደግሞ ባለፈው ወር የጋምቤላ ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመዉ የጀምላ ጭፍጨፋ ነዉ። የኢትዮጵያን መሬት አሳልፎ ለመስጠት በተሸረበ ሴራ ምክንያት ወያኔ፤ ጠረፍ ጠባቂ፤ ፀጥታ አስከባሪ፤ የነበሩትን የታጠቁትን የአካባቢ ሚሊሻዎች፤ ትጥቃቸውን አስፈትቶ፤ ካምፕ ውስጥ እንደከብት በመዝጋቱ ምክንያት፤ አካባቢዉን ክፍት መሆኑን የተረዱ፤ ከ እንሰሳት ዝርፊያ አልፈው የሰው ህይወት ለማጥፋት ተዳፍረው የማያውቁ የደቡብ ሱዳን ኗሪ የሙርሊ ብሔረሰቦች በወሰዱት አሰቃቂ ርምጃ ከ200 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተጨፍጭፈዉ፤ 150 ታፍነዉ ሲወሰዱ፤ እጅግ ብዛት ያላቸውን ቤት እና ንብረት አቃጥለው፤ በሺ የሚቆጠሩ የቀንድ እና የጋማ ከብቶችም ተዘርፈው ተወሥደዋል።
እንዲሁም በተመሳሳይ መልኩ በመተከል ቁጥራቸዉ ወደ 70 የሚደርሱ አርሶ አደሮች በሱዳን መንግስት ተጠልፈዉ መዳረሻቸዉ ጠፍቶ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቀንድ ከብቶችም ተዘርፈው ሲወሰዱ፤ እርምጃ የሚወስድ ቀርቶ፤ የሚጠይቅ መንግስት እንኳ አልተገኘም።
ይህ የሚያሳየው፤ አገራችንም ሆነ ሕዝባችን፤ መንግሥት ተብዬ አገር በቀል ጠላት ቅንብር፤ በውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የጥቃት አደጋ እንደተደቅነብን ነው። በመሆኑም፤ ኢትዮጵያ አገራችንም ሆነ የህዝባችን ደህንነት የሚጠብቅ መንግስት እንደሌለ አዉቀን በሞቱት ወገኖቻችን መሪሪ የሆነ ሃዘናችንን በሃገራዊ ቁጭት እየገለጽን፤ ለዘመድ አዝማድ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን እንላለን። የደቡብ ሱዳንም ሆነ የሰሜን ሱዳን መንግስት በወያኔ ቅጥረኞች ታፍነዉ የተወሰዱ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ከነንብረታቸዉ ወዳገራቸዉ በአስቸኳይ እንዲመለሱ፤ ወንጀለኞችም ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን። የመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብም፤ በዬአካባቢው የራሱን መሪ መርጦ፤ ደህንነቱን ጠብቆ፤ ዳር ደንበሩን እንዲያስከብር ጥብቅ መልክታችን እናስተላልፋለን። ከዉጭ አገር ጋር ተባባሪ የሆነዉ የወያኔን መንግስት እንደ አገር መሪ ቆጥሮ ህዝባችን እንዳይዘናጋ አደራ እንላለን።
በመጨረሻም በጎንደር ክፍለ ሀገር በቋራ ወረዳ የጓንግን ወንዝን ተሻግሮ ከኢትዮጵያ መሬት የሰፈረዉ የሱዳን ወታደር በአስቸኳይ እንዲለቅ እንጠይቃልን።
ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ዳር ድንበሩን ያስከብራል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
ጎንደር ህብረት

የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

የሕወሓት ባለስልጣናት ከአደባባይና መድረክ ለመደበቅ የወሰኑ ሲሆን ቀጣዩ የደህንነት ተቋሙ አሰራር ላይ መከሩ

 የደህንነት ተቋሙ አሰራር በአዲስ መልክ ሊቀየር መሆኑ ተሰምቷል::አዲሱ አሰራርን በተመለከተ ጥናት መጀመሩን እና በደህንነት ተቋሙ ውስጥ ከሕወሓት አባላት ውጪ ሌሎች የሚኖራቸውን ሚና የሚገድብ መሆኑ ታውቋል::እንዲሁም ወታደራዊ ደህንነቶች መበርከት ስላለባቸው አዳዲስ ሰልጣኞችን በመሰብሰብ በሰራዊቱ ውስጥ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን ማውደም እንደሚቻል ታሳቢ ተደርጎ አዳዲ ወታደራዊ ደህነቶች በጦላይ ስልታና እንዲሰጣቸው እንዲሁም የወታደራዊ ደህነት መኮንኖች እስራኤል እና ሩሲያ ሄደው እንዲሰለጥኑ አስፈላጊው ስራ እንዲሰራ ተወስኗል::ወታደራዊ ጄኔራሎች በሳምንት ውስጥ ብቻ ከደህንነት ተቋሙ ባለስልጣናት ጋር ከዚህ ቀደም በተሻለ በተከታታይ እየተገናኙ በሃገሪቱ ላይ የሚነሱ ችግሮች የክልል ባለስልጣናትን በማስቀደም በእንጭጩ በፍጥነት እንዲቀጩ ተወስኗል::
የግንቦት ሃያን የወያኔ በዓል ተከትሎ የሕወሓት ባለስልጣናት ወደ አደባባይ መውጣትን ሊቀንሱ ይገባል የሚለው ሃሳብ ላይ መመከሩ ለደህንነት ቢሮ ቅርብ የሆኑ ሰዎች ገልጸዋል::በዚሁ የምክክር ስብሰባ ላይ አደባባይ ላይ እጅግ አስፈላጊ ሆኖ እስካልተገኘ ድረስ ከፍተኛ የሕወሓት ባለስልጣናት ሕዝብ ፊት ሳይታዩ ከጀርባ ሆነው ስራ ለመስራት ተነጋግረዋል::በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ጥላቻ እያተረፍን ነው የሚል እደምታ ያለው አጀንዳ የተነሳበት ይህ ምክክር ከሙስና እና ከግድያ እንዲሁም ከእስር ጋር በተያያዘ በስፋት እጅ የሚጠቆመው በሕወሓት ባለስልጣናት ላይ እንጂ በሌሎች የኢሕኣዴግ አባል እና አጋር ድርጅቶች ላይ ስላልሆነ እንዲሁም የግንባሩ ድርጅቶች አባላት ሳይቀሩ እጃቸውን ሕወሓት ላይ መጠቆም እንደደረሱ በምክክሩ ላይ መተማመን ላይ ተደርሷል::ከዚህ ቀደም ከክልል ባለስልጣናት ይሁን ከፌዴራል ባለስልጣናት ጀርባ የሕወሓት ባለስልታናት እንዳሉ ቢታወቅም አሁን የታሰበው ለየት የሚያደርገው ግን በረቀቀ መልኩ ለማዘዝ የክልል ባለስልጣናትን ለመወንጀል መዘጋጀታው ነው::
ማንኛውንም ጉዳዮች በማስፈጸም እና በመተግበር ስራ ላይ ሊሰማሩ ይገባል ተብለው የታጩት በሃይለማርያም የሚመራው የደቡብ ድርጅት አባላት ሲሆኑ እንደ ኦሕዴዽ እና ብአዴን እስጥ ያሉ ሰዎች በጥንቃቄ ክትትል እየተደረገባቸው የሕወሓት ባለስልጣናትን ትእዛዝ እንዲፈጽሙ እንዲሁም ማንኛውም ትእዛዝ ለአንድ በክልል ይሁን በፌዴራል ለተመደበ ባለስልጣን ከሕወሓት ሰዎች በቃል ብቻ እንዲወርድ ተደርጎ ምስጢር እንዲጠብቅ እና አፈጻጸሙን እንዲተገብር ማበረታቻ ገንዘብ በማጉረስ ለሚፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ ማድረግ እንደሚቻል ከስምምነት ተደርሶበታል::በሕዝብ ዘንድ ማጉረምረም ቢከሰት ወዲያው ባለስልጣኑን በማሰር አሊያም በመቀየር እንደሁኔታው ወቅታዊ ትኩሳቶችን የተከተለ እርምጃ በልጥሎች እንዲወሰድ እንደሚደረግ ተመክሮበታል::የሕወሓት ባለስልጣናት ከዚህ ቀደም እንደሚያድርጉት ፊትለፊት ድንፋታ እና ፊትለፊት በመጋፈጥ ማዘናጋት ማጭበርበር የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው እና ሕዝቡ እንደነቃ በምክክራቸው ላይ ከመተማመን መድረሳቸው ራሳቸውን ቀስ በቀስ ከሕዝብ መድረኮች በማሸሽ እና ጉዳያቸውን በትእዛዛቸው መሰረት ከሚፈጽሙት ጀርባ ሆነው ከቀደድሞው በተለየ በረቀቀ መልኩ ሊተገብሩ ተስማምተዋል::ቀጣዩ የፕሮፓጋንዳ ስራ የሚሆነው የፖለቲካው ስልጣኑ ከሕወሓት ሰዎች ውጪ እንደሆነ አድርጎ ሕዝብን ማሳመን እንዲሆን ይደረጋል:: 
Minilik Salsawi's photo.

ኬንያ የአለማችን ትልቁን የስደተኞች መጠለያ መዝጋቷን ተመድ ተቃወመ

ከ 300 ሺ በላይ ሶማሊያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ወስናለች
ኬንያ በአለማችን በትልቅነቱ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዘውን የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመዝጋት መወሰኗን የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔውን እንደሚቃወመው ማስታወቁን ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘገበ፡፡
የተመድ ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን፤ ኬንያ ግዙፉን የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ለመዝጋት መወሰኗ፣ በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ የሚገኙ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለከፋ አደጋና ጥፋት የሚዳርግ በመሆኑ ውሳኔውን እንደሚቃወሙት ማስታወቃቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡ የኬንያ ምክትል ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ባለፈው ሰኞ በቱርክ መዲና ኢስታምቡል በተካሄደው የዓለማችን የሰብዓዊ ጉዳዮች ጉባኤ ላይ የአገሪቱ መንግስት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያውን በመዝጋት 300 ሺህ ያህል ሶማሊያውያን ስደተኞችን ወደመጡበት ለመመለስ ያሳለፈው ውሳኔ የማይቀለበስ ነው ሲሉ መናገራቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ ስደተኞቹን መልሶ ለማስፈር ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውንም አመልክቷል፡፡ የኬንያ መንግስት የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ለመዝጋት የወሰነው፣ የሽብርተኞች መደበቂያና ለአገሪቱ ደህንነት ስጋት በመሆናቸውና ለአካባቢው አደጋ ስለሆኑ ነው ማለቱን የጠቆመው ዘገባው፣ተመድ ውሳኔውን ተቃውሞታል፡፡

ዶ/ር ቴዎድሮስ ከቀናቸው፣ የ600ሺ ብር ደሞዝተኛ ይሆናሉ

ዶ/ር ቴዎድሮስ ከቀናቸው፣ የ600ሺ ብር ደሞዝተኛ ይሆናሉ

ከኢትዮጵያ መንግስት በፊት፣ 31 አገራት ለዶ/ር ቴዎድሮስ ድጋፍ ሰጥተዋል
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፤ ከአመት በኋላ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ለመሆን በምርጫ ካሸነፉ፣ በተባበሩት መንግስታት ውስጥ ከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ የያዙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ይሆናሉ፡፡
ለዓለም ጤና ድርጅት መሪነት ድጋፍ ሲያሰባስቡ የቆዩት ዶ/ር ቴዎድሮስ፤ ከ31 የአፍሪካ ሀገራት ድጋፍ እንዳገኙ መረጃዎች አረጋግጠዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፉን የገለፀው፣ ገና በዚህ ሳምንት እንደሆነም፣ ምንጮች ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ቴዎድሮስን ጨምሮ አምስት ሰዎች በየፊናቸው ድጋፍ ለማግኘት ሲጣጣሩ የቆዩ ቢሆንም በመጪው ሐምሌ ወር ለሚካሄደው ምርጫ በተወዳዳሪነት የሚቀርቡት ግን ሶስት እጩዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአለም አገራት በሚሰጡት ድምጽ ቀዳሚውን ደረጃ ያገኘ ተወዳዳሪ፣ የአለም ጤና ድርጅት ዳሬክተር ይሆናል፡፡ ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሸነፉ፣ የመጀመሪያው አፍሪካዊ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ይሆናሉ ተብሏል፡፡ የዳሬክተሩ የወር ደሞዝ 31ሺ ዶላር ገደማ ነው (ከ600ሺ ብር በላይ)፡፡

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ ነው

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ ነው
 Addis Admass
   በየመን በኢትዮጵያ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋሉትና በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ልጅ የሆነቺው የ9 አመቷ ታዳጊ ምናበ አንዳርጋቸው፤ አባቴ ከእስር የሚፈታበትን መንገድ አላመቻቸም በሚል የእንግሊዝን መንግስት ልትከስ እንደሆነ ዘ ኢንዲፔንደንት ዘገበ፡፡ የታዳጊዋ የህግ ባለሙያዎች የእንግሊዝ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚገባውን ያህል አለመከታተሉና ከእስር የሚፈቱበትን መንገድ ለመፈለግ እስከመጨረሻው አለመግፋቱ በህግ ያስጠይቀዋል ማለታቸውን የጠቆመው ዘገባው፣ የእንግሊዝን መንግስት በህግ መጠየቁ፣ አቶ አንዳርጋቸው ከእስር የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው መናገራቸውን ገልጧል፡፡
በእንግሊዝ የውጭና የኮመንዌልዝ ቢሮ ፤የአቶ አንዳርጋቸው እስርና አያያዝ ተቀባይነት የሌለው ነው ቢልም፣ ከእስር ተፈትተው እንዲወጡ ግፊት አላደረገም ያለው ዘገባው፣ ልጃቸው ምናበ፤ አባቷ የሚፈቱበትን ሁኔታ ለመፍጠር ተጨማሪ ጥረት ያደርጋል በሚል ተስፋ መንግስትን ለመክሰስ መዘጋጀቷን ጠቁሟል፡፡

ቴአትርና ፊልም አሁንም ባርነት ላይ ናቸው፡፡ ክ/ሀገር ቴአትር ማሳየት አይታሰብም፡፡


ግንቦት 20፤ ለኪነ-ጥበቡ አበረከተየሚባለው ነገር ቅድመ ምርመራን ማስቀረቱቢሆንም ቴአትርና ፊልምን ግን ከደርግ ሳንሱርአልተላቀቁም፡፡ ለምሳሌ ሥነ ጽሑፍ፣ ስዕልናሙዚቃ ቅድመ ምርመራ አይካሄድባቸውም፤ቀድመው አይታዩም፤ አይመረመሩም፡፡ ይሄመጽሐፍንም ጋዜጣንም ጭምር ነው፡፡ ፊልምናቴአትር ግን ይገመገማሉ፡፡
በደርግ ጊዜ የነበረውአሰራር በፊልምና ቴአትር ላይ እስካሁን ቀጥሏል፡፡ለምሳሌ ቴአትር ለማሳየት ባህልና ቱሪዝምፈቃድ ካልሰጠሽ ቴአትርሽ አይታይም፡፡ ባህልናቱሪዝም ፈቃድ ካልፃፈ፣ ክ/ሀገር ሄደሽ ቴአትር ማሳየት አይታሰብም፡፡ ፊልምሽ ሲኒማ ቤት ለመታየት መጀመሪያ መገምገም አለበት፡፡በአንቺ ስራ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሰዎች(ገምጋሚዎቹ) “ይህን ነገር ጨምር፤ ይህንን ነገርአውጣ” የማለት መብት አላቸው፡፡ እስካሁን በግምገማ ምክንያት የታገዱ ምን ምን የመሳሰሉ ቴአትሮችና ፊልሞች አሉ፡፡
“ወይ አዲስ አበባ” የተባለ የጌትነት እንየው ቴአትር በግምገማ ምክንያት ከታገዱት በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ይህ ቴአትር ተገምግሞ ታግዷል፡፡ ይህ የሆነው ሊከፈት ለህዝቡ መጥሪያ ከተላከ በኋላ ነው፡፡ ኢህአዴግ ወይም ግንቦት 20፤ ፊልምና ቴአትርን ገና ነፃ አላወጣቸውም፡፡ በቃ ቴአትርና ፊልም አሁንም ባርነት ላይ ናቸው፡፡

Saturday, May 28, 2016

በድንፋታና በሃሰት የታጠረው የግንቦት ሃያ አከባበርና አስታዋሽ ያጡ በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችን ዋይታ

በድንፋታና በሃሰት የታጠረው የግንቦት ሃያ አከባበርና አስታዋሽ ያጡ በረሃብ የተጎዱ ወገኖቻችን ዋይታ
) ወያኔ ኢሕአዴግ ስልጣን የተቆጣጠረበት እና የስጋና የመንፈስ መንታ ወንድሙን ገድሎ እሱ የተነሳበትን 25 አመት በማክበር ላይ ይገኛል::ሕወሓት መራሹ ኢሕአዴግ አፄ ሃይለስላሴ በገነቡት ስታዲየም ውስጥ ምንም የመሰብሰቢያ አዳራሽ/ስታዲየም ሳይገነባ ስለ ልማት ሲያወራ ውሏል::ኢሕአዴግ ራሱን የሚያወዳድረው ከራሱ እቅድ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ሳይሆን ከሞቱ እና ከተቀበሩ ጨቋኝ ገዢዎች ጋር መሆኑን የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ራሱ ወያኔ ጨቋኝ አምባገነን መሆኑን ብቻ ነው::
ለግንቦት ሃያ አከባበር 20 ቢሊዮን ብር መድቦ ድንኳን በየመንገድ ዳር ተክሎ የሚጮሕወ ወያኔ በቢሊዮን ዶላር እርዳታ የሚፈልጉ በድርቅ እና በረሃብ የተጎዱ በስማቸው ገንዘብ ለምኖ የሚሰበስብባቸው ዜጎችን ለማስታወስ ፍላጎት የለውም::
Minilik Salsawi's photo.
ግንቦት 20 አምባገነኑና ጨቋኙ የደርግ ስርዓት የተገረሰሰበት ብቻ ሳይሆን ስር የሰደደ የድህነትና የድንቁርና ምዕራፍ በዲሞክራሲ ሽፋት ተከፍቶ ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ሕዝብን ሲፈጅ የኖረበት የእኩይ ቀን መጀመሪያ ነው:: በከፍተኛ ወጪ የአንድ ቀን ፌሽታ ከማድረግ ይልቅ ለዘለቄታው የተጎዱ ኢትዮጵያውያን መታደግ እየተቻለ ከነካድሬዎቹ ተሰብስቦ ጮማ እየቆረጠ ውስኪ የሚራጨው የሕወሓት አገዛዝ ቀንከቀን የሚወቅሳቸውን የንጉሱን እና የደርግን ተግባር በመድገም ብቻ ሳይሆን በአደባባይ በውሸት ሸፋፍኖ ለማለፍ ሲጣጣር እየተጋለጣ ይገኛል::በሙስና ተወዳዳሪ ያልተገኘላቸው ባለስልጣናቱን በመታቀ ከሃገር ውስጥ የሚገኘውን ሃብትና ንብረት እንዲሁም ከውጪው አለም የሚገኘውን እርዳታ እና ብድር ቅርጥፍ አድርገው በመብላት ሃገሪጥውን በልማት እያራመድን ነው በማለት ታይቶ የማይታወቅ ድህነት በደብል ዲጂት አሳድገዋል:: ኢትዮጵያ ዜጎች ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የማያደርጉባትና ቢያደርጉም በጠራራ ፀሃይ የሚገደሉት ነበረች ነች እየሆነችም ነው::
ስንቱን እንስተን ስንቱን እንደምንጥል አናውቅም::በሃገር ቤት ባሉት የግል ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ በላያቸው ላይ ነጋዴ ሆኖ የተነሳው አገዛዝ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቋረጥ ብቻ 40 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ በ6 ወር ውስጥ አድርሶ በ9 ወር ከኤሌክትሪክ ኤክስፖርት የተገኘውን 35 ሚሊዮን ዶላር “ኪራይ ሰብሳቢነት ለአደጋ አጋልጦናል::” የሚለው ኢሕኣዴግ በሙስና ተቀራምቶታል::ይህ እድገት ብለው የሚያወሩት በሌላ መንገድ ደሞ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ነው ብለው ኢኮኖሚው ስጋት ላይ መሆኑን የሚነግሩን ችጋራም ባለስልጣኖች ሃገሪቷን እየገደሏት ነው::ሃገሪቷን በተለያየ መንገድ እያጠፏት የሚገኙት ወያኔዎች ለክብረ ባዓላቸው ያወጡት ከፍተኛ ገንዘብ በርካታ ዜጎችን ከረሃብ ሃገሪቷንም ከልመና ታሪኳ ይገላግላት ነበር::ቢሆንም ይህን ለማድረግ ባለመቻላቸው ስለ ልማት በባዶው ሲደሰኩሩ እየሰማን ነው::ይህንን ድንፋታም እና ሃሰተኛ መንግስት ለመጣል እርስ በእርስ ከመነቋቆር ወጥተን ለሕብረት ቆመን ተግባራዊ ስራ መስራት ይጠበቅብናል