Thursday, July 20, 2017

አዲስ አበባ የሥራ ማቆም አድማውን ተቀላቀለች – ኮልፌ፣ አጠና ተራ፣ ሳሊተ ማሪያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ሱቆች ተዘጋግተው ውለዋል


      




(ዘ-ሐበሻ) ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው የሥራ ማቆም አድማ አዲስ አበባ ደረሰ:: ዛሬ በአዲስ አበባ በኮልፌ እፎይታ ፣ አጠና ተራና ሳሊተ ማርያም አካባቢ ሙሉ በሙሉ የንግድ ሱቆች ተዘግተው ውለዋል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም ሕዝቡ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሰዎችን እያደረገ ነው::

በአዲስ አበባ ከፍተኛ የገንዘብ ዝውውር በሚደረግባቸው በኮልፌ ቀራኒዮ እፎይታ እና ታይዋን ገበያ ሕንጻዎች ሳይቀሩ ተዘግተው መዋላቸውን ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::
እንደምንጮቻችን ገለጻ  ሳሊተ ማርያም አካባቢም እንዲሁ ሱቆች ተዘጋግተው የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል::
በአዲስ አበባ ሳሊተ ማሪያም ቤተክርስቲያን  አካባቢ ያሉ ሱቆች በመዘጋት ላይ ናቸው:: አካባቢውን ፌደራል ፓሊስ ወሮታል:
የሕወሓት መንግስት ተላላኪዎች ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ የሚያስገድዱ መ ል እክቶችን ቢያስተላልፉም ነጋዴዎች እምቢታን መርጠዋል::

Wednesday, July 19, 2017

በኦሮሚያ ክልል የተቃውሞ ስራ ማቆም አድማ ቀጥሎ ሻሸመኔ ደርሷል ። በሻሸመኔ እና አከባቢው የሚገኙ ከተሞች በክልሉ እና በፌዴራል ፖሊስ ተወረዋል።


በኦሮሚያ ክልል የተቃውሞ ስራ ማቆም አድማ ቀጥሎ ሻሸመኔ ደርሷል ። በሻሸመኔ እና አከባቢው የሚገኙ ከተሞች በክልሉ እና በፌዴራል ፖሊስ ተወረዋል።
በኢትዮጵያ በሚገኙ ቁርጥ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ላይ የተደረገው አዲስ የቀን ገቢ ግምት ያስነሳው የተቃውሞ ሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ያደረጉት ሥራ የማቆም ዐድማ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። mereja.com

በጎነደር በጎጃም እና በትግራይ ክፍለሃገሮች ህዝቦች የተፈጠረው የዘር ትርምስ ተጠያቂው የህወሓትና የበኣዴን ኣማራርርና ቅጥረኛ ካድሬዎቻቸው ናቸው!!



  
By ሳተናውJuly 19, 2017 21:28


ከኣስገደ ገብረስላሴ 
ኣንድኣንድ ወገኖች ገዱ ሽማግሌዎች ይዞ ወደ ትግራይ ይመጣል ተብሎ ከተነገረላቸው ረ
በኃላ ። በጠቅላላው የተፈጸመው ወንጀል ገዱ ኣንዳርጋቸው ብቻ መሆኑ በማህበራዊ ሚድያ ሲንጸባረቅ እመለከታሁ ።
ኣስገደ ገብረስላሴ
በእኔ እምነት ግን መጀመሪያ ከላይ የጠቀስካቸው ፓርቲዎች ስራ ኣስፈጻሚ ናቸው ሴሮኞችና ወንጀለኞች ።ከዛ በውረድ ተዋረድ ማእከላይ ከሚቴ ካድሬዎች የጸጥታ ሃይሎች ናቸው ወንጀሎኞች ።
ገዱ ኣንዳርጋቸውና መዋቅሩ የፓርቲው ወሳነ እሳት በመቀጣጠል ህዝብ እንዲፈጅ ዜጎች ለቡዙ ኣመታት ደክሞው ያፈሩት በቢሊዮን የሚቆጠር ሃብት ኣውድማል ። ይህ ከባድ ወንጀል የፈጸመ መሪ ይቅር እና ያገር መሪ ሆኖ ሊመራ ወይ ቆሞ ባገር ውስጥ ሊቀመጥ የሚዳኝ ቢገኝ ሞት ፍርድ ያስፈርዳል ። ግን በኣዴን ህወሓት እንዴት ስጋቸው ይቆርጣሉ ???
ገዱ ኣንዳርጋቸው ከነ መዋቅሩ ገዳይ ካልነው ? ኣባይ ወሉ ከነመዋቅሩስ ምን ብለን እንሰይመው ምንስ ያበኳ ነበር ? የትግራይ ህዝብ እምቢ ኣንዘምትም የማን እጅ ወደማን ይቀስር ብሎት ነው እንጅ ልክ ገዱ እንዳርጋቸው ደመቀ መኮነን በሬድዮ ጣብያዎች ኤፍኤሞች በዬወረዳው እየዞሩ በሰሚናር በመቀስቀስ የዘር ቀስቃሽ የሆኑ ሙዚቃዎች እና ኪነቶች የዘር መርዝ በመርጨት የቀለጠ ግብዣ በማድረግ የዘር እልቂት እንደኣወጁ ሁሉ ፣ ኣባይ ወልዱና መዋቁሩም በድመጽ ወያነ ሬድዮ በየዞኑ በሚገኙ ኤፍ ኤም ሬድዮ ከሁለት በላይ የኪነት ቡዱን ወደ ዘር እልቂት የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን ለትግራይ ህዝብ በጎንደር እና ጎጃም ህዝብ ጦርነት እንደታወጀበት የሚያስቆጥር ፣ ከኣላማጣ እስከ ሕሞራ ፣ዳንሻ ፣ዓዲረመጽ ፣ ጸገዴ ኣባይ ወልዱ እና የህወሓት መሪዎች ፖለቲካ ሃላፊ ኣለም ገብረዋህድ የጸጥታ ሃይሎች ቀስቅሰዋል ። ግን ማን ይዝመትላቸው ። የትግራይ ህዝብ የትግል ተሞክሮ ስላለውና በመሰረቱ የሁለቱ የተበላሹ ፓርቲዎች ሴራ መሆኑ በሚገባ ስላወቀ ነው ።
እኔ ለነዚህ ኣፋኞች በሚዛን ሳስቀምጣቸው ገዱ ፊት ለፊት ህዝብ ጨርሰዋል ።ኣባይ ወልዱም የሚዘምት ህዝብ ቢያጣም ቡዙ ወገኖች ኣስሮ የገቡበት የማይታወቅ ተሰውረዋል ። ስለዚህ ሁለቱ ከነቡዱኖቻቸው ለፍርድ መቅረብ ኣለባቸው!
ትልቁ ነገር ደግሞ የኢህኣደግ ስርኣትም መፈረድ ኣለበት ። ቅጣቱ ደግሞ ህዝቡ በነሱ ሴራ እየተነዳ እርስ በእርሱ ከሚባላ የነሱ ሴራ ወደ ጎን በመተው ህዝብ የራሱን ኣንድ ወጥ መሪ ድርጅት ፈጥሮ ኣስወግዶ ፍርዳቸው ካልሰጠ እርሱ በእርሱ እየተወናጀለ እድሚያቸውከማራዘም ከመራዘም ኣልፎ ሌላ ፋይዳ የለውም
ሌላ በዲያስፖራ ያሉ ኣንድ ኣንድ ወገኖች በሃገራችን ያለው የዘር ግጭት እንዲባባስ እያደረጉ ያሉ የማይናቅ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጱያውን የተለያዩ የዜና ማእከላት ማህበራዊ ሚዲያ ፣በውጭ በስደት ያለው ህዝብ በመደናገር ወደ ኣገር ውስጥ የዘረኝነት መርዝ ግብኣት እየረጩ የህወሓት በኣዴን ፣ኢህኣደግ
ለመፈጽሙት ወንጀል ክርቢት ያቀብላሉ ። እነዚህ ወገኖች በተሰደዱበት ኣገሮች ያለ ጠንካራ ጎናቸው በምምረጥ ለሃገራቸው ቅን ግብኣት ቢያሳረጩ መልካም ነው ።
በመጠቃለል የጎንደር እና የጎጃም ተወካዮች ትግራይ ይገባሉ ምናልባት ከትግራይም ወደ ጎጃምና ጎንደር ከሄዱ ኣያሰሩዋቸውም እንጅ ይህ መልካም እድል እንደኣጋጣሚ ኣግኝታችሁ በምታውቃት ህዝብ ግንኝነት ተዋያይታችሁ ለዘለቄታ ሰላማችን መፍትሄ ልታፋላልጉ እመክራለሁ። ምክር የሚገኝ ከህዝብ ነው ።
ወንጀለኛ መሪዎች ለፍርድ ይቅረቡ ፣
ከኣስገደ ገብረስላሴ
12 / 11 /2009

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በመድፍ የታጀበ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው | ተዋጊ ጀቶች በባህርዳር በኩል ወደ ሰሜን ሄዱ


       




(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በተለይም በኢሮብ ወረዳ ማጭዓ ከሚባል አከባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ:: ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግስታት ስለተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያወጡት መረጃ ባይኖርም ከሕወሓት መራሹ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተዋጊ ጀቶች በባህር ዳር በኩል ወደ ሰሜን ሲሄዱ እንደተመለከቱ የዓይን እማኞች ገልጸዋል::
በኢሮብ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ በመድፍ ጭምር የታገዘ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች የገለጹ ሲሆን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳና መነሻው ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም::
የኤርትራ ሠራዊት ከማጭዓ ምብላዕ ሓኽለ እስከ እንዳ ማካኤል ቤተክርስቲያን ድረስ በመግባት ምሽጎችን መቆፈሩን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ጥሶ በመግባት ምሽግ እስከሚቆፍር ድረስ የድንበር ጠባቂዎች የት ነበሩ? የሚል ጥያቄን አስነስቷል::

ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ድንበር ሠራዊቱን እያስጠጋ ሲሆን ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ በጎንደር ዳባት አቅጣጫ ወደ ሰሜን መስመር በኦራል መኪኖች የተጫኑ ሠራዊቶች ሲሄዱ መታየታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸውልኛል ሲል አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ ዘግቧል::
ዜናውን ተከታትለን እንዘግባለን::

Monday, July 17, 2017

በኦሮሚያ ወረዳዎች የተነሳዉ ህዝባዊ የግብር ይቀነስ ጥያቄ ምላሹ ጠመንጃ ለምን ሆነ ?

  





በአንቦ፣ወሊሶ ፣በጉደር፣ጊንጪ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ግብርን በመቃወም ህዝብ ጥያቄ ማቅረቡ ለምን ወንጀል ይሆናል? ለምንስ በጥይት ያስደበድባል?
ያልተጻፈዉ የወያኔ ህግ ብዙ ነዉ::ምንም ጥያቄ ህዝቡ ቢጠይቅ በጥይት ይደበደባል:: አስደብዳቢዎቹ ደግሞ በኦሮሞ ህዝብ ስም የኦሮሞ ብሄረተኘነትን እናራምዳለን እያሉ የሚያናፉት እነ ኦህዴድ ናቸዉ::

አንድ ጊዜ በወልመራ ወረዳ የሚኖሩ ገበሬ የኦህዴድ ካድሬዎችን እንዲህ ሲሉ አፋጠዋቸዉ ነበር::”እናንተም ገደላችሁን ወይም ትግሬም ገደለን ያዉ ለእኛ ሞት ነዉ::ኦህዴድ ለምንድን ነዉ ከኦሮሞ ህዝብ ጎን ቆሞ የኦሮሞን ህዝብ ጥያቄ የማያደምጠዉ?የወያኔን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከምትራወጡ የህዝብ ጮህት ለምን አትሰሙም::”
ዛሬ የኝህ አርሶ አደር ጥያቄ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነዉ::
በኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ ከመቶ በላይ በብሄር የተደራጁ ፓርቲዎችን ወያኔ ቀፍቅፋለች::እነዚህ በዬብሄሩ የተደራጁ ፓርቲዎች ግን ዋና ስራቸዉ በስሙ የተደራጁትን ህዝብ ማስፈጀት እና ማሳረድ ነዉ::የወያኔም ዋናዉ ግቡ የገደለህ የራስህ ብሄር ድርጅት ነዉ ብሎ እጁን በዉሃ ታጥቦ በመጨረሻዋ ሰዓት ፊቱን አዙሮ እብስ ማለት ነዉ::
ህዝብ ከህዝብ ቢተላለቅ: ኢትዮጵያ በሳት ብትያያዝ: ብሎም አጠቃላይ የሰበአዊነት ቀዉስ በዚያች ሀገር ዉስጥ ቢፈጠር ወያኔ ግድም አይሰጠዉ::ስልጣን ላይ እስካለ አንዴ በግብር: አንዴ በኢንቨስትመንት: አንዴ በድብቅ የሚዘርፈዉን ሀብት ማግበስበሱ ብቻ ነዉ አንድ ቁጥር አላማዉ::
አምቦ የአውቶቡስ መናኸሪያ እንዲህ ተጨናንቋል::

በኦሮሚያ ወረዳዎች የተነሳዉ ህዝባዊ የግብር ይቀነስ ጥያቄ ምላሹ ጠመንጃ ለምን ሆነ ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ መልሱ አንድ ነዉ::ከወያኔ ባህሪ የሚመነጭ ነዉ::ይሄ ጥያቄ በየትኛዉም የሀገሪቱ ክፍል ቢነሳ መልሱ ጠመንጃ ነዉ::በየትኛዉም የሀገሪቱ ወረዳ ወይም ቀበሌ እንዲህ አይነት የእዉነት ህዝባዊ ጥያቄ ከተነሳ መልሱ የሚሆነዉ ጠመንጃ ነዉ::

ለምን? ወያኔ ህዝባዊ መሰረት ስለሌለዉ ህዝባዊ ጥያቄዎችን ማስተናገድ አይችልም::ገዳይ እና አስገዳይ አድርጎ የመለመላቸዉ እና በዬብሄረሰቡ ስም ያደራጃቸዉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ህዝባዊ መሰረት ስለሌላቸዉ የህዝቡን ጥያቄ የሚያደምጡበት ጆሮም የላቸዉም::የወያኔን ትዕዛዝ ተቀብለዉ ህዝቡን ለመግደል ግን ቁርጠኛ ናቸዉ::
በእጅጉ የሚያሳዝነዉ ደግሞ በተቃዉሞ ጎራዉ የተሰለፈዉ ሀይልም ከግል ስሜቱ እና የፖለቲካ እይታዉ ከረጢት ዉስጥ ወጥቶ በጋራ በመምከር ሀገራዊ መፍተሄ የሚያመጣ እርምጃ ላይ ላለመስማማት ያለዉ ቁርጠኛ አቋም ነዉ:: ህዝቡ ግን ብዙ ህዝባዊ ጥያቄዎች አሉት::እያንዳንዱን ህዝባዊ ጥያቄዉን ባነሳ ቁጥር ደግሞ በወያኔ የሚያስገድለዉ ነዉ::

አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ህዝባዊ ጥያቄ ግን በአንድ ማዕቀፍ ዉስጥ የሚፈታዉ እና ህዝቡም እፎይታ አግኝቶ ወደ ብልጽግና መገስገስ የሚችለዉ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በእዉነት መፍጠር ከተቻለ ብቻ ነዉ:: ወደዚህ ግብ የሚሰሩ ተቃዋሚ ሀይላት እስካልተፈጠሩ ድረስ ኩነቶች ይቀጥላሉ::
ለጊዜአዉ እንኳን በጠባብ ፍላጎት አብጠዉ የሚመጡ ሀይላት አሸናፊ ቢሆኑም አስተማማኝ እና ሁል አቀፍ ህዝባዊ ምላሽ መስጠት አይችሉም::ትርምስ እና ትርምስምሱ ይቀጥላል::ህዝብ ግን ከዚህ መከራ የግድ መዳን አለበት::ኢትዮጵያ ከዚህ ሁሉ ህመም መዳን አለባት::

የሕሊና ዳኝነት እና ቀጣዩ ፈተና | ከኤርሚያስ ለገሠ




” ችግሩ ካልተፈታ የአማራ ህዝብ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን እናደርጋለን!” ይሄን የተናገረው የብአዴን ካባ የለበሰውና አማራ ክልል ተብሎ የተፈጠረውን አስተዳደር ለረጅም ጊዜ የመራው አቶ አዲሱ ለገሰ አይደለም። ” ኦቦ!” ምን ጐድሎበት ይሄን ይላል። ” ላለፋት አስር አመታት አንድም አዲስ ማከፋፈያ አልተገነባ።” ይሄንንም ያለው የኢህአዴጉ ጐብልስ በረከት ስምኦን አይደለም። እሱስ ቢሆን ምን ጐድሎበት ። ” ያሉት 25 ሐይል ማከፋፈያ (substations) አብዛኛው በደርግ ጊዜ የተሰሩ ናቸው። አርጅተዋል። ቮልታቸው አነስተኛ ነው። እነዚህን ይዞ ፋብሪካ መገንባት አይቻልም። የተገነቡትም መስራት አልቻሉም። ክልሉ ባለሃብቶችን መጥታችሁ አልሙ የማለት ሞራል የለንም።” ይሄንንም ህውሓቶች እና የፌስ ቡክ ስኳዶቻቸው የቁርጥ ቀን ልጆቻችን የሚሏቸው ታጋይ ታደሰ ጥንቅሹ፣ ታጋይ ካሳ ሸሪፎ፣ ታጋይ ህላዌ ዬሴፍ አይደሉም። ሁሉ በእጅና ደጅ ሆኖላቸው እንዴት ይሄን የሚል የሞራል ልዕልና ያገኛሉ? … ኧረ በጭራሽ!…ታዲያ ማነው ይሄን ያለው?
ተስፋዬ ጌታቸው ይባላል። የአማራ ክልል የካቢኔ ፣ የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሐላፊ ነው። ሌላኛው ደግሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት ልዩ አማካሪ “ማንትሴ” ጥሩነህ ይባላል። ከይቅርታ ጋር ” ማንትሴ” ያልኩት ስሙን ማንበብ ስላልቻልኩ ነው። ከላይ የተገለጠውን እውነታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያፍረጠረጡ ብአዴኖች ናቸው።
እነዚህ ብአዴኖች በሕውኃት እቅፍ ውስጥ ሆነው ይሄን መሬት የረገጠ እውነት ለመናገር መድፈራቸው ሊበረታታ ይገባል። እንደ እውነቱ ከሆነ ጋዜጠኛውን ጨምሮ አንዳች ሂሳብ ሳይሰሩ ግልጥልጥ አድርጐ ማሳየታቸው በአርአያነት ሊታይ የሚችል ነው።ከሩቅ ሆኖ ሊከፍሉ የተዘጋጁትን ዋጋ ከወዲሁ መገመት ይቻላል።
እርግጥ የህዝቡ እምቢተኝነትና የተዳፈነ ቁጭት ተናጋሪዎቹን ወደዚህ ውሳኔ እንዳመራቸው ከጥያቄ የሚገባ አይደለም። የተዳፈነ ህዝባዊ ቁጣ በበረታ ቁጥር ህውሓት `ብአዴን` በሚባል የልጥ ገመድ ያሰራቸው አማሮች ገመዱን መበጣጠሳቸው የማይቀር ሐቅ ነው።
እነዚህ ሁለት የብአዴን ካድሬዎች ያቀረቡት ማስረጃና ምሬት በጥሞና ለተከታተለው ብዙ ምላሾችን ይሰጣል። እንድምታዎቹም ብዙ ናቸው። የበላይ ባለስልጣናት እንደመሆናቸው መጠን የፌዴራሉ መሥሪያቤቶች መረጃ ይደርሳቸዋል። ለምሳሌ የመብራት ሐይል ባለሥልጣን ባለፋት አራት አመት ብቻ 92 ማከፋፈያ በኢትየጵያ ደረጃ ሰርቷል። እ•ኤ•አ• በ2015 ብቻ የተሰሩት ሃይል ማከፋፈያዎች 45 ያህል ይሆናሉ። ይሁን እንጂ የአማራ ንግድ ቢሮ ሐላፊው እንደገለፀው ላለፋት አስር አመታት በአማራ ክልል አንድም ማከፋፈያ አልተገነባም። የገዱ አንዳርጋቸው ልዩ አማካሪ እንደገለጠው ከሆነ ደግሞ የተሰሩት ማከፋፈያዎች በደርግ ጊዜ ተገንብተው ያረጁና ከጥቅም ውጭ የወጡ ናቸው። ይሄን እውነት መስማት በጣም ያሳፍራል።
ሁለቱ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት የሚያውቁት ሌላም እውነት አለ። ህውሃት እድሜውን ለማራዘም እና የገባበትን የውጭ ምንዛሪ ማነቆ ለማስተንፈስ የአገሬውን ህዝብ በኤሌክትሪክ እጦት እያሰቃየ ለጅቡቲ፣ ሱዳን እና ግብፅ ከ3,300 ሜጋ ዋት በላይ ለመሸጥ ዉል ተፈራርሟል። ግብፅ ብቻ ከ2ሺህ በላይ ሜጋ ዋት ለመውሰድ አሰፍስፋ እየጠበቀች ነው። በሌላ በኩል አቶ አርከበ እቁባይን የፈረንጅ ላም ሆነው እያገለገሉ ያሉትና የኢንዱስትሪ ፓርክ የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ቁምሳጥኖች የኤሌክትሪክ ያለህ እያሉ ነው። የባህርዳሩ፣ የኮምቦልቻው እና የጐንደሩ ቁምሳጥኖች ከ934 ሜጋዋት በላይ እንደሚያስፈልጋቸው ለክልሉ መስተዳድርና ለኤሌክትሪክ ባለሥልጣን መስሪያቤት አቅርበዋል። እናም እነዚህ የክልል ባለስልጣናት ቢጨንቃቸው ለዘመናት ተሸክመው የኖሩትን እውነት አፍረጠረጡት። አይደለም የኢንዱስትሪ አብዬት የዩንቨርስቲ ተማሪዎችን ዳቦ ጋግሮ ለማብላት የሚያስችል ኮረንቲ እንደሌለ ይፋ አደረጉ። እንጅባራ እና ወልዲያ ዩንቨርስቲ ልጆቻቸውን የሚልኩ ቤተሰቦች ልጆቹ በጠኔ ሊጐዱ እንደሚችሉ በእጅ አዙር አሳወቁ። መቼስ ለወላጆች ይሄን መርዶ ከመስማት በላይ ውርደት የለም። ለብአዴኖቹ ባለስልጣናትም ይሄን መራር ሐቅ የኢትዩጵያ ህዝብ እንዲያውቅላቸው ከማድረግ ውጭ ጊዜያዊ አማራጭ የለም።
” የትናንትናን በደል ለዛሬ በቀል”
ህውሃቶች ትናንት በትግራይ ላይ የተለየ በደል ተፈፅሟልና የዛሬው የኢኮኖሚ ኢፍትሐዊነት ትክክለኛው የአፀፋ ምላሽ ነው ብለው ያምናሉ። በሌላ በኩል የትግራይ ሕዝብና ትግራይን ትናንት የበደለ ዛሬ መበቀል እንደሚገባ የፀና እምነት አላቸው። ለዚህም ነው በአፈ ቀላጤያቸው ሐይለማሪያም ደሳለኝ አማካኝነት የትግራይን ብድራት ለመቶ አመት ከፍለን አንጨርሰውም በሚል አሳፋሪና አስቀያሚ ይዘት እንዲገለጥ የተደረገው። የሐይለማርያም የልብ ድንዛዜ፣ ከይሉኝታ መሰናበትና የኃፍረትን የመጨረሻ ድንበር መጣስ ወደ ጐን ትተን ለትግራይ የተደረገውን ብንመለከት ንግግሩ ወደ ተግባር መቀየሩን እንመለከታለን። አንድ ምሳሌ ብቻ ላንሳ ። ወጋችን ከኤሌክትሪክ ሐይል ጋር የተያያዘ በመሆኑ ምሳሌውም ከዛው ጋር ይዛመዳል።
ወቅቱ ” በጦርነት ለተጐዱ ክልሎች ልዩ ጥቅም መስጠት” የሚል ግልፅ ፓሊሲ ተቀርጾ ወደ ስራ የአተገባበር ነበር። ሁሉም የመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚቀርጿቸው ፕሮጀክቶች ማእከላዊ መገምገሚያ ምን ያህል በጦርነት የተጐዱ አካባቢዎችን በእቅዳቸው አማክለዋል የሚል ነበር። ከእነዚህ መንግስታዊ ድርጅቶች ውስጥ የኢትዮጵያ መብራት ሐይል ባለሥልጣን አንዱ ነበር።
መብራት ሐይል ከቀረፃቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ ” የትግራይ ክልል የሐይል ፕሮጀክት” የሚል ይገኝበታል። ፕሮጀክቱ መስመሩ ከየት ተነስቶ ፣ በየት አቋርጦ ፣ የት እንደሚደርስ በኤክስፐርቶች እና የባለስልጣኑ መስሪያቤት ሐላፊዎች በቴክኒክና ኢኮኖሚ አዋጭነት መስፈርት ተጠንቶ ቀረበ። ሙያተኞቹ መስመሩ ከባህር ተነስቶ በጐንደር አድርጐ መቀሌ ቢዘልቅ ከቴክኒክ እና ኢኮኖሚ አዋጭነት አንፃር ይጠቅማል የሚል አስተያየት አቀረቡ።
ፕሮጀክቱ የቀረበለት አቶ መለስና የሕውሓት ፓሊት ቢሮ ተበሳጩ። ከህውሃቶች በላይ ህውሃት መምሰል የሚፈልገው ጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ የበለጠ ተበሳጨ። የመብራት ሃይል ስራ አስኪያጅ የነበሩትን ዶክተር ወልደጊዮርጊስ ወልደገብርኤል ጨምሮ ሌሎች የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሃላፊዎችን ጠራርገው አባረሩ። ” የትግራይ ክልል የሃይል ፕሮጀክት” በመባል የሚታወቀውን የግንባታ ፕሮግራም ስሙን ” የሰሜን ኢትዮጵያ ፓወር ትራንስሚሽን ፕሮጀክት” በሚል እንዲቀየር ተደረገ። ስሙን “ትግራይ” ከሚለው ወደ ” ሰሜን ኢትየጵያ ” መቀየር ያስፈለገው የፓለቲካ ኪሳራ እንዳያመጣ በማሰብ ነበር።
መስመሩ ከየት ተነስቶ ፣ በየት አቋርጦ፣ የት ይድረስ የሚለው ተቀየረ። የጐንደር መንገድ በወሎ ወልዲያ እና ቆቦ ተተካ። መነሻውን ባህርዳር አድርጐ ወልዲያ፣ ከዛም ቆቦ፣ ከዛም መቀሌ ላይ ባላ እንዲሰራ ተደረገ። የመቀሌው አንደኛው ባላ ወደ አዲግራት ሲያዘግም፣ ሌላኛው ደግሞ አድዋ፣ አክሱም ፣ ውቅሮ፣ እንዳስላሴ አድርጐ እስከ ሽራሮ እንዲዘልቅ ተደረገ። የኢትዮጵያ ዋልታና ማገር የተባለችው ጐንደር በሕውኃት አይን የኤሌክትሪክ ምሶሶ መሸከም የማትችል ሆነች።
“ከትግራይ ክልል” ወደ “ሰሜን ኢትየጵያ” የተቀየረው ፕሮጀክት ያስመዘገበውን ውጤት ብንመለከት የስያሜው ለውጥ ፓለቲካዊ እንደነበረ በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።ለምሳሌ ከኃይል ፕሮጀክቶቹ ተጠቃሚ ከሆኑ 21 ከተሞች ውስጥ 17 ያህሉ የትግራይ ከተሞች ሆኑ። (አዲሱን የፕሮጀክት ካርታ እና የከተሞች ዝርዝር ለማየት አሌፍ መጽሔት ቅ3 ቁጥር 2 1986 ማየት ይችላል)።
በዚህ ” የሰሜን ኢትዬጲያ ፓወር ትራንስሚሽን” በሚለው የአፍሪካ ልማት ባንክ ብድር በተሰራው ፕሮጀክት ባስገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል በመቀሌ ዛሬ 8 ቢሊዬን ብር ካፒታል ያለው መሶቦ ሲምንቶን፣ ከ6 ቢሊዬን ብር በላይ ያለው መስፍን ኢንዱስትሪያል ተገነባ። አዲግራት መዳኒት ፋብሪካውን ፣ አድዋ አልመዳ ጨርቃጨርቅን ፣ ውቅሮ ሳባ ቆዳ ፋብሪካን… ወዘተ ያለምንም ጭንቀት መገንባት ቻሉ።
እንግዲህ የአማራ ክልል የንግድ ቢሮውም ሆነ የፕሬዝዳንቱ አማካሪ የመጣው ይምጣ በማለት በሕይወታቸው ፈርደው እውነታውን ያፍረጠረጡት ከላይ የተገለፀውን ታሪካዊ በደል ስለሚያውቁ ይመስለኛል ። ትግራይ ደርሰው በመጡ ቁጥርና ከጓደኞቻቸው ጋር ልብ ለልብ ሲነጋገሩ የህዝባቸውን መቆርቆዝ፣ የብዝበዛና የጭቆና ኢላማ መሆን ሲመለከቱ አይናቸው ደም ስለሚቀላ ነው። ሊወለድ የተቃረበው ህዝባዊ አመፅ እነሱንም እንዳይበላቸው በማሰብ ነው። ለዚህም ይመስላል እየደረሰብን ያለው ኢፍትሐዊነት የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅልን እናደርጋለን እስከማለት የደረሱት።

Friday, July 14, 2017

መለስ ዜናዊ እና ገዱ ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? ጸረ አማራዉ ገዱን የአማራ መሪ ነዉ ብሎ የሚቀበል ስነልቦና ያለዉ ተቃዋሚ ሊሆን እንዴት ይችላል?



ሸንቁጥ አየለ
ሰሞኑንም ገዱ ከስልጣን ሊነሳ ነዉ የሚባል ዜና ይሁን ምን በገዱ አፍቃሪዎች እየተነዛ ነዉ::የሚያሳፍረዉ ደግሞ የገዱ ከስልጣን መነሳት የአማራን ህዝብ ጥቅም ይነካል የሚል አሳፋሪ መልዕክት ማሰራጨታቸዉ ነዉ:: እነ ገዱን ልክ የተቃዉሞዉ ጎራዎች በማድረግ እና የህዝብ መብት ተቆርቋሪዎች በማስመሰል የሚቀርበዉ ትንተና አላማዉ ግልጽ ነዉ::ህዝብ ማጃጃል ብሎም ከተቻለም ትግሉን ወደ እነ ገዱ በመቀንበብ እነገዱ የትግሉን ክር እንዲጨብጡት ማድረግ ነዉ::


ለመሆኑ ይሄ ገዱ የሚባል የአማራ ህዝብ ጠላት ስንት ጊዜ ነዉ ከቦታዉ የሚነሳዉ ጃል?
ለመሆኑ ከገዱ የተሻለ የወያኔ አሽከር የሚሆን ሰዉ ወያኔ በመላዉ አማራ ህዝብ ዉስጥ ፈልጎ ያገኝ ይሆን ወይ?
በአንድ አመት ዉስጥ እንኳን አሁን ገዱን ከስልጣን ሊያነሱት ነዉ ሲባል እኮ አስረኛ ጊዜ ነዉ::ገዱ መጀመሪያም: አሁንም ወደፊትም የአማራ ህዝብ ጠላት ነዉ::
እናም ገዱ የሚባለዉ ሙት የብአዴኖች ራስ ወያኔ እስካለ ድረስ ለዉለታዉ ሁል ጊዜም ስልጣን ያገኛል::የአማራን ህዝብ እንዲያስገድል የክልሉ ዋና : ወይም ሌላ ስልጣን ይኖረዋል::ይሄ ሰዉ መደቡ እና አገልጋይነቱ ከጠላት ወያኔ ጫማ ስር መሆኑን የሚዘነጋ ጤናማ ኢትዮጵያዊ በተለይም ጤናማ አማራ አንድም የለም:: በወያኔዎች አይን የወያኔዎችን የተንጋደደ ጫማ ያህል ዋጋ ያለዉ ሰዉ ቢሆንም መደቡ ግን ያዉ የወያኔ አሽከር ብሎም የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነዉ::
የወያኔ መሳሪያ በመሆን አማራዉን ያስገደለ : እንዲፈናቀል የተስማማ: አማራ መጤ ነዉ ሲባል አብሮ ያጨበጨበ: የኢትዮጵያ ብሄሮችን አማራ በቅኝ ገዥነት ይዟቸዉ ነበር ብሎ ህዉሃት ሲሰብክ የተስማማ ሁሉ የአማራ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ነዉ::
ገዱ ደግሞ ይሄን ሁሉ አድርጓል:: አማራን የሚያህል ህዝብ ግንባር በምታክል ክልል ላይ ተወስኖ እንዲኖር: ከመላ ኢትዮጵያ እንዲፈናቀል ያደረገ ገዱ እንጂ ሌላ ማን ነዉ? አማራ በመላ ሀገሪቱ መጤ ሲባል እና ከአባቶቹ ሀገር ላይ እንዳይኖር ሲፈረድበት የተስማማ ገዱ የሚባል ጸረ አማራ እንጅ ሌላ ማን ነዉ? ገዱ በአማራ ህዝብ ላይ የሰራዉን የጠላትነት ስራ ወያኔ: ሻዕቢያ እና ኦነግ በጋራ የሰሩትን ያክላል:: ከተገለጹት የአማራ ህዝብ ጠላቶች በላይም የአማራ ህዝብ ጠላቶች አማራን አማራ መስለዉ የሚያስጠቁት ናቸዉ::
ጸረ አማራዉ ገዱን የአማራ መሪ ነዉ ብሎ የሚቀበል ስነልቦና ያለዉ ተቃዋሚ ሊሆን እንዴት ይችላል?
ከዚሁ ከገዱ ከስልጣን መነሳት ጋር በማስታከክ አቶ አያሌዉ ጎበዜ የሚባለዉን ጸረ ህዝብም አብሮ የማሞገስ አጀንዳ ተያይዞ መራገብ ጀምሯል:: ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ የሚባሉ ጸረ ህዝቦችን ከብአዴን የሙታን ስብስብ ዉስጥ መዞ በማዉጣት እነሱ ልዩናቸዉ ማለት ምን ማለት ነዉ? እነሱ ለክልሉ ብዙ ሰርተዋል ማለት ምን ማለት ነዉ? አማራ ክልልን በደንብ ጠንቅቀን ለምናዉቅ ሰዎች ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ በክልሉ ስራ ሰርተዋል ብሎ የሚያወራ ሰዉ በጣም ያናድደናል ብቻ ሳይሆን መራራ ስሜትን በዉስጣችን ያጭርብናል::
አማራ ክልል ላይ ምንም የተሰራ ስራ የለም::ሰዉ ከመግደል እና ከማሳረድ በቀር::ገዱ ልዩ : አያሌዉ ጎበዜ ልዩ የህዝብ ወገን ናቸዉ ብሎ መናገር ምን የሚሉት ህዝብ የማሞኘት ስልት ነዉ::
ሌላዉ ቀርቶ አማራ ክልል ላይ የተራቡ ሰዎች እንኳን እርዳታ አግኝተዉ በልትዉ ነብሳቸዉ እንዳይተርፍ ቀጥተኛ መመሪያ የሚሰጠዉ ልዩ ሰዉ የተባሉት ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ ናቸዉ::ሲጀምር የባንዳ ልዩ የለዉም::ሁሉም ባንዶች ስነልቦናቸዉ አንድ ነዉ::ወያኔን ሊያገለግል የገባ: የኢትዮጵያ ታሪክ መቶ አመት ነዉ ሲባል የተስማማ: አማራ ወራሪ ነዉ ሌላዉን ኢትዮጵያዊ ቅኝ ገዝቷል ሲባል የተስማማ: የኢትዮጵያን ህዝብ በጎሳ ለማባላት አብሮ ከወያኔ ጋር የሮጠ ሁሉ ጸረ ህዝብ ነዉ::
ምንም የተለዬ ነገር የለዉም:: በወያኔ የደም መርዝ አብሮ ጭብጦዉን አብኩቶ በስልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ብሎ በዉስኪ እየተራጨ ህዝብን በርሃብ: በስደት: በልዩነት: በጥላቻ: በፍትህ እጦት የገደለ እና ያስገደለ ሁሉ ባንዳ ነዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ:: ገዱ የለ: አያሌዉ ጎበዜ የለ እንቶኔ የለ::ሁሉም አንድ ነዉ::እነዚህ ናቸዉ አይደለም ኤርትራን ቆርሰዉ የሸጡት? እነዚህ ናቸዉ አይደለም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርስ የሚያባሉት? እነዚህ ናቸዉ አይደለም አማራ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠዉ የዘር ማጥፋት የሚፈጽሙበት? እነዚህ ናቸዉ አይደል የቀደሙ ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የሰሩትን ሁሉ የናዱት?
እነዚህ ናቸዉ አይደለም እንዴ በመላዉ ኢትዮጵያ የሰበአዊነት ረገጣ ሲደረግ እና ህዝብ ሲታረድ እየወጡ ህዝብ አልተገፋም እያሉ መግለጫ የሚሰጡይት? እነዚህ ጠላት ካልተባሉ ማን ሊባል ነዉ? ታዲያ አማራ ህዝብ ላይ ጣሊያን መጥቶ የዘር ማጥፋት አልፈጸመበት::ወይም ወያኔ አማራን ብቻዉን አለ ብአዴን ሙታን ሰዎች ድጋፍ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ አላደርገዉ:: እኮ ታዲያ ወያኔ እና ብአዴን ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? አንዱ በትግሬ ስም መነገዱ ሌላዉ በአማራ ስም መነገዱ መሆኑ ነዉ ልዩነታቸዉ? መለስ ዜናዊ እና ገዱ ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? እነዚህ ሁሉ ጸረ ህዝብ ናቸዉ:: ጸረ ኢትዮጵያዉያን: ጸረ አማራ በአጠቃላይ ጸረ የሰዉ ልጅ::
ወያኔ በትግሬ ስም ብአዴን የሚባለዉ ሙት ደግሞ በአማራ ስም መነገዳቸዉ ወይም ተደራጀን ማለታቸዉ ምንም ልዩነት የለዉም::ቁም ነገሩ ከሚሰሩት ስራ ላይ ነዉ:: አንድ ቡድን ወይም አንድ አካል ምን ይሰራል ? ወይም ምን ሰራ ነዉ ጥያቄዉ? እዉነትና ፍትህን ያራምዳል ወይስ ሀሰት: ሸፍጥ: ተንኮል: እና ጥላቻን ይፈጽማል?ግፍን: ኢሰበአዊነትን እና ኢዲሞክራሲያዊነትን ይሰራል ወይስ ሲሰራ ይተባበራል ነዉ ጥያቄዉ:: የስራም የተባበረም ያዉ ነዉ::ግፈኛ እና ጸረ ህዝብ ነዉ::
መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ትዉደም የሚል መጽሀፍ ሲጽፍ: ወይም አማራ ይታረድ የሚል መመሪያ ሲያስተላለፍ በዋናነት አንጋች እና ጎታች ሆነዉ ፈጻሚ እና አስፈጻሚ ሆነዉ የሚሰለፉት እነ አያሌዉ ጎበዜ እና እነ ገዱ ብሎም እነሱ የሚመሩት ብአዴን የሚባለዉ ስብስብ ከመለስ ዜናዊ በምን ይለያሉ? በምንም አይለዩም:: በህዝብ ላይ መቀለድ ይቁም::ገዱም : መለስም አንድ ናቸዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ ካምፓቸዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ ጎራቸዉ::የጸረ ህዝብ ልዩ የለዉም::ምድቡ እዚያዉ ጸረ ህዝብ ነዉ::