Tuesday, June 6, 2017

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን እናውቀዋለን፣ ዘመነ ካሴን እናውቀዋለን፣ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋውንም እናውቀዋለን እናንተ ግን ማን ናችሁ?




ጌታቸው በቀለ | የጉዳያችን የጡመራ ገጽ አዘጋጅ

ርኩስ መንፈስን “በኢየሱስ ስም” እያሉ ሊያወጡት ሲሞክሩ መንፈሱ “ኢየሱስን አውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ማን ናችሁ?” አላቸው።የሐዋርያት ሥራ 19፣15

==================
ሰሞኑን በኤርትራ በትግል ላይ የነበረው አርበኛ ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ወጥቶ ሌላ ሀገር ሕክምና ላይ መሆኑን ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በፌስ ቡክ ገፁ ገለጠ። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም በሎስ አንጀለስ ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ላይ በነበረ ሕዝባዊ ስብሰባ ይህንኑ ከጋዜጠኛ ሙሉ ቀን ቃል ጋር የማይጋጭ ቃል ተናገሩ። ጋዜጠኛ ሙሉ ቀን ስለ አርበኞች ግንቦት 7 አንዳች የሚነቅፍ ቃልም ሆነ ስም ጠርቶ የተናገረው ነገር የለም።ጋዜጠኛው በተለያዩ መድረኮች እንደምናገረውም ሆነ በተለያየ አጋጣሚ ሲናገር እንደማውቀው እጅግ ቁጥብ፣ማንንም ክብር የማይነካ እና ለሁሉም የተቃዋሚ ኃይል ክብር የሚሰጥ ነው።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋም ሆኑ ድርጅታቸው እስካሁን በድርጅት መግለጫ መልክም ሆነ በየትኛውም መድረክ የእከሌ ብሔር እንዲህ ነው ወዘተ የሚል ሕዝብ የሚያስቀይም ንግገር ሲናገሩ አልሰማሁም።ታጋይ ዘመነ ካሴም በለቀቀው ቪድዮ ላይ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ላይ ያለውን ክብር ገልጦ በሙሉቀን የተጀመረው የገንዘብ ማሰባሰብ በእርሱ እውቅና መሆኑን ገልጧል። እነኝህ ዜናዎች ሁሉ ላይ አንዳችም የእርስ በርስ መቃረን አይታይም።ታጋይ ዘመነ ነገ የትግል ስልቴ ይህ ነው ብሎ አዲስ ሃሳብ ቢያመጣም (አመጣ ሳይሆን ያልኩት ቢያመጣም ነው) መብቱ ነው።ይልቁንም አርበኞች ግንቦት 7 አንድ አባሉ ያውም በኮማንደር ደረጃ ያለ አባሉ የፈለገውን መንገድ እንዲመርጥ በማክበር ምርጫውን በመስጠቱ ሊመሰገን ይገባዋል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች ታሪክ አንድ አባል የእራሱን ምርጫ ቢመርጥ አይደለም ገና ለገና ከድርጅቱ ሊወጣ ያስባል የሚል ጥርጣሬ ካለ የሚወሰደው እርምጅ ምን እንደሆነ የቅርብ ድርሳናትን ማገላበጥ በቂ ነው።
ባጭሩ ምን ለማለት ነው የፈለኩት?
ሰሞኑን ጋዜጠኛ ሙሉቀን ያላለውን፣አርበኞች ግንቦት 7 ያልሆነውን አለ እና ተደረገ እያሉ የሚፅፉ እና በተለያየ የስውር ስም (anonymous) እየተጠቀሙ ወሬ ሲነዙ የነበሩ እነማን ነበሩ? የተሳሳቱም ካሉ ሳያጣሩ በመናገር እነማን አሳስተውብን ይሆን? ብሎ መጠየቅ ብልህነት ነው። ይህ የዘመነ ካሴ ጉዳይ ለተቃዋሚ ጎራ አንድ አስተማሪ ጉዳይ ነው። በስውር ስም (anonymous) ፌስ ቡክ ስም የተፃፉ መልዕክቶች እንደ ዜና ምንጭ እያደረግን ለሌሎች የምናካፍል ጥንቃቄ እናድርግ።በስውር ስም ሳይሆኑ በስማቸው እየፃፉ ነገር ግን ትንሽ ጫፍ ይዘው የነበሩበት ለማስመሰል አንድ ገፅ የሚፅፉም ትዝብት ላይ እየወደቁ መሆኑን ቢረዱት ጥሩ ነው።ለጊዜው ግን ማለት የሚቻለው – ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን እናውቀዋለን፣ዘመነ ካሴን እናውቀዋለን፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሙሉቀን ተስፋውንም እናውቀዋለን እናንተ ግን ማን ናችሁ?
“ኢየሱስን አውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተ ደግሞ ማን ናችሁ?” አላቸው።የሐዋርያት ሥራ 19፣15

Monday, June 5, 2017

በጎንደር ቅዳሜ ሌሊት የተኩስ ልውውጥ ነበር | የኢትዮጵያ ህዝብ ለወሳኙ ትግል ጥሪ ቀርቦለታል



File Photo
ከሙሉነህ ዮሐንስ
በሰሜን ጎንደር በሁለት ግንባር የጎበዝ አለቆች ላይ የከፈተው የማጥቃት እርምጃ የከሸፈበት ወያኔ ብዛት ያለው ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው እየላከ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ቅዳሜ ሌሊትም አንድ ግንባር ላይ የጋለ የተኩስ ልውውጥ ነበር። በወገን ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። የወያኔ ወታደር ግን እየደነበሩ ወደ ገደል መግባታቸው ታውቋል።
ስለሆነም ህዝቡ ይህን ወያኔ የከፈተበትን የእብሪት ጦርነት አውቆ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስድ ከግንባር መልእክት ተላልፏል። ሰሞኑን ተቋርጦ የነበረው ኢንተርኔት በመጠኑ ተለቋል።
ወያኔ ጎንደር ላይ ብዛት ያለው ወታደር እያከማቸ መገኘቱ በህዝባችን ላይ ጅምላ ፍጅት እስከማድረግ ስለማይመለስ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ። ለኢትዮጵያ ህዝብ ድምፅ የሆነው አመት ሙሉ ከባድ ተጋድሎ እያደረገ ለሚገኘው የጎንደር ህዝብ ከሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኳይ ድጋፍ መደረግ አለበት።

Saturday, June 3, 2017

በአዳማ ከተማ 80 የሚደረሱ የህዝብ ሱቆች በእሳት ቃጠሎ መውደማቸው ተዘገበ።

    



በአዳማ ከተማ 80 የሚደረሱ የህዝብ ሱቆች በእሳት ቃጠሎ መውደማቸው ተዘገበ።
በአዳማ ከተማ አውቶብስ መናሪያ አከባቢ በተለምዶ ፍራንኮ ገበያ በምባል በምጠራ ቦታ በተነሳ እሳት ቃጠሎ እሰከ 80 የምደረሱ ሱቆች በትላንትናው እለት እንደ ወደሙ ምንጮች ለራዳሃ ገለፁ።
ይህ የእሳት ቃጠሎ የደረሰው ትላንት ማታ ከ4 ሰዓት ጀምሮ አሰከ ጠዋት የቆየ ስሆን አስከ አሁን በደረሰን ዘገባ የእሳቱ መንስኤ ምን እንደሆነ ያልታወቀ ስሆን በመንግስት በኩል እሳቱን ለማጥፋት የተደረገ እገዛ እንደለለ እና እሳቱን የምያጠፋ ውሃ 30ኪሜ ከብሾፍቱ ከተማ በማምጣት እንደነበረ ገልፀውልናል።
ምንጮቻችን እንደገለፁ አንድ የኦሮሞ ባለ ሀብት ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የምገመት ንብረት የወደመበት ስሆን በአዳማ ከተማ የምኖሩ ህዝቦች እሳቱን ለመቆጣጠር እሰከ ንጋቱ ድረስ ከባድ ጥረት እያደረጉ እንደነበር ተገልፀዋል።
ይሄን ዘገባ የላከልን ምንጭ እንደምለው የምያሳዝነው ንገር ብኖር በእሳት ከወደመው ንብረት በላይ መኪና አቁመው ሱቁን በመሰበር ንብረትን በመኪና በመጫን የነበሩ ዘራፍዎች ናቸው ያሉትና የሰላም አስከባሪ ሀይል በቦታው አለመገኘት ህዝቡን የበለጠ እነደቆሰለ ምንጮቻችን ገልፀዋል።
የወደመው ንብረት ባለ ሃብቶቹ በህጋዊ መንገድ ግብር ለመንግስት እየከፈሉ እንደነበር ምንጮች ዘግበዋል።
ምንጮች እንደገለፁ የቃጠሎ አደጋ የደረሰው የሙስልም ሱቆች በብዛት ባሉበት ቦታ እንደሆነና ሙስልሞች ለተራዊህ ሰላት ሱቆቹን ዘግተው በነበረበት ወቅት መሆኑ ተዘግበዋል።
መንግስት የብሄራዊ ፈተና ሰበብ በማድረግ ኔትወረክ መዝጋቱ ይታወቃል።
በመንግስት በኩል እስከ አሁን ባገኘነው ዘገባ ምንም የተደረገ እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀውልን ከእሳት ቃጠሎ በኌላ በሀገር ውስጥ ኔትወርክ መዝጋቱ ለምን እንዳስፈለገ እውነት ለብሄራዊ ፈተና ነው ? የምል ጥያቈን አጭሩዋል.
መንግስት ይህን እሳት ለማጥፋት ያደረገዉ እነቅስቃሴ የለም ማለት ይቻላል በተጨማሪም ዘራፍዎች መኪና በማቆም ዘረፋ ሲያካሄዱ ሰላም አሰከባሪዎች በአከባቢው ለምን አልተገኙም?የምሉ ጥያቄዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ተነስተዋል በማለት ዘግበውልናል።

Friday, June 2, 2017

የትግራይ በልማት መጎዳት ነገር.. አሳ ጎርጓሪ… | ከሃብታሙ አሰፋ



<<ትግራይ በልማት ወደሁዋላ ቀርታለች!>> የሚለው የሰሞኑ ለቅሶ አንዳንዶች የተዘጋ ፋይል በግድ እንዲከፈት እየጎተጎቱ ይመስላል።ስርዓቱ ፍትሐዊ አይደለም ሲባል የአማራው እንግዳ ቡድንን ባህርዳር ከነማን <ካልገደልን> ብለው በአስለቃሽ ጭስ የተበተኑት የትግራይ ልጆችና በሰላማዊ የእሬቻ ሀይማኖታዊ በዓል ላይ እጃቸውን ወደ ላይ ለሰላማዊ ተቃውሞ ባመሳቀሉ ላይ ጥይት ማርከፍከፍንም ይጨምራል።ዜጎች እኩል ሊታዩ ይገባል ለማለት ነው። አንዱ አላግባብ የሚገደል መሆን የለበትም።

አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
የሰሞኑ የትግራይ በልማት ወደ ሁዋላ ቀርታለች፣ በፌዴራሉ መንግሰት ተበድላለች አይነት ለቅሶ በበጀት ዋዜማ መሆኑ ብዙ የተዘጉ ፋይሎች እንዲከፈቱ ያበረታታ ይመስላል። ለመሆኑ ትግራይ ከማን ጋር ተወዳድራ ነው ወደ ሁዋላ የቀረችው? ከአሜሪካ ወይስ ከስዊዘርላንድ? መቼም ከአማራ፣ከኦሮሚያ፣ከሱማሌ፣ከደቡብ ወዘተ እያላችሁ በማስረጃ እንደማትሞግቱን ተስፋ አደርጋለሁ። ትግራይን ጨምሮ ሁሉም የአገሬ ሕዝቦች የሚኖሩበት ቦታ በልማት ቢያድግ እመኛለሁ። ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ትግራይ እንደ እናት ልጅ ሌላውን አንዳንዱን እንደጠላት የቀረውን እንደ እንጀራ ልጅ የሚያይ ስርዓት <<የፌደራል>> የሚል ታርጋ ስለተለጠፈለት እንውቀሰው ካላችሁ ለምን ለትግራይ ክልል አደላ በሚል ካልሆነ << ጩኸቴን ቀሙኝ>> አይነት የሰሞኑ ለቅሶ ውሃ አይቋጥርም።
የአንድ አገር ብሄራዊ ዳቦ (በጀት) ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት እንዴት ሲከፋፈል እንደነበር፣ተሰርቆም፣ተለምኖም የመጣው ሁሉ በአድልዎ አንዴት ለትግራይ ክልል ቅድሚያ በሚል ይሄድ እንደነበር ብዙ ማስረጃ መዘርዘር ይቻላል።<<ይሄ ሁሉ ተግዞ የትግራይ ክልል ከሌላውም አፍ እየተቀማ ተወስዶ ያን ያህል አልተጠቀመም!>> የሚል ቅሬታ የሚያቀርብ ቢኖር ፍትሐዊ ያልሆነውን ስርዓትና አመራር መደገፉ አንድ ነገር ሆኖ ጆሮ ገብ ስሞታ ሊሆን ይችል ይሆናል።
በየዓመቱ የአገሪ በጀት ይደለደላል። የበጀት ስሌቱን ዛሬ <<ትግራይ ተደብላለች>> የሚሉት እንዴት እንደተሰራ መለስ ብለው ቢያዩት እንመክራለን።በአጭሩ ሕወሃት በሚቆጣጠረው የፌዴሬሽን ም/ቤት ከየክልሉ ለም/ቤቱ በተወከሉ ፖለቲከኞች የበጀት ድልድሉ ቀመር ይጸድቃል። ባለፉት ሃአ ስድስት ዓመታት፡ኢሄ ድራማ እንደቀጠለ ነው። መጀመሪያ በጦርነት የተጎዱ ክልሎች ልዩ ድጎማ ይሰጣቸዋል ተባለ።በዚህ ሒሳብ ከአቅሟ በላይ( በጀት ስሌቱን ይሄን ታሳቢ ያደረገ በማድረግ) ተቀም ያለ በጀት ለትግራይ ተደጋግሞ ተሰጥቷል።
ከዛሬ 13 ዓመት በፊት አንድ ቀን ለዘገባ ወደ ፓርላማ ስሄድ በአጋጣሚ በሌላ አዳራሽ የጦፈ ክረክር መኖሩን አንዱ አባል ሹክ ይለኛል። ጉዳዩን ለመስማት <<የሕዘብ ተወካዮች>>(እነሱ የሚጠሩበት ስም ስለሆነ ይቅርታ) የፓርላማ አባላት ተብዬዎቹን ስብሰባ ተውኩና በዚያው በፓርላማ ጊቢ አጠገቡ ወደሚገኘው የፌዴሬሽን ም/ቤት ገባሁ።እነዚህ ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት በቀጥታ ከክልሉ ተወክለው የሚመጡ በመሆኑ ብዙዎቹ የየክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ናቸው። የዕለቱ ውይይት የበጀት ቀመር ስሌቱ ላይ ለመወሰን ነበር። ይሄ ደፋር ም/ቤት በአገሪቱ በጀት ስሌት ላይ ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግስቱም ላይ ፈራጅ ነው። ዳኞች በግልጽ ለሚያዩት ሕገ መንግስቱን የጣሰ ክስም ሆነ አቤቱታ <<ይሄ ሕገመንግስታዊ አይደለም >>የሚል ቅሬታ ሲቀርብ ወዲያው ወደዚህ ም/ቤት ይልካሉ፤ይሄ ም/ቤት ከአልሆነ ሌላ ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የለውም። ለበጀት ድልደላው መሰረት የሆነውም ቀመር የሚወሰነው በዚህ ም/ቤት ነው:፡ ታዲያ በዚያ ዕለቱ ስብሰባ የበጀት ቀመሩን ለመወሰን የትግራይ ክልልን ወክለው ከሚገኙት፡ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት መካከል አቶ ሐሰን ሺፋ በጊዜው የፌዴራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ፣ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይ የክልሉ ሌላ ባለስልጣን መገኘታቸው ትዝይለኛል።የአፋር እና የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንቶችም ነበሩ። የሆነው ሆኖ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው ከበጀቱ በህዝበ ብዛት ስሌት ለመቶኛ ሲካፈል በዚያም በዚህም እየተባለ ዛሬ ተጎዳች የተባለችው ከአገሪቱ ህዝብ 6 በመቶውን ምትኢዘው ትግራይ ያለ ማጋነን በአካፋ ይዛቅላታል። የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል ሆኖባቸው ነው መሰል አንዳንድ ክልሎች የበጀት ስሌቱ ቀመር አግባብ አይደለም የሚል ስሞታ በዜያ ስብሰባ ላይ ያነሳሉ።ሕወሓት ይህ መሰሉ ጥአቄ አንዳንዴ በተለያዩ ክልሎች ሲነሳ <<የትግራይ ሕዝብ ደመኞች>> እያለ በማሸማቀቅ ጥአቄውን ሲያዳፍን ቆይቷል። በዕለቱ የቤንሻንጉሉ የጊዜው ፕሬዝዳንት ያረጋል አይሸሹም እየደጋገመ በተለይ ትግራይና ቤንሻንጉልን ጨምሮ አነስተኛ ሕዝብ ያላቸው ክልሎች ለቀመሩ የሕዝብ ብዛት በመቶኛ ከፍ ብሎ ከተሰጠ እንደሚጎዱ በማስታወስ ሰፋ ያለ ዲስኩር እንዲያደርግ ተደረገ:፡ በተናገረ ቁጥር እነ ሐሰን ሺፋን እየደጋገመ ዞሮ ማየቱ ሰውዬው ከሁዋላ በሱ በኩል ሆን ተብሎ እንዲነሳ የተፈለገ አጀንዳ ለመኖሩ ግልጽ ነው። ሕወሓት እንደልቡ ከሚጨፍርባቸው ሰዎች አንዱ ያረጋል ነው። እንደልቡ ከሚጋልብበባው ክልሎች ቤንሻንጉል ክልል አንዱ ነው:፡ ቁጥር የገባቸው በመጠኑ ለማስረዳት ሞከሩ። አንዳንዶች ፈራ ተባ እያሉ የሕዝብ ብዛት በቀመር ስሌቱ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፣መሰረተ ልማት ወደሁዋላ መቅረቱን ቁጥር እያስደገፉ ለማስረዳት ሞከሩ። አጠር አጠር ያለ አስተያየት ሲሰጥ የቆየው ሐሰን ሺፋ ቆጣም ከረርም እያለ በምክር ቤቱ ያሉትን ለማሸማቀቅ እሱ የትግራይ ሕዝብ ደመኞች ያላቸውን እየጠቀሰ የቀረበውን ለሕዝብ ብዛት የበለጠ ይሰጥ የሚለውን አጣጣለ። ሕዝብ ብዛት እየተባለ ቅድሚያ የበጀት ቀመሩ ከፍተኛ ድርሻ ከያዘ በጦርነት ተጎዳችው ትግራይ ተጠቃሚ እነደማትሆን ዘረዘረ። ለይስሙላ የተደረገው ውይይት ሐሰን ሺፋ ያስረገጠበትን ሀሳብ መሰረት ያደረገ ውሳኔ ተላለፈና ተዘጋ።በዚህ ቀመር ስሌት በጀት ይመደብና <<ፓርላማው>> ሰኔ 30 ለእረፍት ከመዘጋቱ በፊት አጸደቀው ይባላል፡:
የበጀቱን ጉዳይ ያነሳሁት በአገሪቱ ሕዝብ ስም የተገኘ ገቢ፣ከብድርና ከዕርዳታ ከሚመጣው ማን የአንበሳውን ድርሻ ሲቀረጥፍ እንደኖረ በግልጽ ያሳያል ብዬ ነው። ከዚህ በተረፈ በእነ ኢፈርት ስም ከዚህ በጀት ጨምሮ ከየባንኩ የተዘረፈው፣ የመሰረተ ልማት፣የፋብሪካዎች አይነትና ቁጥር ፣በሰበዓዊነት ተግባር የመጡ መንግስታዊ ድርጅቶች ሳይቀር በአማራ፣በኦሮሞ፣በሶማሌ ሆነ በሌላ ክልል ለመስራት ያመጡትን ፕሮጀክት አጥፈው ዛሬ ተበደለች ወደተባለው ትግራይ ካላዞሩ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው እየተነገራቸው አንዳንዶች ያንን ሲፈጽሙ ጥቂቶች እየጣሉ ወጥተዋል፡፡በዚህ አድሎዋዊ ሆን ተብሎ በተሰራበት ፖሊሲ ሳቢያ ህብረተሰቡን በልማት ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ወደ አንድ አካባቢ(ትግራይ) በብዛት እንደሚገፉ ተደጋግሞ የተዘገበ ነው:፡ በእርግጥ በአማራ ክልል ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናትን ለማምከን ዘመቻ ጭምር እተደረገ የ10 ዓመት ህጻናት ሳይቀር ወሊድ መከላከያ ከለፍላጎታቸው በክንዳቸው እየተቀበረ መካን እነዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል። ህጻናት በጊዜ ክትባት አጥተው ከተወለዱት በስንት መቶኛ አንደሚሞቱ ይህም ቁጥር ከትግራይ በስተቀር በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ብዙ መሆኑን ባለፈው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ለመቃወም የራሱ ስርዓቱ ያሰራጨወን ማስረጃ ይፋ ያደረገው የአማራ ባለሙያዎች ጥናት ያሳያል።

የትግራይ ተሟጋቾች ይሄ ማለት እያንዳንዱ የትግራይ ሕዝብ ተጠቀመ ማለት ነው ተብሏል ብለው አጀንዳ ለማስቀየር ወይ ለማደናቆር ሲሞክሩ ይገርመኛል።ዛሬም ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ህጻናት ኢትዮጵያውያንን እያየን፤ በበጀቱ ዋዜማ <<በተቃዋሚ ታጋዮቹ>> አንደበት የሚደለቀው የባቡሩና በልማት ወደ ሁዋላ መቅረት ዜማ ሌላው ቀርቶ የድሬዳዋን ከተማ ሕዝብ መከራና ድህነት ያየ አይታዘባችሁም? ዛሬም በሰው ጫንቃ በምጥ የተያዘች እናት ብዙ ኪሎ ሜትሮች እየተጓዘቸ መንገድ ላይ ሕይወቱዋ በሚያልፍበት አገር፣ዜጎች በገፍ ስራ አጥ ሆነው የብሔራዊ ዳቦ ድርሻቸው በአድልዎ እየተቀማ፤ ከቆሻሻ ላይ እስከመብላት ሲደርሱ፣ቆሻሻ ላይ ኖረው በቆሻሻ ተቀብረው ሲሞቱ ይሄን ስርዓት ያቆመ ሕወሓት በበላይነት እያስተዳደረ <<ባቡር…በልማት ቀረን ተበደልን….>> ስትሉ አታፍሩም? ባይሆን ሲታደግም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ በአገሪቱ ሀብትና በእዳ ከመጣ ሀብት እኩል ካልሆነ ሌላው የበይ ተመልካች የሚሆንበት ስርዓት ለአገር አደገኛ መሆኑ እንዴት አይገለጥላችሁም? ዘንድሮ እናቱ የሞተችበትም ውሃ የወረደችበትም እኩል ያለቅሳል ሆኖ እንጂ በእውኑ በልማት የተጎዳችው ትግራይ ከየትኛው ክልል ጋር ተወዳድራ ነው? መቼም እዛ ሰፈር ማፈር ከቀረ 26 ዓመቱን አክብሯልና ዓለም አቀፉ የሒሳብ ስሌት እኛ ሳናውቀው ተቀየረ እንዴ? በሉ አንግዲህ አሳ ጎርጉዋሪ አይደል ከነተረቱ ሁሉም እንዴት እየተጎዱ እንደኖሩ ያቅሙን ይጸፍ።ፈርዶብናል እነሱ ከረሱት ማስታወስ ምን ይከፋል።

በሲያትሉ ጉባኤ በፕሮፌሰሩ የተብጠለጠለው አፄ ቴዎድሮስ ነው [ቬሮኒካ መላኩ]




… ሌላው በሲያትሉ ጉባኤ በፕሮፌሰሩ የተብጠለጠለው አፄ ቴዎድሮስ ነው ። ክሱ የሚለው ቴዎድሮስ አምባገነን ስለነበር ህዝብ ጠላው ይላል ። ፕሮፌሰሩ ከ 150 አመታት በፊት የነበረው ቴዎድሮስ “ዴሞክራት ” እንድሆን ጠብቀው ነበር መሰለኝ ። አስቂኝም አስገራሚም ነው።
በዚሁ ወቅት እኮ ስልጡን የነበረችው ፈረንሳይ ጊሎቲን የተባለ አንገት የሚቀላ ማሽን ፓሪስ አደባባይ አስቀምጣ ህዝቡን እንደ ሸንኮራ የምትቀላ አገር ነበረች ። አሜሪካ በዚሁ ዘመን አካባቢ አገሪቱን ለመገንባት በእርስ በርስ ጦርነት ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህዝቧን ቅማለች ።
እስኪ አፄ ቴዎድሮስ ከሞተ ከ50 አመታት በኋላ ስለነበረው የሩሲያ መሪ ጆሴፍ ስታሊን እናውራ ።
በ1879 ዓ.ም ጐሪ በተባለች የጆርጂያ የገጠር ቀበሌ የተወለደው ስታሊን
ከሌኒን ሞት በሁዋላ የኮሙኒስት ፓርቲውን የዋና ፀሐፊነት ስልጣን ተቆጣጠረ። ስታሊን ስልጣን ላይ እንደወጣ ተፎካካሪና ተቀናቃኞቹን የነበሩትን ስመጥር የሶቪየት ህብረት ግንባር ቀደም ታጋይ አብዮተኞች እና ህዝቡን ጨፈጨፈ ።
በ1940 ዓ.ም ትሮትስኪን ወደር በሌለው ጭካኔ ሜክሲኮ ድረስ ቅጥረኛ በመላክ በመጥረቢያ አስፈልጦ አስገደለው። በሚሊዮን የሚቆጠር ሩሲያዊ ድራሹ ጠፋ የተረፈውም ወደ ሳይቤሪያ እየተላከ በበረዶ ማጎሪያዎች ተቀፈደደ ።
ለድፍን ሠላሳ አንድ አመታት አንድ መቶ ስልሳ ሚሊዮን የሆነውን የሶቪየት ህብረትን ህዝብ ወደር በሌለው ጠንካራ የብረት ክንድ ሰጥ ለጥ አድርጎና አንቀጥቅጦ ገዛው ።
ጆሴፍ ስታሊን አምባገነን የነበረ ቢሆንም ለአገሩ የነበረው ፍቅር ወሰን አልነበረውም። ሩሲያን ከሃያላን አገሮች የፊት መስመር እንድትሰለፍ ያደረገ መሪ ነበር ። የሩሲያን ድንበር አልፎ ግዛቱ የገባውን የናዚ ጦር እንክትክቱን እያወጣ በርሊን አድርሶ የሰባበረው የጆሴፍ ስታሊን ቀይ ጦር ነው። የአለምን የሃይል ሚዛን የቀየረውን ሁለተኛው የአለም ጦርነት በማሸነፍ ሩሲያን ሃያል እና ተፈሪ አገር አደርጓል ።

የመጀመሪያ ልጁና የአብራኩ ክፋይ ያዕቆብን በሁለተኛው የአለም ጦርነት በናዚ አገሩ ስትወረር “አባትህ አገርህ ነው እንጅ እኔ አይደለሁም ” በማለት በወታደርነት ዘምቶ አባት አገር ሩሲያን ከጠላት እንድከላከል ላከው ።
ያእቆብ ከወራሪ ናዚወች ጋር ሲዋጋ በጀርመኖች ተማረከና ተገደለ ።በእነ ያእቆብና ብዙ ሺዎች ሩሲያውያን መስዋእትነት አለም ከናዚ ጭፍጨፋ ዳነች ።
ዛሬ ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ የስታሊን ሃውልት አምሮና ደምቆ ይታያል ። ሩሲያኖች መሪያቸው አምባገነን እንደነበረ እና ሚሊዮኖችን እንዳስጨፈጨፈ እያወቁም አገራቸውን ታላቅ አድርጓታል እና ያከብሩታል ።

ስታሊንን እና ሩሲያውያንንን ማንሳቴ ምኒልክ ገደለን ቴዎድሮስ ፈለጠን እያሉ ለሚነፋረቁ የኢትዮጵያ ልሂቃን አብነት የሚሆኑ ከሆነ ብዬ ነው። ቴዎድሮስ ቆረጠም ፈለጠም ከተባለ የእኛዎቹን ( የአማራ) ቅደመ አያትና ምንጅላት ነው ። ይሄን ያደረገው አገር ቀና እንድል እና እንድገነባ ነውና መይሳውን እንረዳዋለን ። ስታሊን ለአገሩ ለሩሲያ ልጁን ያእቆብን መስዋእት አደረገ አፄ ቴዎድሮስ ደሞ ለአገሩ ለኢትዮጵያ አንድ ህይወቱን ሰጠ ።

Thursday, June 1, 2017

ወንድማችን አርበኛ ዘመነ ካሤ በአስቸኳይ የእኛን እርዳታ ይሻል

By ሳተናው


አርበኛ ዘመነ ካሤ የወያኔን ዘረኛ ሥርዓት ለመዋጋት በግንባር ቀደም ከተሰለፉ ወጣቶች መካከል ነው፡፡ ሆኖም ከዓመታት በፊት በደረሰበት አደጋ የጤንነት እክል ገጥሞታል፡፡ የተሻለ ሕክምና ካላገኘ የቀኝ እጁ ሊታዘዘው አይችልም፡፡ ታጋይ ዘመነ ከዚህም በተጨማሪ የኩላሊት ሕመምም ተጠቂ ሆኗል፡፡ ከላይ በተገለጹት ምክንያቶች የተነሳ ወንድማችን በአስቸኳይ የእኛን እርዳታ ይሻል፡፡ አነሰ በዛ ሳትሉ የምትችሉትን ትደግፉ ዘንድ ወገኖቹን ይጠይቃል፡፡

These content links are provided by Content.ad. Both Content.ad and the web site upon which the links are displayed may receive compensation when readers click on these links. Some of the content you are redirected to may be sponsored content. View our privacy policy here.
To learn how you can use Content.ad to drive visitors to your content or add this service to your site, please contact us at info@content.ad.
Family-Friendly Content

Website owners select the type of content that appears in our units. However, if you would like to ensure that Content.ad always displays family-friendly content on this device, regardless of what site you are on, check the option below. Learn More
                   
 




በሳዑዲ አረቢያ ምሬቱ እና መጉላላቱ እንደቀጠለ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ገለጹ


    

(ቢቢኤን) ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አስፈላጊውን ፕሮሰስ ማለፍ ያለባቸው ስደተኛ ኢትዮጵያውያን፣ አሁንም ከመጉላላት እና ከምሬት አለመዳናቸውን ተናገሩ፡፡ እንደ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገለጻ ከሆነ፣ በጂዳ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤትም ሆነ በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚዲያ የሚናገረው እና በተግባር እየሰራ ያለው ስራ የተለያየ ሲሆን፣ ወደተጠቀሱት ቢሮዎች የሔዱ ኢትዮጵያውንም አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ በምሬት እየገለጹ ናቸው፡፡
በተለይ ደግሞ በየቀኑ ለመሳፈሪያ 100 ሪያል እያወጡ ከመኖሪያቸው ኤምባሲ እና ቆንጽላ ጽህፈት ቤት መመላለሱ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት እያደረሰባቸው እንደሚገኝ የገለጹት ኢትዮጵያውያኑ፣ በየቀኑ ከፍተኛ ወጪ እያወጡ ቢመላለሱም ጉዳያቸውን ማስፈጸም እንዳልቻሉ ይናገራሉ፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያወጣው የምህረት አዋጅ ሊጠናቀቅ ከአንድ ወር በታች የሆኑ ቀናት በቀሩበት በዚህ ሰዓት፣ ፕሮሰሳቸው መሔድ የሚገባውን ያህል አለመሔዱ እንዳሰጋቸውም ገልጸዋል፡፡ ቆንጽላውም ሆነ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚያወጡት ተደጋጋሚ ማስታወቂያዎች ላይ፣ ስደተኞችን በተቀላጠፈ ሁኔታ እያስተናገዱ እንደሆነ የሚናገሩት ሁሉ ውሸት መሆኑን የሚናገሩት ስደተኞቹ፣ ሁሉ ነገር ከአቅማቸው በላይ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡
የምህረት ቀኑ እያለቀ መምጣቱ ያሰጋቸው ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ፣ በለቅሶ ጭምር አቤቱታ ሲያቀርቡ የሚያመላክቱ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ወጥተዋል፡፡ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት፣ ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ደፋ ቀና እያሉ መሆናቸውን ቢገልጹም፣ ሳዑዲ ውስጥ እየተደረገ ያለው ነገር ግን ባለስልጣናቱ ከሚናገሩት ጋር ፍጹም የተቃረነ መሆኑን የዓይን እማኞች ይገልጻሉ፡፡ የኢትዮጵያ አምባሲ እና ቆንጽላው ለስደተኞች ደንታ የሌላው መሆናውን የሚናገሩት ስደተኞቹ፣ ዜጎች እንዴት መስተናገድ እዳለባቸው ከሌሎች ሀገራት ኤምባሲዎች እንዲማሩ ተናግረዋል፡፡ በሳዑዲ አረቢያ ከ300 ሺህ በላይ ወረቀት አልባ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ይገለጻል፡፡ የምህረት አዋጁም እነዚህን ሁሉ የሚመለከት ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ,ወደ ሀገራቸው የተመለሱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ግን በእጅጉ ትንሽ ሆኖ ተገኝቷል፡፡