Wednesday, May 3, 2017

የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል! (በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ)



  • ጎንደርና ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሁለት ወር ብቻ 9 የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል!
  • “ህወሃት የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ክፍል የበቀል መወጫ እያደረገው ነው”፤ ነዋሪዎች
ላይቆም የተቀጣጠለው የሰሜን ምዕራብ ብረት አከል ህዝባዊ አመፅ የትግል ስልቱን እየቀያየረ ባህርዳር ደርሷል፡፡ አስር ወራትን ያስቆጠረው የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ከገጠር ሽምቅ ውጊያ ወደ ከተማ የደፈጣ ቦምብ ጥቃት ተሻግሯል፡፡ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል፡፡ ድርጊቱ ሰላም የነሳው ህወሃት “የአማራ ክልልን የበቀል መወጫ እያደረገው” መሆኑ ይነገራል፡፡
ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ የደህንነት አቅሙንና የበዛ የመከላከያ ኃይሉን አማራ ክልል ላይ ቢያደርግም የነፃነት ኃይሎች ተከታታይነት ያለው ጥቃት ከመፈፀም ያገዳቸው ኃይል የሌለ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ የመጀመሪያዉ ዙር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመጠናቀቁ ከአንድ ወር በፊት መጋቢት የመጀመሪያ ሳምንት እስከ ሁለተኛዉ ዙር አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመጀመሪያ ወር ሚያዚያ አራተኛ ሳምንት ድረስ ጎንደር ከተማ ውስጥ ሰባት፤ ባህርዳር ከተማ ሁለት በድምሩ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታዎች ደርሰዋል፡፡
የቦምብ ጥቃቶቹ ያነጣጠሩት በአገዛዙ ማህበራዊ መሰረቶች (ባለስልጣናቱ በእጅ አዙር የሚነግዱባቸው ሆቴሎች፣ የደህንነቱ አባሪ ተባባሪ የሆኑ ስውር ነጭ ለባሾችን ቤት፣ የአገዛዙ ተሽከርካሪዎች፣ . . .) ላይ መሆኑ ደግሞ የነፃነት ኃይሎችን መዋቅራዊ ጥንካሬ አጉልቶ ያሳየ ተብሎለታል፡፡ በሁለት ወር ውስጥ ብቻ ዘጠኝ የቦምብ ጥቃት ባስተናገዱት ሁለቱ ከተሞች የወጣቶች የጅምላ እስር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ከሁለቱም ከተሞች የሰበሰብናቸው መረጃዎች እንደሚያመለክቱት “ህወሓት ክልሉን የቂም በቀል መወጫ እያደረገው ይገኛል” ሲሉ ነዋሪዎች ህወሓትን ይወነጅላሉ፡፡ “ከእያንዳንዱ የቦምብ ጥቃት በኋላ ፍንዳታው የደረሰበት ከተማ በተኩስ እሩምታ ሲታመስ ያድራል” የሚሉት ነዋሪዎች “በሌሊት ወጣቶችን ከመኖሪያ ቤታቸው አፍሶ መውሰድ የተለመደ ድርጊት ሆኗል” ይላሉ፡፡
በአንፃሩ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ የቦምብ ጥቃቶች የአገዛዙ ልሳን በሆኑ የሚዲያ ውጤቶች መግለጫዎች ሲሰጡ ባይሰማም ከጉዳዩ አሳሳቢነት የተነሳ የአሜሪካ መንግሥት አዲስ አበባ ባለው ኤምባሲው በኩል ዜጎቹ ወደ ባህርዳርና ጎንደር እንዳይጓዙ በይፋ ክልከላ ማድረጉን አሳውቋል፡፡ በየጊዜው እየደረሱ ባሉ የቦምብ ፍንዳታዎችና የሽምቅ ውጊያዎች የተነሳ በሰሜን ምዕራብ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ቁሟል፡፡ ለዕለት ፍጆታነት ከሚውሉ ሸቀጣሸቀጦች ውጪ ይህ ነው የሚባል የንግድ እንቅስቃሴ አለመኖሩ ደግሞ አካባቢው በኢኮኖሚ እንዲደቅ አድርጎታል፡፡
በቀደመው አመፅ የፈራረሰበትን መዋቅር በድህረ-“ተሃድሶ” እንቅስቃሴው መልሶ ማቋቋም የተሳነው ብአዴን የመካከለኛ አመራሩ ሽሽት መቆሚያ አጥቷል፡፡ የሰሜን ምዕራብ የመረጃ ምንጮቻችን ከእያንዳንዱ የቦምብ ጥቃት ጀርባ መዋቅራዊ ሽፋን እንዳለዉ ይጠቁማሉ፡፡
“በርግጥም በእስካሁኑ የቦምብ ጥቃቶች ተጠያቂ የተደረገ አካል አለመኖሩ የነፃነት ኃይሎች መዋቅራዊ ድጋፍ እንዳላቸው አስረጅ ምሳሌ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል” የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ፡፡ ጎንደር ውስጥ በሁለት ወራት ከደረሱት የቦምብ ጥቃቶች ውስጥ አምስቱ ጥቃቶች በኤፍ ዋን (F one) ቦምብ የተፈፀሙ ሲሆን፤ በተመሳሳይ መልኩ ከሦስት ቀን በፊት ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሙዚቃ ድግስ ላይ የደረሰው የቦምብ ጥቃት በፍንዳታና በማፈንጠር አቅሙ አቻ የሌለው እስራኤል ሰራሹ ኤፍ ዋን (F one) ቦምብ መሆኑን የመረጃ ምንጮቻችን ዘገባ ያመለክታል፡፡

ኦሮሚያ በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም በተመለከተ የተለቀቀውን ረቂቅ አዋጅ መንግሥት አላውቀውም አለ



‹‹በፌዴራል ደረጃ ሕግ የማውጣት ሥልጣን ያለው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው››
የኦሮሚያ ክልል
‹‹የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም ለመወሰን የወጣ አዋጅ›› በሚል ርዕስ የተለቀቀውን ረቂቅ ሰነድ፣ መንግሥት እንደማያውቀው አስታወቀ፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ረቂቅ አዋጆች የሕግ አወጣጥ ሥነ ሥርዓትን ተከትለው የሚያልፉ እንጂ ለማኅበራዊ ድረ ገጽ ፍጆታ የሚውሉ አይደሉም፡፡
‹‹እኛ የምናውቀው ሰነድ አይደለም፤›› ያሉት ሚኒስትሩ፣ በመንግሥት በማይታወቅ ሰነድ ላይ ማብራሪያ መስጠት እንደሚቸገሩም ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የተለቀቀውን ረቂቅ የሕግ ሰነድ ያውቀው እንደሆነ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹በፌዴራል ደረጃ የሚተገበር ሕግን የማርቀቅ ኃላፊነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው፤›› በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ነገር ግን የኦሮሚያ ክልል በፌዴራል ደረጃ የሚወጣው ሕግ ሊያካትታቸው ይገባቸዋል ያላቸውን ጉዳዮች ለፌዴራል መንግሥት ማስታወቁን ጠቁመዋል፡፡
‹‹የኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ/አዲስ አበባ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም ለመወሰን የወጣ አዋጅ›› ተብሎ የተለቀቀው የሕግ ረቂቅ ሰነድ የአዲስ አበባ ከተማ ስም በጽሑፍ ‹‹ፊንፊኔ/አዲስ አበባ›› ተብሎ መጠራት እንዳለበት ይገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራና ኦፊሴላዊ ቋንቋ አማርኛና አፋን ኦሮሞ እንዲሆን የሚል አንቀጽ ይዟል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 49 ሥር ከንዑስ አንቀጽ አንድ እስከ አምስት ድረስ ስለአዲስ አበባ የተደነገገ ነው፡፡
በድንጋጌዎቹ መሠረት አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግሥት ርዕሰ ከተማ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሙሉ ሥልጣን እንዳለው፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ተጠሪነቱ ለፌዴራል መንግሥት ስለመሆኑና ከኦሮሚያ ክልል ጋር ስላለው የጥቅም ግንኙነት ይገልጻል፡፡
ይህንን የጥቅም ግንኙነት የሚገልጸው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ አምስት ሲሆን፣ ‹‹የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ፣ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሀል የሚገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፤›› ይላል፡፡
በማኅበራዊ ድረ ገጾች የተለቀቀው ረቂቅ የተባለው ሰነድ ይህንኑ ጥቅም ለማስጠበቅ የተረቀቀ ቢሆንም፣ ከላይ የተጠቀሰው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ እንደማይገድበው ይገልጻል፡፡
‹‹በዚህ (ረቂቅ) አዋጅ ውስጥ የተጠቀሱት ዝርዝር የክልሉ መብቶችና ልዩ ጥቅሞች በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 49 ንዑስ አንቀጽ (5) ላይ የተገለጸው አጠቃላይ አነጋገር የሚገድበው አይሆንም፤›› በማለትም ይገልጻል፡፡
ይህ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀ ረቂቅ ሰነድ በ14 ገጽ የቀረበና 46 ገጽ አባሪ ማብራሪያዎችን የያዘ ነው፡፡
ምንጭ ፦ሪፖርተር

Tuesday, May 2, 2017

የሕወሓት ወታደሮች የአምቦን ነዋሪ እያዋከቡ ነው | ወጣት ሆኖ በምሽት የሚንቀሳቀስ ይታሰራል



(ዘ-ሐበሻ) በአምቦ ከተማ ቀስ በቀስ እየተነሳ ያለው የወጣቶች እና የተማሪዎችን አልገዛም ባይነት ተከትሎ በአካባቢው የሰፈረው የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት ነዋሪዎችን እያዋከበ መሆኑ ተዘገበ::
አምቦ ከተማ ፎቶ ከዘ-ሐበሻ ፋይል
ከአምቦ አካባቢ የሚመጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ጋብ ብሎ የነበረው የአምቦ ነዋሪዎች አልገዛም ባይነት ሰሞኑን በስፋት እየታየ መምጣቱን ተከትሎ የሰፈረው ሠራዊት ዓይኑ ያላማረውን እያጋዘ እንደሚያስርና እንደሚደበድብ ታውቋል::
ምሽት ላይ በከተማዋ ድንገት ሲንቀሳቀስ የተገኘም በተለይ ወጣት ከሆነ እንደሚታሰር አልያም በአጋዚዎቹ ትንኮሳ እንደሚያጋጥመው የሚገልጹት ምንጮቹ በአደባባይ የፈለጉትን ሰው እያስቆሙ ጥያቄ በመጠየቅ አፍሰው እንደሚወስዱ ገልጸዋል::
በአምቦ የህዝብ አልገዛም ባይነቱ ከ ዕለት ወደ ዕለት እየታጋጋለ ሲሆን በአካባቢውም በርካታ የሕወሓት ሠራዊት መስፈሩ የደረሰን መረጃ ያመለክታል::
በአምቦ ያለውን ሁኔታ ዘ-ሐበሻ ተከታትላ ትዘግባለች::

በወገኖቻችን ላይ በ ሕወሃት ና ደጋፊዎቹ የሚፈጸምውን የግፍ፣ ሰቆቃ ና ወንጀል በአለም አቀፍ ስለመምዝገብና ማስርጃ ስልመያዝ አስፍላጊነት። (በሙሉቀን ገበየው)




ባልፉት 26 አምታት በላይ፡ ሕወሃትና ደጋፊዎቹ  በኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን ላይ የፈጸሙትና እይፈጸሙት ያሉት በደል፣ግፍ ና ስቃይ ስፍር ቁጥር የለውም። የሰው ልጅ በወገኑ ላይ እንዲህ ያለ ጭካኔ መፈጸሙን መስማት ለማመን ይከብዳል። ይህ ወንጀላቸው ግድያ፣ እስራትን፣ ግርፋትን፣ ማፍናቀልን፣ከስራ ማባረርን፣ ማስቃየትን(የአካል፣የኧአምሮ፣ ስሜት፣ የገንዝብ/ንብርት የምሳስሉትን) በዘር ማጽዳትና  ሌላውንም ይጨምራል።

በዚህ ስቃይ ያለፉ ወግኖቻችን፡ በቃልና በጽሁፍ የሚያቀርቡትን ማስርጃዎች መስማት እጅጉን አደርጎ ይረብሻል ፤ይዘገንናልም። ይህን ወንጅል የሚፈጽሙት ወንጅለኞች በህይውት ያሉና፣ በስልጣን ላይ የተቀመጡ፤ አሁንም እጥፍ ድርብ ሰቆቃን የሚፈጽሙ ናቸው።

ይህን አስከፊ ወንጀል ለመምዝገብና ለማስርጃነት ለመያዝ የሞከሩ ድርጅቶችና ግልሰቦች ቢኖሩም፤ ስፋትን ጥልቀት ባለው አብዛኛውን ሰቆቃ ለማስርጃነት መዝግቦ በቀጣይነት፤ እንዲሁም ኢትዮጲያውያን በቀላሉ ሊመዘግቡት በሚችል መልኩ የተዛጋጁ አይደለም። ይህም በሚደርሰው ጫናና በተለያዩ ምክንያቶች ነው።
የቀድምው የኢትዮጲያ ሰበአዊ መብት ጉባኤ (ኢሰመጉ በ ፕሮፌሰር መስፍን የተመሰርተው) እና በወጣቱ ጸሃፊ ሙሉቀን ተስፋሁን በአማራ ወጎኖች ላይ የደርሰውን እንግልትና ስⷃይ በመጽሃፉ ማስፈሩ የሚጠቀሱ መልካም ማስርጃ የማኖር ስራዊች ነብሩ።

አሁን ያልንበት ዘመን የመረጃ ዘምን ነው። መረጃ በቀላሉ የሚምዘገበብት፣ የሚሰራጭበት  ለሌላም ጊዜ ማስቀመጥ የሚቻልበት ዘመን ነው። ባልፉት 2 አምታት እንኳ በመሃበራዊ ሚዲያ የቀርቡ አንዳንድ ሰቆቃዎችን ለማየት፣ለማንበብ ችልናል። በተደራጀ፣ ቀለል ባል መልክ፣ ሁሉም ሊያየውና በማስርጃ ሊመዘግብ የሚያስችል  አለምአቀፋዊ መዝገብ (electronic) ያስፈልገናል።

ሳይመን ዊዘንታሃል የሚባል  በ ናዚ የስቅይ ማጎሪያ ቤት(Holocaust)  የተሰቃየና በኋላም ናዚዎችን የማደን (ማሳደድ)  እና በመከታተል፣ ማስርጃ ያኖር ይሁዳውያን  ታዋቂ ጸሃፉ ነበር። ሳይመን በወግኖቹ ላይ ሰቆቃ የፈጸሙትን የናዚ ወንጅለኞችን ማስረጃ በማሰባሰብና በመከታትል ብዙ ወንጅለኞቹን ከሁለትኛው የአለም ጦረነት ቦኋላ ለፍርድ ያቀረበ፡ በይሁዳውያን ላይ የደርሰወን ሰቆቃ የሚመዘግብ ማእከል በቪያና 1961 (እአአ) የመሰረተ ታላቅ ሰው ነበር። የሱ ስራዎች  ብዙ ናዚዎችን በህይወታቸው እርፍት የነሳና ለፈርድ ያቀርበ ስው ነበር።

እኛም ኢትዮጲያውያን የተደራጀ፣ በቀላሉ ሊሰበስብ የሚያስችል፣ ማንኛውም ኢትዮጲያዊ  የደረሰብትን፤ የተመለከተውን፣ ሌሎች ያሳወቁትን የሕውሃት ወንጀለን፤ ሊዝገብወ የሚገባ አለማቀፋዊ ባሀረ-ማስረጃ መዝገብ ያስፈልገናል። እንዚህ የህወሃት ወንጀልኞች የትም ቢደብቁ፣የሚፈጽሙት ወንጅል የማይረሳና ወደፊት እነርሱን በህግ ስር ለማቅርብ የሚረዳ መሆኑን ሊያውቁት ይገባል።

ስለዚህም፡ በአለም ላይ ያልችሁ ኢትዮጲያውያንና የኢትዮጲያን ወዳጆች ሁሉ፤ በመረጃ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በ ህግ ሞያ (Information Technology and Law) እውቀቱና ልምዱ ያላችሁ፡ ይህን አለምአቀፋዊ  ኢትዮጲያውያን ላይ የሚደርሰወን ወንጅል የሚመዘግብ ባህረ-መዝገብ (Data base, website) እንድታቋቁሙ ጥያቄ አቀርባልሁ። ለዚሁም በሚያስፈልገው መልክ (በምከር፣ በገንዝብ፣ በመሳስሉት) ለመርዳት ብዙዎቻችን ፍላጎቱ አለን።

እንዲህ ያል የመረጃ ማእከል፡በቀላሉ በይትኛውም የአለም ከፍል ያለ ኢትዮጲዊ የደርሰበትን፤ ያየወን ወይም የሰማውን መርጃ፣ ማስረጃ (የጹሁፍም ይሁን የድምጽ ወይም ምስል) እና ተገቢውን መረጃ በማን፤ የት፣መቼ፣ምን አይነት ስቅይ/በደል፣የወንጅሉ ውጤትና ሊሎችንም መምዝገብ ያስችላል።ለወደፊቱም ማስርጃ ይሆናል።
ዘመናዊ Information Technology ምስጋና ይገባውና ባሁኑ ሰአት መረጃ በ ወያኔ ላይ ለምሰብሰብ እንደ ሳይመን  ዊዘንተሃል ከአንዱ አለም ወደ ሌላ አለም መጓጓዝና መድከም የለብነም።

ምንም እንኳ ይህ ሃሳብ ቀለል ያለ ቢምስልም ወያኔ ላይ ለሚደረገው ትግል አስፈላጊና ጠቃሚም ነው። የዛሬ ባለስልጣኖች የነገ በፍርድ መንብር ተንበርካኪዊች እንዲሆኑ ያስችለናል።

(በዚህ ሃሳብ ላይ ኢትዮጲያውያን የሚሰጡትን ምክር ተከትሎ ሁለተኛ ክፍል ጽሁፍ ይቀጥላል።)

የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች አመጽ ቀስቃሽ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ተነግሯቸዋል ተባለ


የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች አመጽ ቀስቃሽ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ተነግሯቸዋል ተባለ
አመጽ ቀስቃሽ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ተነግሯቸዋል ተባለ – ካለፈው ሳምንት ሚያዚያ 11 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስቴዲየም በሚገኘው የመንገዶች ባለሥልጣን አዳራሽ በፈረቃ ከመንግሥት ሰዎች ጋር እየተወያዩ የሚገኙት ባለ ኮድ አንድ የታክሲ ሾፌሮች በቁጥር ከ5ሺ ይልቃሉ፡፡
ውይይቱ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ሲሆን አዲስ የወጣውን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደነብ ቁጥር 395/2009 ከሚመለታቸው አካላት ጋር ለማስተዋወቅ የተሰናዳ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ኾኖም መድረኩ ቅሬታና የዓመታት ብሶት ገንፍሎ በወጣባቸው የታክሲ ባለንብረቶችና ሾፌሮች ቁጥጥር ሥር ወድቋል ለማለት ያስደፍራል፡፡
በሰባቱ ቀናት ስብሰባ የመናገር እድል የተሰጣቸው ተወያዮች መንግሥትን ክፉኛ የተቹ ሲሆን የብዙዎቹ አቤቱታ “መንግሥት እኛን እንደተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ እንደ አገልግሎት ሰጪ አድርጎ አይመለከተንም” የሚል ነው፡፡
“እኛን ከመክሰሳችሁ በፊት ራሳችሁን ብትፈትሹ ጥሩ ነበር” ያሉ አንድ የታክሲ ባለንብረት “በአገሪቱ ሙስና የተፈለፈለው ከናንተ ቢሮ አይደለምን?” ሲሉ ጉቦ የማይጠይቅ ትራፊክ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል የ15 ዓመት ልምዳቸውን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡
በየቀኑ ከ10 እስከ 20 የሚሆኑ ታዳሚዎች ሐሳባቸውን እንዲሰጡ በተደረገበት በዚህ ዉይይት ፖለቲካዊ መንፈስ የነበራቸው ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡
“በ97 ምርጫ ዋዜማ ለሰልፈኞች ነጻ ትራንስፖርት ሰጥታችኋል ብላችሁ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በበጎ እንደማታዩን ይገባናል፡፡” ያሉ ሌላ ባለንብረት ንግግራቸው በጭብጨባ ከተቀቋረጠ በኋላ ሐሳባቸውን የቀጠሉ ሲሆን ሁሉም ዘርፎችን መንግሥት ባለው አቅም ሁሉ እየደጎመ ታክሲን ቸል ያለበት ምክንያት ከዚሁ የጠላትን ስሜት የመነጨ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡ “ለመንግሥት ሠራተኛ በሰበብ አስባቡ ደመወዝ ትጨምራላችሁ፣ የኛን ታሪፍ ለማሻሻል ግን አንድ ቀን እንኳ አስባቸሁ ታውቃለችሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በዚህ አስተያየት የተበረታቱ ሌላ የታክሲ ባለንብረት የመናገር እድሉን ያገኙ ሲሆን “እዚህ አገር በሕዝብም በመንግሥትም እየተጠላን፣ ዘላለም እየተረገምን የምንሠራ እኛ ታክሲዎች ነን፡፡” ካሉ በኋላ “ተመስግነን አናውቅ፣ አትርፈን አናውቅ፣ ሕይወታችን ተለውጦ አያውቅ፡፡ እስቲ ከታክሲ ሥራ ተነስቶ እዚህ ደረሰ የተባለ ሰው ንገሩኝ” ሲሉ ታዳሚውን ጠይቀዋል፡፡ “እኔ ንግግሬን በሌላ አትውሰዱብኝና እኛ ታክሲዎች ጧት ተነስተን ባንሠማራ እኮ አገሪቷም ትቆማለች፡፡ መንግሥትም የሚሽመደመድ ይመስለኛል፣ ከናንተ ውስጥ ግን ይህን የሚያስብ ያለ አይመስኝም” ሲሉ ሐሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡ ታዳሚውም በጭብጨባ ድጋፉን ገልጾላቸዋል፡፡
” ለመሆኑ የመኪና መለዋወጫ ዋጋን ታውቃላችሁ? ስፔርፓርት ስንት ነው?” በሚል ጥያቄ የሰነዘሩ ሌላ የታክሲ ባለንብረት፣ “ዛሬ አንድ ስፖኪዮ ቢሰበር ስንት ብር እንደሚያስወጣን ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ ባልጠራችሁን ነበር” ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡ “ለነገሩ መንግሥት ሕዝብን መስማት ካቆመ ስለቆየ በናንተ አልፈርድባችሁም፤ እኛ ትዝ የምንላችሁ እኮ አድማ ስንመታ ብቻ ነው፤ ጃንሆይንም ታክሲ ነው ያወረዳቸው፣ ታሪክ ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ አትጠሩንም ነበር” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አባት በመድረኩ አስተናባሪዎች ተግሳጽ ደርሶባቸዋል፡፡
” እዚህ መድረክ ስላገኘን ብቻ እንዳመጣልን መናገር ተገቢ አይመስለንም፡፡ ታክሲዎች ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ ይቅርብኝ ብሎ ያለቀረጥ ከአንድ ሺ በላይ ታክሲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የተደረገውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የትርፍ ህዳጋችን መጨመር አለበት፣ ሥራው በሚፈለገው መልኩ እያተረፈን አይደለም የሚለው ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ ካመጽን አገር ትቆማለች ማለት ግን ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው፤ መንግሥት እናንተ የምታገኙት ትርፍ ወቅቱን ያገናዘበ እንዳልሆነ ይረዳል፡፡ ለዚህም ጥናት እያደረገ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡” የሚል ምላሽ ከመድረክ መሪዎች በአንዱ ተሰጥቷል፡፡

መንግስት በየቦታው የጀመራቸው ፕሮጀክቶች በአብዛኛው በጅምር በመቅረታቸው ሕዝቡን እያማረረ ነው | በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የመሠረት ድንጋይ ተጥሎ ፕሮጀክቱ የውሃ ሽታ መሆኑ የተለመደ ሆኗል



እንደ ትንሳኤ ሬዲዮ ዘገባ መሰረት በአገር ሃብት ዘረፋ የተሰማራው ሙሰኛው የህወሃት አገዛዝ ለገጽታ ግንባታ ሲል በተለያዩ ክልሎች አስጀምሮአቸው የነበሩት የልማት መሠረቶች በአብዛኛው ገና ከጅምር ላይ እንዳሉ የተቋረጡ አለያም ግማሽ መንገድ ተገፍቶ የቆሙ መሆናቸው ታውቋል።

ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ሳያደርግ የአገርና የመንግሥት ገንዘብ አለአግባብ እንዲባክን ምክንያት እየሆኑ ነው በማለት ህብረተሰቡ ማማረሩን ወደ ተለያዩ ክልሎች ለሥራ የተላኩ ልማታዊ ጋዜጠኞ መዘገባቸውን ከአገዛዙ ሥር ከሚተዳደሩ ሚዲያዎች ዘገባ ለማወቅ ተችሎአል።
በቅርቡ ወደ ኢሉ አባቡር ተልኮ የነበረው የልማታዊ ጋዜጠኞች ቡድን በቡኖ በደሌ ወረዳ ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ለመዘርጋት ከ9 አመት በፊት ተጀምሮ የነበረው ፕሮጀክት እስከዛሬ ድረስ አገልግሎት መስጠት አለመቻሉ ብቻ ሳይሆን የተዘረጉ የኤሌክትሪክ ገመድ መሸከሚያ ሚሶሶዎችና በየቦታው የቆሙ ትራንስፎርመሮች መወዳደቅ መጀመራቸውን መመልከታቸው ዘግበዋል።
ስለዚህ ፕሮጀክት ለጋዜጠኛው ቡድን አስተያየታቸውን የሰጡ የበደሌ መብራት ሃይል ሃላፊ ፕሮጄክቱን የተረገበው ድርጅት ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተከፈለውና ርክክብ ሳይፈጽም እንደተሰወረ ተናግረዋል።
ሃላፊው ስለዚህ ችግር በወቅቱ ለበላዮቻቸው ሪፖርት አድርገው እስከ ዛሬ ምንም አይነት እርምጃ እንዳልተወሰደም አረጋግጠዋል።
ገንዘቡ ከተበላ ቦኋላ ባክኖ ከቀረው ከዚህ የፕሮጄክት ሥራ በተጨማሪ በዚያው ዞን የመጠጥ ውሃ ለማዳረስ፤ ኪሊኒኮችና ጤና ጣቢያዎችን ለመገንባት እንዲሁም ወረዳዎችን የሚያገናኙ የመኪና መንገዶች ለመሥራት በሚሉ ሰበቦች ብዙ ሚሊዮን የአገር ሃብት በከንቱ ባክኖ ቀርቶአል።
በጣም የሚያሳዝነው በነዚህ አብዛኛው ቦታዎች ላይ ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ቦታው ለልማት ይፈለጋል እየተባለ ከተፈናቅሉ ቦኋላ ልማት የተባለው ነገር በተግባር ሳይታይ በርካታ አመታት እየተቆጠሩ ነው።
በአብዛኛው በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለልማት ተብለው የሚጀመሩ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ ከተቀመጠላቸው ቦኋላ
የውሃ ሽታ ሆነው የሚቀሩ አለያም ደግሞ የተወሰነ አሸዋና ድንጋይ በቦታው ከተጣለና ቁፋሮ ከተካሄደ ቦኋላ እዛው ላይ የሚቀሩ ናቸው።
በደቡብ ክልልም ተመሳሳይ ችግሮች እየተስተዋሉ እንደሆነ በርካታ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የህወሃት ንብረት የሆኑ ሚዲያዎች አልፎ አልፎ እነዚህን እውነታዎች ይፋ በማድረግ ችግሩን በበታች ሃላፊዎች ላይ ለማላከክና ሥርዓቱን ከተጠያቂነት ነጻ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እየተስተዋለ ነው።
የመንግሥትን ልማታዊነትን ለመስበክና በመላው አገሪቱ እየተስፋፋ ነው የሚሉትን የዕድገትና የብልጽግና ዜና ብቻ በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለማዘናጋት ወይም ለማደንዘዝ የተቋቋሙ የህወሃት ሚዲያዎች ህዝባችን እየተማረረባቸው ያለውን እነዚህን ችግሮች በመዘገብ ሥራ ላይ እየተጠመዱ ያሉት መንግሥት ችግሮቹን እንዳወቀና መፍተሄ ለመስጠት እንደሚንቀሳቀስ ባዶ ተስፋ በመስጠት ተቃውሞ እንዳይነሳ ጊዜ ለመግዛት እንደሆነ ሚዲያዎቹን የሚከታተሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ።
በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ከተጀመሩ አመታት ያስቆጠሩና በእንጥልጥል የቀሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፕሮጄክቶች እያሉ ህወሃት ህዝቡን በተስፋ ለመደለል ሲል አሁንም በጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አማካይነት የተላያዩ መሰረተ ድንጋዮችን በበርካታ ቦታዎች ማስቀመጥ መቀጠሉ በርካታ ሰዎችን እያነጋገረ ነው።
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሚያዚያ 14 ቀን ከጎንደር ከተማ ወጣ ብላ በምትገኘው የጤዳ ከተማ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ መሠረት ድንጋይ ለማስቀመጥ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በስፍራው ተገኝቶ እንደነበር የገለጹ ምንጮቻችን የአካባቢውን ህብረተሰብ ለማስደሰት በዕለቱ 35 በሬዎች ታርዶ እንደነበርና በስርዓቱ ላይ ቂም የቋጠረው የከተማው ህዝብ ግን ወደ ግብዣው ቦታ ባለመሄድ ድግሳቸውን እንዳሰናከለባቸው አስረድተዋል።
አሁን በጠዳ ከተማ ለጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ በተቀመጠበት ቦታ ላይ ቀደም ሲል ይኖሩ የነበሩ ዜጎች ከአመታት በፊት ቦታው ለልማት ይፈለጋል በሚል ሰበብ ያለምንም ካሳ እንዲፈናቀሉና መሬቱም ያለምንም ጥቅም ለአመታት ከተቀመጠ ቦኋላ ህብረተሰቡ ውስጥ የተፈጠረውን ቅሬታ ለማስታገስ ነው ይህ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠው የሚሉ አሉ።
ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሰሞኑን አደዋ ውስጥ ለፓን አፊሪካ ዩኒቬርሲቲ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ሲያስቀምጥ ባደረገው ንግግር በአደዋ ያስቀመጠው መሠረተ ድንጋይ ከዚህ ቀደም በሌሎች ቦታዎች ተቀምጠው እንደቀሩት መሠረተ ድንጋይ ብቻ ሆኖ እንደማይቀር ቃል በመግባት በሌሎች ቦታዎች የሚደረገው ለፕሮፖጋንዳ ፍጆታ እንደሆነ ማረጋገጫ ሰጥቶአል።

ከሃይለማሪያም በስተጀርባ ያለው ” ስሁል ሚካኤል ” ማን ነው? [ ቬሮኒካ መላኩ]



ብዙ ጊዜ የአለፉ አገር መሪዎችን ታሪክ ማንበብ እወዳለሁኝ ። ይሄን የማደርገው የመሪዎች ባህሪ ፣ አመራር ጥበብ ፣ ጥንካሬ ፣ ድክመት የአገርንም የህዝብንም እጣ ፋንታ ሲወስን አንብቤለሁኝና ወይም አምናለሁና የመሬዎችን ታሪክ ማንበቡ ፋይዳው ብዙ ነው የሚል የግል እምነት ስላለኝ ነው።
አፄ በካፋ የተባሉት ንጉስ ጎባጣ ነበሩ አሉ ። ታዲያ በዙሪያቸው የነበሩት መኳንንቶች ፣ መሳፍንቶች ቀጥ ብለው ከሄዱ ቁመታቸው ንጉሱን ስለሚበልጥና ይሄም ንጉሱን ሊያስከፋቸው ይችላል ብለው ስለሚያስቡ ንጉሱን ለመምሰል ጎበጥ ብለው ይሄዱ ነበር አሉ ።ይሄን የተመለከተው ህዝብ ” እንደ ንጉሱ አጎንብሱ! ” ማለት ጀመረ ይባላል ። “የጎባጣ አሽከር አጎንብሶ ይሄዳል ። ለምን? ቢሉት ጌታዬን ለመምሰል ነዋ ” የምትባለውም አባባል ከዚሁ የተያያዘች ሳይሆን አይቀርም ።
እኔ ሳስበው እነዚያን መኳንንቶች “የሚጎብጡት ” ንጉሱ አስገድደዋቸው ሳይሆን ይልቁንስ ለሀይለኛው የማደግደግ ሰውኛ ባህሪያው ስለሆነ ይሆናል።
ጆሴፍ ስታሊንም የግራ እጁ ከቀኝ እጁ አጭር ስለነበረች ባለስልጣናቱ አይናቸውን ወደዛች አጭር እጅ ከወረወሩ ጣጣው ከባድ እንደ ነበር ይነገራል ።
እኛም በጊዜያችን በህይወት ያለ ሳይሆን ከሞተ 3 አመታት ያለፈው መሪ አነጋገር ፣እጅ እንቅስቃሴ ፣ መነፅር አደራረግ ፣ ምንም ሳያስቀር ኮርጆ የሚተገብር መሪ እየተመለከትን ነው ። ልዩነቱ የድሮዎቹ መኳንንቶች የሚያደገድጉት ለህያዋን ሲሆን ይሄኛው ለሙት መሆኑ ነው ።

ዛሬ ስታሊንንም በካፋንም ማንሳቴ ” የእኛው ጉድ ” ስለሆነው “ጠቅላይ ሚንስትር” ልፅፍ ፈልጌ ነው ። ” ጠቅላይ ሚኒስትር ” የሚለውን ማእረግ በትምህርተ ጥቅስ ማስገባቴ እስካሁን ጠቅልሎ ስለማያውቅ ወደፊትም ይጠቀልላል ብዬ ስለማልገምት ነው።

የዚህ ፅሁፍ አላማ የታዘዘውን የሚያወራው እና ስራ የተባለውን የሚሰራውን ሃይለማሪያምን መገምገም ሳይሆን ከመጋረጃው ጀርባ ያለውን “ስሁል ሚካኤልን ” መፈለግና ማፈላለግ ይሆናል ።
በመጀመሪያ “ስሁል ሚካኤል ማን ነው? ” የሚል አንባቢ አይጠፋምና በዚህ ላይ ትንሽ ጊዜ ላጥፋና ወደ ዋናው ጉዳይ እገባለሁኝ ። ራስ ስሁል ሚካኤል በ1750 ዎቹ ከትግራይ ወደ ጎንደር በአፄ ኢዮአስ ዘመነ መንግስት ጊዜ በአንገቱ ድንጋይ አስሮ እና አደግድጎ ለደጅ ጥናት ወደ ጎንደር ቤተ መንግስት ገባ ።
ስሁል ሚካኤል ወደ ጎንደር የሄደው ትግራይ ውስጥ በደል ስለበዛበት የደረሰበትን በደል ለማመልከት ነበር ። ነገር ግን ስሁል በደሉን አመልክቶ ወደ ግዛቱ ወደ ትግራይ ከመመለስ ይልቅ እዛው ጎንደር ቤተመንግስት በመቅረት እንደ አማካሪም በመሆን እያገለገለ ቆየ ። እየዋለ እያደረ ተንኮል እየሸረበ እና እየገመደ ቤተ መንግስቱን ማተራመስ ጀመረ ። በመጀመሪያ የራስ ሚካኤል ስሁል የመጀመሪያ ሰለባ የሆነው ንጉስ ኢዮአስ ነበር ። ንጉስ ኢዮአስን በሻሽ አንቆ ከገደለ በኋላ ከአምባ ግሸን የ 70 አመቱን አዛውንትና አንድ እጁ የተቆረጠውን ዮሃንስ በማምጣት አፄ ዮሃንስ ብሎ አነገሰ ።

አምባ ግሸን ወይም ወህኒ አምባ የሚባለው ቦታ በዛ ዘመን የነጋሲ ዘር ያላቸውና በስልጣን ላይ ያለው ንጉስ ሲሞት የሚተኩት ልኡላን የሚከማቹበት ቦታ ነበር ። የአምባ ግሸን ጉዳይ (ወህኒ አምባ) ራሱን የቻለ አስደናቂ ታሪክ ስላለው ወደፊት እመለስበታለሁኝ ። ራስ ሚካኤል ስሁል ኢዮአስን በሻሽ አንቆ ከገደለ በኋላ ራሱ በኢዮአስ ዙፋን ያልተቀመጠው የነጋሲነት ዘር ስላልነበረው እና ቢነግስ ህጋዊነት እና ቅቡልነት ከህዝቡ እንደሚነፈገው በመረዳቱ ነበር ።
በዚህም አማካኝነት ያለው አማራጭ እጅግ ደካማውን ፣ እጀ ቆራጣውን እና የ70 አመቱን ዮሃንስን ዙፋኑ ላይ አስቀምጦ ከመጋረጃ ጀርባ ሆኖ በአሻንጉሊቱ ንጉስ አማካኝነት አገር ማስተዳደር ጀመረ ።

አሻንጉሊት ከሆንክ Use and throw (ተጠቅሞ መወርወር) ነውና አሁን የመጣል ባለተራ የ70 አመቱ አዛውንት አፄ ዮሃንስ ሆነ ። ትኬቱን ስሁል ቆረጠ ። ስሁል ሚካኤል ይሄን ንጉስ ለ 1 አመት ከተጠቀመበት በኋላ እንደፈለገው አልታዘዝለት ሲል በ1761 ከምግብ ጋር መርዝ አብልቶ ገደለው ። የ70 አመቱን አዛውንት በመርዝ ከገደለ በኋላ ከአምባ ግሼን የሟቹን ዮሃንስን ልጅ ተክለሃይማኖትን አስመጥቶ አነገሰ ። በዙፋኑ ላይ አፄ ተክለሃይማኖት ለስሙ አንግሶ ከመገረጃ ጀርባ ሲገዛ ለትንሽ አመታት ከቆየ በኋላ ህዝቡ ስለአመፀበት ሸሽቶ ወደ ትግራይ ሄዶ እዛው አገሩ ሞተ ።

አሁን በመጠኑም ቢሆን የራስ ስሁል ሚካኤልን ታሪክ ያስረዳሁ መሰለኝ ። ስለዚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ” ራስ ስሁል ሚካኤል ” የሚለው ስም የሚወክለው አሻንጉሊት ንጉስ አስቀምጦ ከመጋረጃ ጀርባ ያለ ፣ ዋና ስልጣን ያለው ፣አድራጊ ፈጣሪ ሰው ማለት ነው ። ፈረንጆቹ ” King Maker ” የሚሉት መሆኑ ነው ።

የታሪክ ምሁራን እና ፖለቲከኞች ” ታሪክ ራሱን ይደግማል ። አይደግምም ። ” እያሉ ጎራ ለይተው ይከራከራሉ ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበረው ሄንሪ ኪሲንገር “ ታሪክ ራሱን ይደጋግማል ። ማንኛውም በምድር ላይ የተነሣ መንግስት በተመሳሳይ መልኩ በመጨረሻ ከመፈራረስ አልዳነም” ብሏል ። በመቀጠልም “ታሪክ ከሽፈው የቀሩ ጥረቶች፣ ሳይፈጸሙ የቀሩ ምኞቶች ጥርቅም ነው። . . . ስለዚህ የታሪክ ተመራማሪ የሆነ ሰው አሳዛኝ ሁኔታ መምጣቱ የማይቀር መሆኑን ተቀብሎ ለመኖር ይገደዳል” ብሏል ።

ኮሚኒስት ፈላስፎች በተቃራኒው “ታሪክ ራሱን አይደግምም ባይሆን በአዲስ መልክ ይከሰታል ” ይላሉ። ዲዲሮ እንደሚለው ፈላስፋ ይሄን በምሳሌ ሲገልፅ << በአንድ ጅረት ውስጥ ሁለት ጊዜ አትታጠብም ። የታጠብክበት ውሃ አልፎ ወርዷል ። እንደገና የምትታጠበው በአዲስ ውሃ ነው ። >> ይላል ።

እኔ በበኩሌ ከ250 አመታት በፊት ስሁል ሚካኤል ያነገሰው እጄ ቆራጣው እና የ 70 አመቱ አሻንጉሊት አዛውንት ከ 250 አመታት በኋላ መለስ ዜናዊ ከጎለተው የ 58 አመቱ ” ጠቅላይ ሚንስቴር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ስለሚመሳሰልብኝ ታሪክ ራሱን ይደግማል የሚሉትን ምሁራን እቀበላለሁኝ ። ዋናውን ጉዳይ ትቼ የታሪክ ትንታኔ አበዛሁ መሰለኝ ባይጠቅማችሁም አይጎዳችሁም በማለት ነው።

አንባቢ እንድረዳልኝ የምፈልገው ይሄ ፅሁፍ ስለአገራችን ኢትዮጵያ የፖከቲካ ሁኔታ ቢዳስስም ፅሁፌ የሚያተኩረው ህውሃት እና ሃይለ ማሪያም ደሳለኝ ላይ ብቻ ነው ። በእኔ እምነት ሌሎቹ ድርጅቶች በራሳቸው ሂይወት የሌላቸው ግኡዝ የሆኑ እንግዴ ልጆች ናቸው የሚል እምነት ስለአለኝ ነው ።

ህውሃት በኢትዮጵያ አቆጣጠር በለስ ቀንቶት አራት ኪሎ ቤተመንግስት ከገባ ጀምሮ አገሪቱን የገዛበትን የአገዛዝ ዘዴ በሶስት ዋና ዋና ወቅቶች መክፈል እንችላለን ።

1) ከ 1983 _ 1993 ~ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ የህውሃት የስልጣን ዘመን በድርጅቱ ውስጥ ጎልቶ የወጣ እና ፈላጭ ቆራጭ የሆነ ስልጣን ያለው ሰው አንድም አልነበረም ። በነዚህ 10 አመታት መለስ ዜናዊ በሽግግሩ ጊዜ የፕሬዚደንትነት እና ከሽግግሩ በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን ቢኖረውም የፈላጭ ቆራጭነት ስልጣን አልነበረውም ። በዚህ 10 አመታት ህውሃት ይከተል የነበረው የአመራር ዘዴ ከበርሃ ይዞት የመጣውን Collective Leadership ( በህብረት መምራት) ባህል ነበር ። በዚህም መሰረት እነዚያ 10 አመታት ህውሃት እንደ ድርጅት በጋራ በመወሰን ሲገዛ ኖሯል ።

2) ከ1993 _ እስከ መለስ ዜናዊ ሞት ድረስ ~ የኢትዮ ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በተከሰተው የህውሃት ክፍፍል የመለስ ዜናዊ ቡድን ማሸነፉን ተከትሎ አገሪቱ ህውሃት ከሚባል የሽፍታ ቡድን መመራት ወደ አንድ አምባገነን መሪ የተሸጋገረችበት ወቅት ነበር ። በእነዚህ አመታት ህውሃት ማለት መለስ ዜናዊ ማለት ነበር ። በ 1993 አም መለስ ዜናዊ ክፍፍሉን አሸንፎ ከወጣ በኋላ በአገሪቱ ውስጥ ብቸኛ ፈላጭ ቆራጭ ሆኖ ብቅ አለ። በእነዚህ አመታት ህውሃት ብቻ ሳይሆኑ ብአዴን ፣ ኦህዴድ ፣ ዴኢህዴን እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ይተነፍሱ የነበሩ በመለስ ዜናዊ ሳምባ ነበር ።

3) ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ _ ዘመነ አሻንጉሊት ።
እነዚህ አጭር አመታት የአገሪቱ ፖለቲካ መዋህር በማን ላይ እንደሚሽከረከር ያልታወቀበት ፣ አገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ በፖለቲካ ተቃውሞ እየተናጠችበት ያለበት ወቅት ነው ። የፖለቲካ ንጠቱ ( Political turmoil) ምን እንደሚወልድ አወዛጋቢ የሆነበት አመታት ናቸው ። አሁን የምንገኝበት ወቅት ለፖለቲካ ተንታኞች ፈታኝ የሆነበት ወቅት ይመስለኛል ።

ለመሆኑ ከሃይለማሪያም ጀርባ ሆኖ አሻንጉሊቱን የሚያዘው ማነው ??
አባይ ፀሃዬ ነው? ስብሃት ነጋ ነው? ሳሚራ የኑስ ነው ? ጌታቸው አሰፋ ነው? ደብረ ፂዮን ነው? ማነው? ማነው ማነው? ሃይለማሪያም ደሳለኝ የተባለ ግራማፎን ካሴት አጉርሶ የሚያስወራው ማነው?

መቼም ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ፈጣሪ ለጉድ የፈጠረው ነው ። በኢትዮጵያ የታሪክ መፃህፍት የዚህን ሰው የአሻንጉሊትነት ታሪክ የተጋራ አምሳያ አላነበብኩም ። ቅድም ከላይ የጠቀስኩት ስሁል ሚካኤል ያስቀመጠው እጄ ቆራጣው የ 70 አመቱ አዛውንት አፄ ዮሃንስ እንኳን አንድ አመት ብቻ አሻንጉሊት ሆኖ በስሁል ሚካኤል መዘወሩ ስለአስመረረው “እምቢኝ ” ብሎ ሞቱን መርጧል ።

ሃይለማሪያም ደሳለኝን ካለፉ የኢትዮጵያ መሪዎች ጋር ማነፃፀር ከባድ እንደሆነ ይገባኛል ። እሱም ራሱ “መሪ ነኝ ” ብሎ ደፍሮ ለህሊናው የሚናገር አይመስለኝም ያውቀዋላ ። ከሌሎቹ መሪ ከነበሩት ማወዳደር ቢከብደንም እስኪ ከልጅ ኢያሱ ጋር እናነፃፅረው ።
ልጅ ኢያሱ ስልጣን ሲይዝ 13 አመት ታዳጊ ልጅ ነበር። ሃይለማሪያም ስልጣን “በየሰዘበት ” ወቅት የ 55 አመት ሰው ነበር ።
ልጅ ኢያሱ በ 13 አመት እድሜው “ሞግዚት አልፈልግም ” ብሎ አገር ማስተዳደር ጀመረ ። ብዙ ለውጥ አመጣ ። ኋላ ቀር የነበረውን እና ለዘመናት ረግቶ የነበረውን “ሌባሻይ ” እና “ቁራኛ ” የተባለውን የፍትህ ስርአት አስወግዶ በዘመናዊ ፍትህ ስርአት ተካው። በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ዘመናዊ የፖሊስ ሰራዊት አቋቋመ ፣ ዘመናዊ ኦዲት ሲስተም ተከለ ፣ በሃይማኖትም በኩል ትልቅ ለውጥ አመጣ ። ከሁሉም የበለጠ በሰማይ በምድሩ የተከበሩ የነበሩትን እነ ራስ አባተ ቦያለውን በማሰር ስልጣን እንዳለው ለህዝቡ አረጋገጠ ። ልብ በሉ ይሄ የ 13 አመት ልጅ ነበር ።
አሁን ስለሃይለማሪያም ምን ላውራ ? ባስብ ባስብ ምንም አላገኘሁም ። ደከመኝ ።

ሰሞኑን እንደምንሰማው ህውሃት ቢያንስ ለሁለት ቢበዛ ለሶስት ተከፍሏል ይባላል ። ይህ በሆነበት ሁኔታ የሃይለማሪያም ደሳለኝን “ስሁል ሚካኤል ” ማወቅ ብዙ ጥቅም አለው። ከአመት በፊት በኢህአዴግ ውስጥ በተደረገ ግምገማ ሃይለማሪያም ብልጭ ብሎበት ስብሃት ነጋን ” ስጋ እንዳየ ጩልሌ ዙሪያየን ሲዞረኝ ይውላል ” ብሎ ተናግሮ ነበር ። ሃይለማሪያምን የሚያዘፍነው ድጄ ስብሃት ነጋ ይሆን እንዴ? ።

በህውሃት ሰዎች ዘንድ ለአመታት ብሃት ነጋ “King Maker ” እንደሆነ ይወራል ። ሰውየው ኦፊሻል የሆነ የፖለቲካ ስልጣን ባይኖረውም እንደፈለገ ሲዘላብድ ይውላል ።
ነጋሶ ጊዳዳም በፃፈው መፅሀፍ ” ፕሬዚደንት በነበርኩበት ወቅት አቦይ ስብሃት እሁድ እሁድ ቤተመንግስት እየመጣ ዋና እንዋኝ ይለኝና በምንዋኝበት ወቅት ትእዛዝ የሚመስል ነገር ጣል አድርጎብኝ ይሄዳል ” ብሎ ነበር ። አባይ ፀሃዬም ቀላል አይደለም ።እንደ ልደቱ ተንሸራታችነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ። ሳሞራም ቢሆን ከጀርባው ያለው ሃይል ቀላል አይደለም ።

የሃይለማሪያም ” ስሁል ሚካኤል ” ማነው? ይሄ ሰውዬ ራሱ ደክሞ እኔንም አደከመኝ ።እኔም ይሄው ” አፋልጉኝ? “እላለሁኝ። ሃበሻ ሲተረት “ሙት ወቃሽ አትሁኑ ” ይላል ። እኔም ዛሬ ሃይለማሪያም የተባለ ሙት ወቃሽ ሆንኩኝ መሰለኝ። ይቅር ይበለኝ! !