Tuesday, April 4, 2017

መጀመሪያ ባለስልጣኖቹ የአህያ ስጋ መብላትን በደንብ እንደተለማመዱ ግንዛቤ ይያዝበት | ሸንቁጥ አየለ


ወያኔ የአህያ ስጋ በቻይና ነጋዴዎች በኩል ኤክስፖርት እንዲደረግ ሲፈቅድ የኢትዮጵያ ህዝብ መንፈሱ እንደ ሚበሳጭ : ልቡ እንደሚያዝን: የመዋረድ ስሜት እንደሚሰማዉና ተስፋ መቁረጥ እንደሚንጸባረቅ በደንብ ያዉቃል::የኢትዮጵያ ህዝብ እስላሙም ሆነ ክርስቲያኑ ወይም ሌላ እምነት ያለዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የባህል እና የመንፈሳዊ መሰረቱ ይሄን ነገር አጥብቆ የሚጽዬፈ እንደሆነ ያዉቃል::ሆኖም ወያኔ ሆን ብሎ የኢትዮጵያ ህዝብን መንፈሳዊ መሰረተ ለማዋረድ ብሎም የባህል እሴቱን ወደ አልቦ ለመክተት ማንኛዉንም የጸረ ኢትዮጵያዊነት ስነልቦና የዉጭ ባህል እያመጣ ኢትዮጵያ ህዝብ መሃል ይደፋል:: በዚህም ህዝቡን ተስፋ እንዲቆርጥ: ከመንፈሳዊነት እንዲላቀቅ: ባህል የሌላዉ ህዝብ እንዲሆን : ስነልቦናዉ የተሳከረ እና ግራ የተጋባ እንዲሆን የመደላድል አዉድማዉን ይጥላል::

ኢትዮጵያዊነት የጋራ መገለጫ እሴቶች እና የጋራ ዉህድ መንፈሳዊ መሰረቶች እንዳሉት ብሎም እነዚህ ህዝባዊ መሰረቶች ህዝቡን እንዳስተሳሰሩት የሚያዉቀዉ ወያኔ ይሄን መሰረት መናድ እንዳለበት የወሰነዉ ጫካ ሆኖ ነዉ:: የዘራዉ የጎሳ ልዩነት: የሀይማኖት የእርስ በርስ መቃቃር: የታሪክ መቆሳሰል እና አለመተማመን ጭብጥ ብሎም የኢትዮጵያዊነት ህላዌን የመካድ ጥልቅ እርሾ የመጨረሻዉን ፍሬ የሚያፈራለት በኢንቨስትመንት እና በኢኮኖሚ ልማት ስም ኢትዮጵያዉያን ያላቸዉ መሰረታዊ የመንፈሳዊ: የባህል እና የስነልቦና እሴት ሁሉ ለመጨረሻ ጊዜ ተዋርዶ ሲበጣጠስ እንደሆነ አስልቶ የተነሳዉ ወያኔ ምናልባትም ወደፊት የሰዉ ልጅ ኩላሊት መገበያያ ማዕከል በገሃድ በሀገሪቱ እንዲኖር ሊፈቅድና ኢትዮጵያዊነት የመጨረሻዉ የባዶነት ስሜት ዉስጥ ጠልቆ እንዲገባ ሊያደርግ እንደሚችል ይታወቃል:: ለነገሩ ምን የቀረ ነገር አለ? ግን ብዙ የቀረ የኢትዮጵያዊነት እርሾ አለ::ወያኔ የማያዬዉ ::እኛ ኢትዮጵያዊያኖቹ ግን የምናዬዉ !
በነገራችን ላይ ከጥቂት አመታት በፊት ከተወሰኑ የወያኔ ባለስልጣኖች አንደበት በገሃድ የሚሰማ ንግግር ነበር::ይሄዉም ቻይና በሚሄዱበት ጊዜ አብዛኞች የአህያ ስጋ እየበሉ እንደመጡ በኩራት ይናገሩ ነበር::የፈረስ ስጋም በላን ሲሉ የተደመጡ ነበሩ:: ይሄን እኔ እራሴ በጆሮዬ ሁሉ ሰምቼ ዘግንኖኛል:: እንዴዉም በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ “ባህል እና የአመራር ስልት” የሚል አንድ ጽሁፍ አቅርቤ ነበር::እናም መጀመሪያ ባለስልጣኖቹ የአህያ እና የፈረስ ስጋ መብላትን በደንብ እንደተለማመዱ ግንዛቤ ይያዝበት::
የብልጽግና ጽንሰ ሀሳብ ሊቃዉንቱ በስፋት አብራርተዉ እንደ ገለጹት ሁል አቀፍ ብልጽግና (holistic development) በአንዲት ሀገር ዉስጥ ሊኖር የሚችለዉ ባህልን: መንፈሳዊነትን: ማህበራዊ መሰረትን: ህግን እና ፍትህን: ተቋማትን: ታሪክን: ስነልቦናን: ኢኮኖሚን: ፖለቲካን: አካባቢን : የሰዉ ሀብት ብልጽግናን እንዲሁም ሌሎችንም ተያያዥ ጉዳዮችን ሁሉ ያካተተ እና ግንዛቤ ዉስጥ ያስገባ የተሳለጠ የብልጽግና ፖሊሲ እና እስትራቴጅ ሲኖር ብቻ ነዉ ::ወያኔ ይሄን በደንብ ያዉቃል::ግን እርሱ ግቡ ኢትዮጵያን ማበልጽግ ሳይሆን ራዕይዉ ኢትዮጵያን ወደ አልቦነት ደረጃ በማዉረድ የዘቀጠ ማህበረሰብ የሚኖርባት ለአገዛዝ የምትመች የጎሳ ስብስብ የሆነች ስመ ሀገር ማድረግ ነዉ::እሱ ያለ ተቀናቃኝ እየጨፈረ እንዲኖር መሆኑ ነዉ::
የዝንጀሮን ቅኔ እዚህ ማጣቀሱ ግን መልካም ነዉ:-
የእግዜርን ነገር ምኑን አዉቀሽዉ :
ወይ እኔ እበላዉ አንቺ አርመሽዉ !
እናዳለች ዝንጀሮ ይሄ ሁሉ ደባዉ እራሱን የሚያጠፋ ብሎም ምናልባትም ደግሞ ኢትዮጵያዉያንን ባልታሰበ ሚስጥራዊ ኩነት የሚያስተሳስር እልህን የሚያጭር እርሾ ሆኖ ሊወጣ ይችል ይሆናል::

በነፃና ገለልተኛ አደራዳሪ ያልተመራ ድርድር ለህዝብ ጥያቄ ትክክለኛውን መልስ አያመጣም!

    


ገዥው ፓርቲ ግንቦት 2007 ዓ.ም. በተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫ መቶ በመቶ ድልን ተጐናፅፌያለሁ ብሎ አውጆ መስከረም 2008 ዓ.ም. መንግሥት ቢመሰርትም ጥቂት ወራትን እንኳን በሰላም ማስተዳደር አቅቶት ሀገሪቱ በተቃውሞ መታመስ ጀመረች፡፡
ይህ ሥጋት ያደረባቸው በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንም

Monday, April 3, 2017

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ላለፉት 20 አመታት ለበረከተው አሰተዋአዖኦ ለታላቅ ሽልማት እና እውቅና በቃ !!!

    


ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ ላለፉት ☞ 20 አመታት ለበረከተው አሰተዋአዖኦ ለታላቅ ሽልማት እና እውቅና በቃ !!!
FB_IMG_1491228273669

የ25ኛው የማኅበረ ግሩያን ዘረ ኢትዮጵያ ልዩ የእውቅ እና የአክብሮት ሽልማት ይካሄዳል ! መርሐ ግብር ቅዳሜ ሜይ 28 ቀን 2017 በአሜሪካን አገር ይካሄዳል።

በሚያካሂደው የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ” ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ” በሚል መርህ ዘንድሮ ለ25ኛ ጊዜ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ይካሄደል።

ዘንድሮ 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በአሉን የሚያከብረው ማኀበረ ፣የዘር ግንዳቸው ከኢትዮጵያ የሚመዘዝና እንዲሁም በትውልድ የሌላ አገር ተወላጅ ሆነው ፤ለኢትዮጵያ መልካም ነገርን በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ያበረከቱትን በየአመቱ በሚያካሂደው
የእውቅናና የሽልማት መርሃ ግብር ፣ ክብር ለሚገባው ክብር ይሰጣል።

ዘንድሮ ማኀበረ የምስረታውን 25 ኛ አመት የብር ኢዮቤልዩ በልዩና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በተዘጋጀበት ወቅት፣ የ25ኛው አመት ልዩ የክብርና የእውቅና መርሐግብር ተሸላሚዎች መካከል #ልዩ_ተሸላሚ አድርጎ የመረጠው (y) ድምጻዊ #ቴዎድሮስ_ካሳሁን_ገርማሞን ነው !!!

✍ ቴዲን ልዮ ተሸላሚ የሚያደርገው በሥነ ፅሁፍ ዘርፍ ታላቅ የግጥም ፀሐፊ፣ በሙዚቃው ዘርፍ ታላቅ ድምፃዊና የዜማ ደራሲ፣ በታሪክ ዘርፍ ስለ ኢትዮጵያ ምድሯና ህዝቦቿ፣ባህሏና ትውፊቷ፣ ጀግኖቿና አንፀባራቂው ድሏ፣ የሃይማኖት መቻቻልና የታላላቅ ልጆቿን ገድል በሥራዎቹ በማሳየቱና ለትውልዱ ልዩ የታሪክ ተናጋሪ በመሆኑ እና የበርካታ የሙያና የሰብአዊ አገልግሎቶች ባለቤት በመሆኑም ጭምር ነው።

✍ ቴዲ አፍሮ ለሕዝብ ባቀረባቸው አራት የሙዚቃ አልበሞቹና በርካታ ነጠላ ዜማዎቹ እስካሁን በኢትዮጵያ ምድር ድምፃዊነትን ከግጥምና ዜማ ደራሲነት ጋር አዳምሮ በብዛትም፣ በጥራትም በሕዝብ ተቀባይነት በማገኘትም እንዲሁም በሽያጭም ተወዳዳሪ ያልተገኘት የሙያ ባለቤት ነው ።

♦በሼመንደፈር ☞ የሐይማኖት መቻቻልን ፣
♦በጥቁር ሰው ☞ አርበኝነትን፣
♦በያስተሰርያል ☞ እርቅን ፣
♦ በካብ ዳኀላክ ☞ የመለያየት ከባድነትን፣
♦በፀባዬ ሰናይ ☞ ትዳርን ፣
♦በአቡጊዳ ☞ ፊደል አስቆጣሪዎቻችንን ፣
♦በስለ ፍቅር ያሳለፍነው ዘመናችንን፣
♦በሰባ ደረጃ ☞ የጥንቷን ሸገርን፣
♦ በኡኡታዬ ☞ የዘመናት ጩኸታችንን ፣
♦በታሪክ ተሰራ እና ☞ ኃይሌ ኃይሌ የኦሎምፒክ ውሏችንን፣
♦በግርማዊነትዎ ☞ አፄ ኃይለ ሥላሴንና ፓን አፍሪካን፣
♦በዋልያ ☞ ብሔራዊ ቡድናችንን፣
♦ በኮርኩማ አፍሪካ ☞ ስደታችንን እና ስለ በርካታ የሰው ልጆች የሕይወት ውጣ ውረድን፣ ስኬትን፣ ሃዘንን፣ ደስታን ወዘተርፈ የሚዳስሱ ስራዎቹን ላለፉት ☞ 20 አመታት ለአድማጭው አድርሶ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን አገኝቷል።

ክብር ለሚገባው ክብር እንስጥ ! ፍቅር ያሸንፋል !!!

የዚህ የዜና ምንጭ እና መረጃ © ጴጥሮስ አሸናፊ ነው። እኔም (ይድነቃቸው ከበደ) በእንዲህ መልኩ መረጃው እንዲዳረስ አድርጌያለሁ። ለቴዲ ካለኝ ክብርና አድናቆት ብቻ !

የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ኦሮሞው በማንነቱ በስሙ ጭምር እንዲሸማቀቅ ይደረግ ነበር?… ለምን? (ኤርሚያስ ቶኩማ)


ሳተናው
By ሳተናውApril 3, 2017 04:49

 2  544  546

ቴዲ አፍሮ የቀድሞ ነገስታትን ስም ጠርቶ ክብር መስጠቱን ተከትሎ አንዳንድ አዛውንት ፖለቲከኞች ያንን የኢቢኤሱን ጋዜጠኛ ጨምሮ ደጋፊዎቻቸውን ለማሳመን የሚጠቀሟቸው ቃላቶች ያስቁኛል። ከእነዚህም መካከል አንደኛው በቀድሞው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ኦሮሞው በማንነቱ በስሙ ጭምር እንዲሸማቀቅ ይደረግ ነበረ የሚለው ትልቁ ማሳመኛቸው ነው ሆኖም ይህ ደጋፊን ለማፍራት ሆን ተብሎ የተቀመረ ማሳመኛ ነው፤ ሰው በስም መጠሪያው እንዲሸማቀቅ ይደረግ የነበረው አሁንም የሚደረገው በኦሮሞው ላይ ብቻ ሣይሆን በደቡቡም በአማራውም ላይ ጭምር ነው።
ጥሩ ምሳሌ ልንገራችሁ ድምፃዊ ኤልያስ ተባባል የተወለደው ጎንደር ነው አዲስ አበባ ሔዶ የሙዚቃ ካሴት ሊያሳትም አሳታሚዎችን ሲጠይቅ ትክክለኛ ስሙን ልዋጥህ ተባባልን ካልቀየረ  ህዝቡ ካሴቱን እንደማይገዛው ተነግሮት ነው ከልዋጥህ ተባባል ወደኤልያስ ተባባል የቀየረው። የማዲንጎ አፈወርቅም ስም ተቀይሮ እንደሆነ ሰምቻለሁ እርግጠኛ ባልሆንም ትክክለኛ ስሙ ተገኝ አፈወርቅ ነው የሚል ነገር ሰምቻለሁ።
ማዲንጎ አፈወርቅ ስሙን ብቻ ሳይሆን ስታዲየም ዙሪያ ይዞት ይዞር የነበረውን ማሲንቆና የለበሰውን ቁምጣ ሁሉ ጥሎ ሁለት ጆሮውን ተበስቶ ሱሪውን ዝቅ አድርጎ እንዲሄድ ከፍተኛ የማንነት ቀውስ ውስጥ እንዲገባ ሆኗል።
በርካታ የአማራ ተወላጅ አዲስ አበባ ሲገባ ከድላርጋቸው ወደዳጊ ከእማዋይሽ ወደኤሚ ከፈለቀ ወደፊሊሞን ከአንዳርጋቸው ወደኤንዲ ከሙላቱ ወደሙለር ስሙን ይቀይራል። ይህንን የሚያደርጉት በስማቸው ምክንያት አዲስ አበባ ላይ የሚያጋጥማቸውን ነገር በመፍራት ነው። በኦሮሞውም ላይ የሆነው ተመሳሳይ ነው በርካታ ኦሮሞዎች አዲስ አበባ ሲሔዱ ስማቸውን ከጋዲሳ ወደጌዴዮን ከአቶምሳ ወደአትናትዮስ ይቀይራሉ።
በነገራችን ላይ ሰውን በስም ማሸማቀቅ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም ሀገር ያለ ነው ለምሳሌ የጀርመንን ብንመለከት Schartzmugel የሚለው ስም መጠሪያቸው የሆኑ ሴቶች በብዛት በስማቸው ይቀልድባቸዋል የእነርሱ ስም ዘመናዊ እንዳልሆነና እንዲቀይሩት ሲነገራቸው ልትሰሙ ትችላላችሁ በአንፃሩ Katrina በጣም ተወዳጅ የጀርመን ሴቶች ስም ነው።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው በስሙ እንዲያፍር የሚደረገው ጎሣ እየተመረጠ አይደለም ከሁሉም ጎሳዎች ስም እየተመረጡ አዲስ አበባ ላይ ሰው ለመቀለድ ይሞክራል የእስራኤል ስሞች እንደዘመናዊ ስም ሲታዩ ሀገርኛ ስሞች መሸማቀቂያ ናቸው።
ደሚቱ የሚለው የኦሮምኛ ስም ሲተረጐም ማሪቱ እንደማለት ነው ሆኖም በዚህ ሰአት ልጅህን ማሪቱም አልካት ደሚቱ ስሟን ሰምቶ የሚስቅ ሰው አታጣም ይህ የሰው ልጅ ለስም ካለው ግምት የሚነሳ ነው እንጂ አንዱን ጎሣ በመናቅ ሌላውን ለማሞገስ ተብሎ የሚደረግ ነገር አይደለም አልነበረምም።
የቀድሞ ነገሥታት የፈጸሟቸው ስህተቶች መኖራቸው እሙን ነው ሆኖም ኢትዮጵያን እንደኢትዮጵያ ለማቆየት የከፈሉት መስዋዕትነት ከሰሩት ስህተት ይበልጣል ለዚህ ደግሞ አሉባልታ እያወሩ ሊለያዩን የሚሞክሩትን እንደኢቢኤሱ ጋዜጠኛ ያሉትን በሥራቸው እንዲያፍሩ በማድረግ እንደቴዲ አፍሮ እና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ያሉ ሀገር ወዳዶች ለሚሰሩት ሥራ ክብር ልንሰጣቸው እንጂ ልንወርፋቸው አይገባም።
ኢትዮጵያውያን ከሚለያዪን ነገሮች ይልቅ የምንመሳሰልባቸው ነገሮች እልፍ አእላፍ ናቸው፤ ሊለያዩን የሚሯሯጡትን እያስወገደን አንድነታችንን ማጠናከሩ ለሁላችንም መልካም ነው።
ኤርሚያስ ቶኩማ

Sunday, April 2, 2017

Breaking: በጎንደር ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ቦምብ ፈነዳ


  


 2  1184  1186


(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ከተማ ማራኪ ካምፓስ አቅራቢያ የሚገኘው ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል በፈነዳ ቦምብ የተነሳ ጎንደር ከተማ ስትታመስ ማምሸቷ ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳደረሱን መረጃ ከሆነ በሆቴሉ ቦምቦ የፈነዳው 3:30 አካባቢ ነው:: በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ ለማጣራት ዘ-ሐበሻ እየሞከረች ሲሆን በኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት መረጃውን ወዲያው ለማግኘት አልቻልንም::
እንደምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ የሕወሓት መራሹ መንግስት ወታደሮች ከተማዋን ሲያምሱት የዋሉ ሲሆን ከሆቴሉ ፊት ለፊት በሚገኘው ኡስማን መስጊድ በመገባትም ብርበራ ማድረጋቸው ተሰምቷል::
ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽና የተሟላ ሬስቶራንትን የያዘ ነው::
ለቦንቡ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ኃይል እስካሁን ባይኖርም ሰሞኑን በተደጋጋሚ በባህርዳርና ጎንደር ተመሳሳይ አደጋዎች እየደረሱ መሆኑን ዘ-ሐበሻ አስቀድማ መዘገቧ አይዘነጋም:
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን::

በወልድያ ከተማ የትግራይ ተወላጆች መንግሥት ትጥቅ እንዲፈቅድላቸው ጠየቁ – (ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው )



By ሳተናውApril 2, 2017 10:45






 1  81  82
ከባለፈው ሐምሌ ወር የዐማራ ተጋድሎ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በወልድያ ከተማ አዳጎ እና ፒያሳ የሚባሉ የንግድ ተቆጣጥረው የሚገኙ የሕወሓት አባላት የትግራይ ተወላጆች መንግሥታቸው የተለየ ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀው የፀጥታ አካላት ተመድበው ሲጠብቁ ቆይተዋል፡፡
ሆኖም ባለፈው ሳምንት ለሰሜን ወሎ ዞንና ለወልድያ ከተማ አስተዳደር የንግድ ተቋማችንና ራሳችን ለመጠበቅ መንግሥት ትጥቅ ሊያስታጥቀን ይገባል በማለት የትግራይ ተወላጆች በሕብረት ጥያቄ እንዳቀረቡ ሰምተናል፡፡ በወልድያ ከተማ አብዛኛዎቹ የንግድ ተቋማት በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ የአካባቢው ተወላጆች በልዩ ልዩ ሰበብ ከንግድ እንዲወጡ አሊያም አካባቢውን ለቀው እንዲሔዱ ይገደዳሉ ተብሏል፡፡
በከተማው የንግድ እንቅስቃሴ ማዕከል የሆኑት ከአዳጎ እስከ ፒያሳ ድረስ ሁሉም በአንድ ብሔር ተወላጆች የተያዘ እንደሆነ ነው ነዋሪዎች የሚገልጹት፡፡

ሕወሃት ረግጦ ለመግዛት ወሰኗል- ድርድሩም ከሽፏል #ግርማ_



10574269_10102022508184183_7482740824080748847_n
“ድርድሩ” ከሽፏል። ሕወሃት በሶስተኛ አካል ለመደራደር ፍቃደኛ አልሆነም። አንድ ጦማሪ እንዳስቀመጠው ” ከኛ ውጭ ማንም አደራዳሪ አይገባም። በሀገር ጉዳይ፣ ከፈለጋቹ እኔ አደራድራለሁ፣ ካልሆነም በዙር እርስ በእርሳችን እንደራደራለን” በሚል ህወሃት የመጀመሪያም/የመጨረሻም ውሳኔዉን ዛሬ አሳውቋል።
ሰማያዊ፣ መኢአድና ኢዴፓ በዋናነት ሶስተኛ አካል በሌለበት መደራደር የማይታሰብ መሆኑ በመግልጽ አገዛዙ ከግትር አቋሙ እንዲለሳለስ ተማጽኖ ቢያቀርቡም፣ ገዢው ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ የደረቀ አቋም በመያዙ  ስብሰባው ተበትኗል። ኢሕአዴግ ዉስጥ ካሉ ምንጮቼ በደረሰኝ መረጃ፣ ይህ ዉሳኔ የሕወሃት ዉሳኔ ነው።
ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ኢዴፓ በአመራር ደረጃ መክረው በይፋ አገዛዙ “ለመደራደርና የአገርን ችግር በዉይይት ለመፍታት ፍቃደኛ አለመሆኑ” ያሳወቃሉ ተብሎ በተጠበቀው መሰረት፣ ሰማያዊና መኢአድ አቋማቸዉን ግልጽ በማድረግ፣ ያለ ሶስተኛ አደራዳርሪ ድርድር እንደማይኖር ገልጸዋል።
ሌሎች ቀደም ሲል ግብስብስ ድርጅቶች ብዬ ያልኳቸውን በመያዝ አገዛዙ “ከተቃዋሚዎች ጋር ዉይይት እያደረግን ነው” የሚል ዳንኪራ ለማሳየት መሞከሩ አይቀርም። ያሳያልም። ሆኖም መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ ምን አልባትን ኢዴፓ የሌሉበት የ”የተቃዋሚዎችን” ዉይይት ማንም ለቁም ነገር አይቆጥረውም።
ለሰማያዊ፣ መኢአድ፣ መድረክና ኢዴፕ አመራሮች በዚህ አጋጣሚ ያለኝን ትልቅ አክብሮት መግልጽ እወዳለሁ። ትእግስተኛ ሆነው፣ ከደጋፊዎቻቸውና ከብዙ ወገኖች ጠንካራ ትችት እየቀረበባቸውም በመርህ ደረጃ ዉይይትን መሸሽ አያስፈለግም በሚል አስተዋይ ዉሳኔ ብመወሰን፣  አገርና ህዝብን በማስቀደም የአገር ችግር በሰላም እንዲፈታ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል። ለትግሉ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል።፡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አመሰግናቸዋለሁ።
አገር ቤት ያሉት ተቃዋሚዎች አንዱ ሊሰሩት የሚችሉት የነበረው ነገር በድርድር ለዉጦችን ማምጣት ነበር። ያንን ሞክሩ ግን ያን በር ሕወሃት ዘጋው። መቼም በአንድ ብቻ አይጨበጨብም። አገዛዙ የአገርን ችግር በንግግርር ለመፍታት ፍቃደኛ ካለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ የሆነው አገዛዙ ራሱ ይሆናል።
ሴማያዊ/ኢዴፓ/መኢአድ መድረክ ጽ/ቤቶቻቸውን ዘግተው ወደ ግል ኑሯቸው ይሂዱ አልልም።፡ምንም መንቀሳቀስ ባይችሉም፣ ራሳቸውን ከራዳር አስወጥተው ሊሰሩት የሚችሉት ነገር ካለ (በግሌ ሁሉንም ነገር ታፍኖ ይሄን ሊስሩ ይችላሉ የምለው የለም) ስራቸውን ይቀጥሉ። ወደፊት ነገሮች ከተለወጡና ከተስተካከሉ ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ነገሮች ስለሚኖር ባይበታተኑ ጥሩ ነው።
አገር ቤት ያሉ ሰላማዊና ሕጋዊ ድርጅቶች እነርሱ ማድረግ ያአለባቸዉን አድርገዋል። ሆኖም ግን ሕጋዊ ያልሆኑ እጅግ በጣም በርካታ ድርጅቶች አሉ። አሁን እነርሱ መንቀሣቀሥ አለባቸው።የሚያደርጉት ትግል ትልቅ reconfiguration ያስፈልገዋል። አገር ቤት ያለው ሕጋዊና ሰላማዊ ትግልን መቼም ቢሆን የተጨበጠ ስራ ለመስራት ዝግጁነትና አቅም ካለው (አሁን ባለው ሁኔታ አይኖረውም) መደገፍ ያለበት ትግል ነው። ሆኖም ግን ለሁሉም ጊዜ አለው እንደሚባለው፣ አሁን አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መሸከም ከሚችሉት በላይ የሆነባቸው መሰለኝ። ስለዚህ ትግል የዱላ ቅብብሎሽ ነዉና፣ ዱላዉን ሌሎች መረከብ አለባቸው። ወደ ሰላማዊ ግን ሕጋዊ ወዳልሆነ፣ የእምቢተኝነት ትግል መኬድ አለበት።