Tuesday, November 8, 2016

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ዙማ በኢትዮጵያ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አስተላለፉ፡፡


የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ዙማ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አስቸኳይ የፖለቲካ ውይይት ማድረግ እንደሚገባ በመግለጽ ጥሪ አስተላለፉ፡፡በአገሪቱ የመጨረሻ መፍትሄ ለማግኘት መነጋገር በጣም ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
ወይሮዋ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግስት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባር ላይ ሲያውል የዜጎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች መከበራቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ተቃውሞውን ተከትሎ የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ዕቀባ መደረጉን የተቃወሙት ዙማ መንግስት አገልግሎቱን እንዲለቅም ጠይቀዋል፡፡
ሊቀመንበሯ አስቸኳይ አዋጁ በስራ ላይ በሚውልበት ወቅት የተረጋጋና ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲደረግ በመጠየቅ መንግስት የዜጎችን መረጃ የማግኘት፣በግኑኝነት ቴክኖሎጂዎች የኢንተርኔት አገልግሎትና የማህበረሰብ ሚዲያዎችን ይጨምራል የመጠቀም መብትን ግምት ውስጥ በማስገባት አለመጓደላቸውን እንዲያረጋግጥ አሳስበዋል፡፡

በለንደኑ የኦሮሞ ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን ያለው ኦቦ ሊበን ዋቆ ማነው? /ኪያ ቲላ /


ኦቦ ሊበን ዋቆ ማነው? በለንደኑ የኦሮሞ ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን ያለው ኦቦ ሊበን ዋቆ ማነው?  /ኪያ ቲላ /
የለንደኑ የኦሮሞዎች ስብሰባ… ወያኔን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ አሽቀንጥሮ ለመጣል በመደረግ ላይ ባለው ማንኛዉም አይነት ትግል ውስጥ ተሰማርቶ ለሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ!!! አንዳንድ ግዜ እራሴንም ሆነ የሀገሬን ልጆች ክፉኛ እታዘባለሁ፣ ያለንበትም ዝብርቅርቅ ህይወት እራሳችን የፈጠርነው በመሆኑ በጣም አፍራለሁ። ለዚህም ነበር የስው ልጅ ማንነት መለኪያ ስለሆኑት ሶስቱ ጽንሰ ሃሳቦች እውቀት፣ እምነትና ብልህነት ለመፃፍ የተነሳሳሁት። እኛ የዚህ ዘመን ትውልድ የሆንን ኢትዮጵያውያኖች እምነትና ብልህነት እንደ ቁምጣ ያጥረናል ብል ማጋነን አይሆንብኝም።
ምክንያቱም ማንነቱንና የሚሰራውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ትውልድ ሁሉ በቀላሉ ወደ ነፈሰበት አብሮ አይነፍስምና። ሰሞኑን ለንደን ላይ የኦሮሞ ልጆች ተሰባስበው ወጥና ሁሉን አቀፍ የሆነ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲመክሩ እንደ ሰነበቱ ሁላችንም የምናውቀው ነው። በዚሁ ስብሰባ ላይ ብዙዎቹ ያነሱት ነጥብ ጥንካሬ ያለው ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦች የስነዘሯቸው ሃሳቦች ደግሞ ብዙ ኢትዮጵያዊያኖችን ሲያስቆጣ በተቃራኒው ትግሬዎችን አስፈድቋል። ይህንን የሚያስቆጣ ሀሳብ ከሰነዘሩት ውስጥ አንዱ ሊበን ዋቆ ይባላል። ይህ ሰው ማን እንደሆነና አላማውስ ምን እንደሆነ ከነባር የኦነግ አመራሮችና ወያኔዎች ውስጥ ሆነው መረጃ በሚስጥር ከሚያቀብሉን አባሎቻችን በደረሰኝ መረጃ ላይ በመመስረት የነበረውን አጠቃላይ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃይቁ ምን እንደነበር ለማስጨበጥ እሞክራለሁ። ሊበን ዋቆ የተወለደው ነጌሌ ቦረና ከተማ ውስጥ ነው። ይህ ሰው እድሜውን በሙሉ በህብረተሰቡ አመለካከት እንደ ወራዳነት በሚቆጠሩ ተግባሮች (ስካር፣ ሌብነት) የታወቀ ሲሆን የኦሮሞ ልጆችን ለእርድ አሳልፎ መስጠትን ደግሞ ልዩ ስጦታው በማድረግ እስከ ዛሬ ይዞት ዘልቋል። አሁን ደግሞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የመኖር ህልውናውን ባጣበትና ከወያኔ ጋር ጉሮሮ ለጉሮሮ እየተናነቅ በመውደቅ ላይ ባለበት በዚህች አጣብቂኝ ወቅት ዩኒፎርሙን ቀይሮ በአዲስ መልክ ብቅ ለማለት ችሏል። ሊበን ዋቆ በ1963 አስመራ ከሚገኘው የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋም (TTI) ተመርቆ በመምህርነት በጋምቤላና በአርሲ አገልግሏል። አርሲ ውስጥ በመስራት ላይ እያለ የኢህአፓ አባል በመሆን ለደርግ በሰላይነት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህን ወቅት ከእሱ ጋር የታሰሩት የኢህአፓ አባላት በሙሉ ሲረሸኑ እሱ ግን በነፃ ተለቆ በወቅቱ ያበረከተው የተሳካ የስለላ ስራ እንደ ውለታ ተቆጥሮለት ስኮላርሽፕ ተሰጠውና ወደ ቺኮዝሎቫኪያ ተላከ። ከቺኮዝሎቫኪያ ሲመለስ ወለጋ ተመድቦ አብዲሳ አጋ ትምህርት ቤት ውስጥ በመምህርነት እንዲሰራ ነጆ ተላከ። ነጆ በገባ ማግስት ስለትምህርት ቤቱና ስለ ሰራተኛው ምንም አይነት ግንዛቤ ሳይኖረው ሰራተኛውን ማመስ ጀመረ። በነጆ ከተማ ተማሪዎችን ለሰላማዊ ሰልፍ ይዞ መስከረም ሁለት ለሚደረገው ስልፍ ድጋፍ ለመስጠትና የደርግን ትኩረት ለመሳብ ከዚህ በፊት ማንም ሰው ሞክሮት በማያውቀው ሁኔታ ተማሪዎችን ድጋፍ ሰልፍ ከትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ይዞ በመውጣት ድጋፍ የሰጠ ቀንደኛ የደርግ ካድሬ የነበረና ብዙ ሰው ለእስርና ለሞት አሳልፎ የሰጠ ሰው ነው። በዚሁ ትምህርት ቤት ውስጥ ለደርግ ሊሰሩ የሚችሉ ካድሬዎችን በመመልመል ሥራ ላይ ተጠመደ። በሳምንት አንድ ቀን የርእዮተ አለም ትምህርት የሚሰጥበትን የውይይት ክበብ አቋቋመ። ከዚያም ሰዎችን ሁሉ ማንነታቸዉን በመምሰል (ለምሳሌ የደርግ ካድሬ ሲያይ ካድሬ በመሆን፣ ተቃዋሚዎችን ሲያገኝ ተቃዋሚ በመሆን) መቅረብን አጠናክሮ ቀጠለ። በዚያ ጊዜ በምእራብ በኩል የሚደረገው የኦነግ እንቅስቃሴ ገና ለጋ ሰለነበር በተገኘው አጋጣሚ እነሱ ውስጥ ሰርጎ በመግባት በእንጭጩ ለማስቀረት ብዙ ጥረት አድርጎ ነበር። እድሜው ከ35 ዓመት በላይ መሆኑ እየታወቀ የነጆ ወጣቶች ማህበር ፀሐፊ ሆኖ ተመረጠ። ብዙም ሳይቆይ ደርግ የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ሲያቋቁም ከመጀመሪያዎቹ ሶስት የነጆ ተመራጮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመረጠ። የነጆ አስተዳዳሪ የነበሩትን አቶ ደበሌን እንኳን በመቅደም የደርግ ፓርቲ አባል ሆነ። ከዚያም አሁን ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩትን ሁለት ጓደኞቹን ሀብታሙ ብርሃኑንና ዶ/ር መዝገቡ ኢፋን ወትውቶና ቃል ገብቶ በማሳመን የፓርቲ አባል ካደረጋቸው በኋላ ከኋላ ሆኖ ማስወጋቱን ተያያዘዉ። ከዚያም ሀብታሙ ብርሃኑ ፀረ ፓርቲና ፀረ የኢትዮጵያ አንድነት ተብሎ ተፈረጀና በድብቅ እንዲገደል ተወሰነበት። አንድ ቀን ማታ በርይሁን ደበሌ የተባለ ሰው ሀብታሙን በሽጉጥ አፈሙዝ እራሱ ላይ መትቶት ተኩሶ ሊገድለው ሲሞክር ለጥቂት አምልጦ ነጆ ፓሊስ ጣብያ ገባ። ከዚያም በርይሁን ደበሌ ሌላ አባተ ይገዙ የተባለ ሰው ጨምሮ ፓሊስ ጣብያ ድረስ በመሔድ ሀብታሙን አስወጥተው ሊገሉት ሲሉ በወቅቱ የፓሊስ ጣብያው አዛዥ የነበረ አወል የሚባል ስው መሀል በመግባት ነፍሱን ሊያተርፈው ችሏል። ኋላም ሀብታሙ ህይውቱን ለማትረፍ ነጆን በአስቸኳይ ለቆ በመውጣት ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመልሶ ገባ። በሌላ በኩል ደግሞ ክትትሉ በመዝገቡ ላይ ተጠናክሮ ቀጠለ። በኦነግ አባልነት ፈርጀውት መግቢያ መውጫ አሳጡት። በድሉ ገ/ሚካኤል የሚባል የደርግ ባለስልጣን መዝገቡን በደንብ ስለሚያውቀውና ስለሚወደው ከመገደል እንዳተረፈው መረጃ ሲደርሰው መዝገቡ የሥራ ዝውውር ወደ አዲስ አበባ በመጠየቅ ነጆን ለቆ ለመወጣት በዝግጅት ላይ መሆኑን ስለደረሱበት እምሩ የተባለ የነጆ አስተዳዳሪ መዝገቡ እንዲታሰር ትእዛዝ ሰጠ። አወል ተብሎ የሚጠራ የነጆ ፓሊስ ጣብያ አዛዥ መዝገቡን ለረጅም ጊዜ ስለሚያውቀው በሚስጥር አስጠርቶ ስላለው ጉዳይ ካስረዳው በኋላ በአስቸኳይ ነጆን ለቆ እንዲወጣ ነገረው። ከዚህ ሁሉ እንቅስቃሴ ጀርባ ሆኖ ነገሮችን ሲያሽከርክር የነበረው ሊበን ዋቆ እንደነበር ኋላ በማስረጃ ተረጋግጧል። ሊበን ዋቆ ፍላቴ በተለያየ ጊዜ ሊቀርባቸው ከሞከረው የነጆ ነዋሪዎች ውስጥ ማርቆስ አብርሃም፣ የቦጂው ተወላጁ መምህር ንፍጣለም፣ የነጆ አስተዳደር የነበረ ጂፋር ደበሌ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው። ኋላም ማርቆስ አብርሃም ለአጭር ጊዜ ወደ ቤጂ በመሄድ ከኦነግ አባሎች ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና አብሮ ለመስራት ሲንቀሳቀስ ቆይቶ ተመለሰ። ማርቆስ ወደ ነጆ እንደተመለሰ ከላይ ስማቸው ከተጠቀሰው ማለትም ከመምህር ንፍጣለም፣ ከጂፋር ደበሌና ሌሎችም ጋር በመሆን ከሊበን ዋቆ ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ፈጥረው የኦነግን እንቅስቃሴ ለማጠናከር መስራትን ቀጠሉ። ብዙም ሳይቆይ ከሊበን ዋቆ በስተቀር ሁሉንም ግለሰቦች ይዞ ለማሰር ደርግ ወደ ነጆ ሰራዊት አሰማራ። ማርቆስ እጄን አልሰጥም በማለት ሲታኮስ ቆይቶ ሲገደል የተቀሩትን ደግሞ ደርጎች ሰብስበው አሰሯቸዉ። ሊበን ዋቆ በምእራቡ በኩል የሚንቀሳቀሰውን የኦነግ ሰራዊት ለማስመታት በደርግ ስልጠና የተሰጠው ሲሆን ግዳጁንም በአግባቡ ስለፈፀመ የኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር ተደርጎ በመሾም ወደ ንጉሴ ፋንታ ነቀምት ተላከ። ከዚያም ኦነግን ለመምታት በደንቢ ዶሎ፣ በቤጂ፣ በጊዳሚ፣ በአንፊሎ፣ በመንዲና ናጆራ የደርግ ሰራዊት እያሰማራ የኦነግ አባልና ደጋፊ የሆኑ የኦሮሞ ወጣቶችን ይዞ ማሰርንና መግደልን አጠናክሮ ቀጠለ። ብዙ ሳይቆይ የሻምቡ አውራጃ አስተዳዳሪ ተደርጎ ተሾመ። ሻምቡ ለጥቂት ጊሴ በአውራጃው አስተዳዳሪነት ከሰራ በኋላ የቦረና አውራጃ አስተዳዳሪ ተደርጎ ወደ ደቡብ ተዛወረ። በ1987 ዓ.ም. ደርግ በመውደቅ ላይ መሆኑን ሲረዳ ከነትጥቁ ደርግን ከድቶ ለኬንያ መንግስት እጁን በመስጠት ቲካ የስድተኞች ካምፕ ተቀላቀለ። ኬንያ ውስጥ ሚስት አግብቶ ሶርሳ ተብሎ የሚጠራ ልጅ ወለደ። በ1991 ዓ. ም. ሚስትና ልጁን ኬንያ ውስጥ በመተው ወደ አሜሪካ ተጓዘና ኑሮውን ሜሪ ላንድ ውስጥ ታኮማ ፓርክ መሰረተ። በ1993 ዓ. ም. የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ፓርቲ አቋቋመ። ልጁ በኖሬዥያኖች እርዳታ ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ሊቀላቀው ሲፈልግ አባትነቱን ቢክድም በ DNA ምርመራ አባትነቱ በመረጋገጡ ምክንያት አሜሪካ ከመጣ በኋላ የመሰረተው ትዳር ፈረሰ። በ2013 ዓ.ም. ወደ ኬንያ በመሔድ ሀይማኖቱን ከክርስትና ወደ እስልምና ከቀየረ በኋላ የ22 አመት ልጅ አግብቶ ወደ አሜሪካ ተመለሠ። በኋለኛው የህይወት ዘመኑ በወዳጅነት የቀረባቸው ትግሬዎች ዲግሪ መግዛት ወይም በፎቶ ኮፒ ማሽን አባዝቶ ለአባሎቻቸው ማደል ባህላቸው ሰለሆነ እንደዚህ አይነቱ ዲግሪ ትግሬዎች ሲያድሉ ካልደረሰው በስተቀር ከየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የphd ማእረግ እንዳላገኘ ማረጋገጥ ችለናል። መለሰ ዜናዊ እንደሞተ ለቅሶ ላይ ከእኔ በስተቀር ሌላ ሰው ላሳር ሲል እንደሰነበተ የአይን ምስክሮችና ፎተግራፍ አረጋግጠውበታል። ኑኑ ተብላ የምትጠራው ልጁም ለወያኔው EBS አገልግሎትና በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የወያኔ ኤምባሲ ውስጥ እንደምትስራ አረጋግጠናል። ወንድ ልጁም እንደዚሁ። በዚህ የህይወት ወጣ ውረድ ውስጥ ሲዋዥቅ ነበር ትግሬዎች ሊበን ዋቆን አግኝተው የራሳቸውን አስተሳሰብ በማጥመቅ ተልእኮውን በብቃት እንዲወጣ ወደ ለንድኑ ኮንፍረንስ የላኩት። መቸም ትግሬዎች ስልጣን ላይ ለመቆየት ርካሽ ግለሰቦችን ፈልጎ የራሳቸው ማድረግንና ለሚያጠፉት የገንዘብ መጠን ደንታ እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ህዝብ አያቅም ማለት አልደፍርም። ግለሰቦች በህዝቡ እስካልተመረጡ ድረስ የህዝብ ውክልና ሊኖራቸው አይችለም። ማራመድም የሚችሉት የራሳቸውን እምነት ብቻ ነው! የኦሮሞ ህዝብ ኢትዮጵያን የመሰረተ ትልቅ ህዝብ ሰለሆነ የመገንጠል መንፈስ የለውም። የመገንጠልን ፕሮፓጋንዳ ማራመድ ደግሞ የሚጠቅመው ትግሬዎችን እንጂ ሌላውን ህብረተሰብ አይደለም። ኦሮሞ ለመገንጠልም ከፈለገ ጊዜ ሊፈጅ ይችላል እንጂ ምንም አይነት ኃይል አያቆመውም። ትግላችንም ከትግሬዎች ጋር ብቻ ሳይሆን ከምእራባውያን ጋርም ነው። ለዚህም ነው ወደ ነፈሰበት መንፈሱን በማቆም በአቋም፣ በእምነትንና በብልህነትን ታንፀን በትእግስት ትግሬዎችን ከትከሻችን ላይ አውርደን ለመጣል ኢትዮጵያዊ የሆን ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንታገል የምንለው። መቸም መጠኑ ይለያይ እንጅ በሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ ሆዳምና ባንዳ መኖሩንም አንርሳ ::
(ምንጭ፡ ኪያ ቲላ ፌስቡክ ገጽ)

ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት ጋየ ::

 


ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት ጋየ ::
ዩንቨርስቲው አግዶት የነበረውን welcome ceremony ትናንትና ጀምሮ ቢፈቀድም ፤ ትናንትን የትግርኛ ሙዚቃ well come ጋር በመጋበዙ አዳራሹ በጨኸት እየተናወጠ ተማሪዎች አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል። ይሔ ከሆነ ከ1 ቀን በኋላ በአሁኗ ሠአት የአዲስ ተማሪዎች ዶርም በእሳት እየጋየ ነው። እሳቱ በጣም ከባድ ነው። ከአሁኑ ጋር ይህ block ሲቃጠል 3 ኛው ነው።
ደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጊቢው በአጋዚ ተከቧል። አሁን ደግሞ ሌላ ጦር መሣሪያ የጫኑ መኪናዎች ወደ ጊቢው አየገቡ ነው። ምን እየሆነ እንደሆነ ለማየት እራሱ ከቤታችን መውጣት አልቻልንም። ተማሪዎች ከውስጥ ጩኸት አያሠሙ ነው። የእሳቱ ምክንያት አልታወቀም። እሳቱ የተነሳው  ማታ 3. 00 ነው።

Friday, November 4, 2016

የወያኔ የሹመት አጀንዳ = የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ = ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ አይንአውጣነት


የወያኔ የሹመት አጀንዳ = የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ = ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ አይንአውጣነት – ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለ ተጠያቂነት ሞራሉ የለውም። በኢትዮጵያ ስር የሰደደውና የተንሰራፋው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሙስና እና የመልካም አስተዳደር ችግር ሁሉ ያሳተፈ ስል ነቀል ለውጥ እስካልተደረገ ድረስ በዘራፊው ሕወሓት መራሽ አገዛዝ ይስተካከላል ማለት ዘበት ነው። ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ አይን አውጣነት ሽወዳ ይቁም ፤ የወያኔ ሹመት አጀንዳው ተከትሎ ሃይለኛ ወቀጣ እየተደረገ ነው። ወያኔን ለማያውቅሽ ታጠኙ በሏት። ሕዝባዊ ንቅናቄ የፖለቲካና ኢኮኖሚ በድርቅ እና በተለያዩ ጫናዎች አጣብቂኝ ውስጥ ከውስጥ እና ከውጪ ስትገባ ሕወሓት ሽወዳ ለማድረግ የምትጠቀምበት ዘዴ አንዱ ማኮላሻ አጀንዳዎችን በመፍጠር ከጀርባ ሴራዎች ላይ ማጠንጠን ነው። በሕወሓት ኣጨብጫቢዎችና በተቃዋሚው ጎራ ድጋፍና ትችትን ያስከተለው የሃይለማርያም የወጥ ቤት ካቢኔት የሕዝቦች ነጻነት ባልተረጋገጠበት ሃገር ምን አይነት ፌዝ ነው የተያዘው፧የሳምንቱ ምርጥ ቀልድ ነው የሆነብኝ።በሃገሪቱ ሁለት የሚታይና የማይታይ መንግስቶች ኣሉ የሚታየው በሃሰት ተተብትቦ ሲኖር የማይታየው ግን ይገላል ያስራል ያሳዳዳል፤
የወያኔ ባለስልጣናት ተሰብስበው ችግሩ እኛ ጋር ነው አሉ እየተባልን ያለነው ሽተታቸውን አመኑ ብለን ሆዳችንን ለማባባት ከሆነ ሞኛቸውን ይፈልጉ፥፥ካሁን ቀደም ከጠ/ሚ ተብዬ ቢሮ ጀምሮ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያቤቶች እና አካሎቻቸይ ያልተባል ያልተማል ያልተነገር ነገር የለም ያልተሰበሰበ ያልተገመገመ ያልተወሰነ ወዘተ የለም፥ሆኖም ነገሮች ሁሉ ማዘናጊያ ከጊዜ አጣብቂኝ ለመውጣት የሚጠቀሙባት ልማታዊ ሽወዳ ናት፥በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ ላይ የተሰማራው ወያኔ ጭፍሮቹን እያስጨበጨበ አዲስ የግፍ ስልት ለመቀየስ ብቅ ማለቱን ያመለክታል፥፥ላለፉት 25 አመታት የት ነበረኡ ? ይህ ሁሉ የወያኔ ባለስልጣን ዛሬ ስለ ሃላፊነት እና ተጠያቂነት የሚነግሩን?ሞራላቸውስ ? ለመሆኑ ብሄራቸውን እና አብሮ አደግነታቸውን መከታ በማድረግ በየመንግስት መስሪያ ቤቱ የተሰገሰጉት እነማን ናቸው? የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በየሃገሩ የሚገኙ ኤምባሲዎች በዋቢነት ማስቀመጥ ይቻላል::ይህ ተባለ ያ ተባል ብሎ ስለ ቆራጥነት ከማላዘን መጀመሪያ እርምጃው ከሕወሓት ተጀምሮ ተግባራዊ ስራዎች ሲተገበሩ ነው ቆራጥነት የሚባለው፥እውነት ከሆነ ላላዛኞቹ ብቻ፥፥
የወያኔ ባለስልጣናት በተለይ ሕወሓት በዘረፋ እና በብሄር ተኮር መጠቃቀም ግንባር ቀደም ባለኔትዎርክ ነው ቀሪ የወያኔ ድርጅቶችም በኔትወርክ ቢደራጁም ከሕወሓት እውቅና ውጪ አይንቀሳቀሱም የሁሉ እኩይ ተግባር መሪ ሕወሓት ነው!! ካሁን ቀደም በተለያየ ጊዜ የሙስና ኔትወርኮችን ለመበጣጠስ ተጠያቂነት እና ሃላፊነትን ለማስፈን የተደረገው ሙከራ በሌቦች ባለስልጣት ከሽፎ የመልካምነትን ጥያቄ ያነገቡ እስር ቤት ታጉረዋል :: ለዚህም ዋና ተጠቃሽ በሙስና እስር ቤት የሚገኘው መላኩ የሕወሓት ስውር እጆች አላሰራ አሉን ስላለ ብቻ ተይዞ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::አሁን ከመላኩ እና ከገብረዋህድ በላይ ሃገሪቷን ያራቆቱ ቡድኖች ጠፍተው ነው? ይህ ደግሞ በብሄር በመንደር በአብሮ አደግነት የተሳሰረው ኔትወርክ በከፍተኛ ባለስልጣት እጅ(በሕወሓቶች) እንደሆነ በገሃድ ያሳያል::
በኦሮሚያና በኣማራ ክልል የተደረጉ ግድያዎች መብትና ነጻነትን የጠየቁ ሕዝቦችን በጥይት መፍጀት ማሰር ማሳደድ ከኣገዛዙ ኣከፊ ተግባራቶች ግንባር ቀደም ናቸው። በሃገሪቱ ሁልት የሚታይና የማይታይ መንግስቶች ኣሉ የሚታየው በሃሰት ተተብትቦ ሲኖር የማይታየው ግን ይገላል ያስራል ያሳዳዳል!የሰው ልጆች ነጸነት ባልተረጋገጠበት ዜጎች በአሸባሪ ታርጋ እስር ቤት በሚገቡበት አገር እንዴት መልካም አስተዳደር ይረጋገጣል?መጀመሪያ ነጻነት!!! ከአጣብቂኝ ለመውጣት የተደረገ የልማታዊ ሽወዳ የፖለቲካ ስልት አንዲት ቅርንጫፍ ነው::ይህ ጉዳይ ቆራጥ እርምጃ ከተወሰደበት የሕወሓት እና ጭፍሮቹ ጉሮሮ መቁረጥ ስለሆነ መተግበር ያስቸግራል አሊያም ይህን ለመተግበር ከተቃዋሚዎች ጫን ያለ የትግል ስልት ይዞ መዝለቅን ይጠብቃል::ላለፉት 25 አመታት ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በዘረፋ እና በሃሰት ፕሮፓጋንዳ አገር እመራለሁ የሚል ቡድን በየትኛው ሞራሉ ሰላማዊ መንገድን በአንድ ጀንበር ይቀበላል::ከአጣብቂኝ ለመውጣት የሚደረግ ልማታዊ ሽወዳ ይቁም::ከጅምሩ ኋላፊነት የጎደለው አገዛዝ ስለተጠያቂነት ሞራሉ የለውም!!! 
Image may contain: one or more people

አዲሱ የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ነገሪ ሌንጮ አለኝ ያሉት የዶክትሬርት ዲግሪ የውሸት ዲግሪ መሆኑ ታውቋል።


አዲሱ የኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ነገሪ ሌንጮ ከህንድ አገር Andhra University አለኝ ያሉት የዶክትሬት ዲግሪ የውሸት ዲግሪ መሆኑ ታውቋል። እሳቸው በተመረቁበት አመት ብቻ 580 የውሸት ዲግሪዎችን በመሸጥ የዩንቨርሲቲው አስተዳዳሪዎችና ዲን በሙሉ በህንድ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ነበር።
http://www.thehindu.com/…/fake-degree-ce…/article4261482.ece ልጅ ግሩም
Yonas Tekelea's photo.

የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ታስረ


Image may contain: 1 person , people smiling , closeup
የኢትዮ-ምህዳር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ ታስረ
(ከ10 ቀናት በኋላ የፍርድ ውሳኔ ይሰጠዋል)
———–
የሳምንታዊው ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ፣ በጋዜጣው ላይ ግንቦት 2007 ዓ.ም ታትሞ በወጣውና በመንበረ ፓትሪያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም ላይ የገንዘብና የንብረት ሙስና መኖሩን የሚያጋልጥ ዜና መስራቱን ተከትሎ፣ የቀረበበትን ክስ ሲከታትል ቆይቶ ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 6ኛ ወንጀል ችሎት የጥፋተኘት ውሳኔ ተሰጥቶት ታስረ።
የጋዜጠኛውና የጋዜጣው ጠበቃ አቶ በሀይሉ ተስፋሁን እንደገለጹት፤ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ካደመጠ በኋላ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 613/3 መሰረት ከባድ የስም ማጥፋት በሚል ደንበኛቸው ጥፋተኛ መባሉን ተናግረዋል።
እንደጠበቃው ምላሽ ከሆነ፣ በወቅቱ ዜናውን የሰራው ሪፖርተር ከሰበካ ጉባዔው የውስጥ ምንጮች በመረጃ ተገቢውን መረጃ ከማጠናቀር ባሻገር፤ የዜና ዘገባውን ሚዛናዊ ለማድረግ ሪፖርተሩና ጋዜጠኛ ጌታቸው ጉዳዩ የሚመለከተውን ሃይማኖታዊ ተቋም ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም “ዜናውን እንዳታወጡት!” የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ነበር።
ክሱ ከተጀመረም በኋላ ክሱን በበቂ ሁኔታ መከላከላቸው የሚናገሩት ጠበቃ በሃይሉ፣ በዛሬው የፍርድ ቤት ወሎ የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ከተሰማ በኋላ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 06 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
ጋዜጠኛ ጌታቸውም ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ የታስረ ሲሆን ከነገ በኋላ ባሉ ቀናት ወደቂሊንጦ እስር ቤት ይዘዋወራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮ-ምህዳር በሀገራችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ትታተም የነበረች ጋዜጣ ስትሆን በተለያዩ ጊዜያት ህትመቷ እየተቋረጠ በዋና አዘጋጁ የግል ጥረት አሁንም ደረስ ዘወትር ቅዳሜ የምትነበብ ጋዜጣ ነች። ጋዜጠኛ ጌታቸውም በተለያዩ ጊዜያት እየተከሰሰና እየታሰረ አስቸጋሪውን የኢትዮጵያ የጋዜጠኘት ሙያ በመጋፈጥ ላይ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሙስና የዜና ዘገባ ቀርቦበት ኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣ ላይ ክስ አቅርቦ ነርበ። ጌታቸውም እንደዋና አዘጋጅነቱ ክስ ቀርቦበት ከባልደረቦቹ ጋር ሀዋሳ ፍርድ ቤት ሲመላለልሱ፤ እነሱ ተጭነውበት የነበረው ባጃጅ ተሽከርካሪ ሆነ ተብሎ ተገጭቶ የመገልበጥ አደጋ ገጠመው።
የጋዜጣው ከፍተኛ አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ኤፍሬም በየነም በአደጋው በደረሰበት ከባድ አደጋ ከወገቡ በታች ፓራላይዝድ ሆኖ ዛሬም ድረስ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ይገኛል።
ጋዜጠኛ ኤፍሬም በሀገርና ከሀገር ወጪ የህክምና እርዳታ ቢደረግትለም ከገጠመው ችግር ሊፈወስ አልቻለም። በወቅቱም ጋዜጠኛ ጌታቸው ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበት እንደነበረ አይዘነጋም።

ወያኔ የደረሰበትን የዋጋ ግሽበት ተከትሎ አንድ ዶላር ወደ ኣርባ ይጠጋጋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ኣይሏል።


Image may contain: one or more people
 – ወያኔ የደረሰበትን የዋጋ ግሽበት ተከትሎ አንድ ዶላር ወደ ኣርባ ይጠጋጋል የሚል ከፍተኛ ስጋት ኣይሏል። የሕዝብ ተቃውሞ የሕዝብ ኣስተዳደር ችግር እዳ እና የዋጋ ግሽበት/የገንዘብ ውድቀት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ንዶታል::ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች በሕዝባዊው ንቅናቄ ጫና ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው።
ሕዝባዊ ንቅናቄው በኢትዮጵያ ከተስፋፋ ጀምሮ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሳይሆን የተከሰተው የውጪ ምንዛሬ የለም። ባለፉት ስድስት ወራት የተገኙ የውጪ ምንዛሬዎች በባለስልጣናት ተዘርፈዋል ከውጪ ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ምንዛሬዎች ወደ ባለስልጣናት ኣካውንት ተዛውረው ሃገር ቤት ሳይገቡ በመንገድ ተጠልፈዋል። የሃገሪቱ ካዝና የውጪ ምንዛሬ ናፍቆታል። የዶላር ያለህ እያለ ነው።
የዶላር ምንዛሬ በሃምሳ ፐርሰንት ኣድጎ ወደ ኣርባ ብር መዳረሻ ይገባል የሚሉ የወያኔ ኣገዛዝ የኢኮኖሚ ኣማካሪዎች መላ መዘየድ ኣቅቷቸው ፈጠዋል። ወያኔ ከፍተኛ ኣጣብቂኝ ውስጥ ይገኛል።ኢንቨስተሮች ገንዘባቸውን ከሃገር ኣውጥተው ጨርሰዋል ብር በጃቸው ያለ ሰዎች ብሩን በዶላር ቀይረው ዞር ብለዋል። የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ሊቀበር ሰከንዶች በቀሩበት ሰዓት ላይ ወያኔ የሃሰት ፕሮፓጋንዳውን ቀጥሏል።
ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ሕዝብ በገዛ ኣገሩ ነጻነቱናን መብቱን ተገፎ የበይ ተመልካች መሆኑ ባለስልጣናት እና ዘርማንዘሮቻቸው በዘረፋ ላይ መሰማራታቸው እና ስርአቱ የሚከተለው የተጭበረበረ ፖለቲካ በሃሰት ፕሮፓጋንዳ መታጀቡ ነው::መፍትሄው ደሞ ስልጣን መልቀቅ ብቻ ነው::የወያኔ የፖለቲካና የኢኮኖሚ እንቅስቃሲዎች ተሽመድምዷል። ትግሉም ወሳኝ ምእራፍ ላይ መሆኑ ተረጋግጧል:: ወገን የሞተውን ወያኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የቀብር ስነ ስርአቱን የምንፈጽምበት ወቅት ላይ ነን ።ለስርኣቱ ቅርበት አላቸው ያሉ ምንጮች ወያኔ ወገቡ እንደተሰበረ እየተናገሩ ነው::ወያኔ ስልጣኑን ለህዝብ እንዲያስረክብ በተገኘው የትግል ስልት በመሳተፍ የዜግነት ድርሻችንን እነወጣ። #ምንሊክሳልሳዊ