Friday, November 4, 2016

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን እንዲያስፈቱ ተጠየቀ።


የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን እንዲያስፈቱ ተጠየቀ። Minilik Salsawi
የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይዘሮ ትሬዛ ሜይ በሕወሓት የማሰቃያ እስር ቤት በስቃይ ላይ የሚገኙትን ታጋይ ኣንዳርጋቸው ጽጌን ለጉዳዩ ኣትኩሮት ሰጥተው ጣልቃ በመግባት እንዲያስፈቱ ተጠየቀ። እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ቢሮ የታጋር ኣንዳርጋቸው ጉዳይ እንዳሳሰበው ከገለጸ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በታጋይ ኣንዳርጋቸው መፈታት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሯ ኣቤቱታውን እንዲያሰማ የታጋይ ኣንዲ ቤተሰቦቻቸው ጠይቀዋል። ዝርዝሩን ከዚህ ሊንክ ያንብቡት 

Thursday, November 3, 2016

ሼህ ኣላሙዲን ቢል ክሊንተን ወደ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ኣንድ ጉዞ ሁለት ሚልዮን ዶላር ይከፍላሉ።


 
 
ሼህ ኣላሙዲን ቢል ክሊንተን ወደ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ኣንድ ጉዞ ሁለት ሚልዮን ዶላር ይከፍላሉ። Minilik Salsawi
 
ሼህ ኣላሙዲን የቀድሞ የኣሜሪካ ፕሬዝዳንት ቢል ክሊንተን ወደ ኢትዮጵያ ለሚያደርጉት ኣንድ ጉዞ ሁለት ሚልዮን ዶላር ይከፍሏቸውል ተባለ። ዘገባውን ያወጣው ዊክሊክስ እንዳለው በክሊንተን ፋውንዴሽን የተገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሼህ ኣላሙዲ 6 ሚሊዮን ዶላር የከፈሉበት ቼክ መገኘቱ ኣጋልጧል። በኣጠቃላይ ከሃያ ሚሊዮን ብር በላይ ከፍለዋል ሲሉ መረጃዎቹ ዋቢ ተደርገዋል። ዝርዝሩን ከዚህ ያገኙታል።

ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካቢኔ ሹም ሽር ተቹ


ተቃዋሚዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን የካቢኔ ሹም ሽር ተቹ
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያደረጉትን የካቢኔ አባላት ሹም ሽርን ተችተዋል፡፡ መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ሲሉ አዲሱን የሚኒስትሮች ሹመት አልተቀበሉትም፡፡ ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች መለዋወጥ ለውጥ አያመጣም ብለዋል፡፡
በዛሬው የካቢኔ ሹም ሽር ከ30 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ውስጥ ዘጠኝ ሚኒስትሮች ባሉበት እንዲቀጥሉ ሲደረግ ሃያ አንዱ አዲስ ሚኒስትር አግኝተዋል፡፡ ከአዲሶቹ ተሿሚዎች ውስጥ አራቱ በባለፈው ካቢኔ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ሲመሩ የነበሩ እና ወደ አዲስ ቦታ የተዘዋወሩ ናቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ በሚኒስቴር ዴኤታነት ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም ሚኒስቴር የነበሩ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪነት ሲሰሩ የነበሩ አንድ ባለስልጣን ደግሞ ወደ ሚኒስትርነት ቦታ ተመልሰዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተሿሚዎቹን በምክር ቤት አቅርበው ከማጸደቃቸው በፊት እንደተናገሩት ለሹመት ዋና መመዘኛ ያደረጉት ውጤታማነት፣ ለህዝብ ቀልጣፋ አግልግሎት መስጠት መቻል እንደዚሁም ፖሊሲ እና ስትራቴጂ የማስፈጸም ብቃትን ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራረሮች ግን ሹመቱ መሰረታዊውን የኢትዮጵያን ችግር እና የወቅቱን የፖለቲካ ቀውስ አይፈታም ባይ ናቸው፡፡
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ህዝብ እየጠየቀ ያለው የፖሊሲ እና መሰረታዊ ለውጥ እንጂ የግለሰቦች ሹም ሽር አይደለም፡፡ ሊቀመንበሩ ሹም ሽሩን ገዢው ፓርቲ “ቀባብቶ በማለፍ” ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርገው ሲሉ ይተቹታል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ አዲስ ካቢኔ መስርቼያለሁ ባለ በአንድ ዓመት ውስጥ 21 ሚኒስትሮችን መለወጡ “መጀመሪያውኑ ችግር እንዳለበት ያመለክታል” ይላሉ፡፡
ዛሬ በድጋሚ በተዋቀረው ካቢኔ ውስጥ በተለያየ ዘርፍ የዶክተርነት ማዕረግ ያላቸው 14 ሚኒስትሮች እንደተካተቱ የተገለጸ ሲሆን ሁለት ፕሮፌሰሮችም ቦታ አግኝተዋል፡፡ ይህም ቢሆን የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ቀልብ አልገዛም፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩት ዶ/ር መረራ ግን የዶክተርነት ማዕረግ ያላቸው ተሿሚዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ገዢውን ፓርቲ ሲያገለግሉ የነበሩ እንደሆነ ይከራከራሉ፡፡ ሹመቱንም “ኋላ የነበሩትን ፊት ማምጣት” ሲሉ ይገልጹታል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲው አቶ ይልቃል የቀደመው ካቢኔ ሲጸድቅ “ማስተርስ ያላቸው እና የተማሩ” እየተባለ የትምህርት እና የትምህርት ልምዳቸው ሲነገር እንደነበር ያስታውሳሉ፡፡ የአሁን ሹመት “የተለየ ነገር የለውም” ባይ ናቸው፡፡ “የኢህአዴግ አብዮታዊ ዲሞክራሲ እና ጥፍንግ ያለ የማዕከላዊነት አመለካከት እስካልተለወጠ ድረስ የግለሰብ መቀየር ምንም ዓይነት ለውጥ አያመጣም” ይላሉ፡፡
ሁለቱም የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ኢትዮጵያ ያለችበት ወቅታዊ ችግር የሚፈታው በሚኒስትሮች መለዋወጥ ሳይሆን “ኢህአዴግ መሰረታዊ እና የፖሊሲ ለውጥ ሲያደርግ ነው” ይላሉ፡፡ ነጻ ምርጫ፣ ሁሉንም በእኩልነት የሚያስተናግድ ስርዓት እና እውነተኛ መድበለ ፓርቲ ስርዓት እንዲኖር ካልተፈቀደ እንደዚሁም እንደ ፍርድ ቤት እና መገናኛ ብዙሃን ያሉት ተቋማት ነጻ ሆነው እንዲንቀሳቀሱ እስካልተደረገ ድረስ ለውጥ አይመጣም ባይ ናቸው፡፡

የፖለቲካ ጥላቻ ለለውጥ በሚደረገው ሂደት ላይ ችግር ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው።


የፖለቲካ ጥላቻ ለለውጥ በሚደረገው ሂደት ላይ ችግር ስለሚፈጥር በጊዜ ሊታረም የሚገባው ጉዳይ ነው። ( ምንሊክ ሳልሳዊ )
የሕዝብ ማንዴት ያሌላቸው ፖለቲከኞች ራሳቸውን የሕዝብ ወኪል አሊያም በሕዝብ የተቀቡ አድርገው ሲያቀርቡም የፖለቲካ እብደቶች እየገነኑ ይመጣሉ::በሃገራችን ፖለቲካ ውስጥ የሚታዩ የፖለቲካ ጥላቻ ምቀኝነት ግለኝነት ቅናት የመሳሰሉት ለውጡ በእንብርክክ እያስኬዱ የሚገኙ ሲሆን ሂደቶን ሁሉ ባለህበት እርገጥ ሆነዋል:: እንደኔ እምነት ጥላቻ ምቀኝነት ቅናት ክፋት እና ግለኝነት የጎሳ እና ከፋፋይ ፖለቲካ የሚከተለ እንደ ሕወሓት ያሉ ድርጅቶች ያነገቡት አርማ ነው::መልካም እና ጽኑ ታጋዮች እንደተጠበቁ ሆነው በስለናል የትግል ልምድ አለን ከሚሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እዚህ ግቡ የማይባሉ ገደል ማሚቱዎች ድረስ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቦርቅቀው ለማተራመስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም::ከኛ በላይ ላሳር የሚሉ እንጭጭ ፖለቲከኛ ነን ባዮች ጥቂቶች ሰፊዉን ሜዳ በተግባር ኣልባ ፕሮፓጋንዳ ብቻ አጣበዉት ሌላው እጁን አጣጥፎ ሲያይ መመልከትም ግርምትን ይፈጥራል::የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰከረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ይህን ያህል ተተራምሷል ለማለት ግን አያስደፍርም::

የጣሊያን ፖሊስ ወደ ሃገር የሚገቡ ስደተኞችን በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በድብደባ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ ይፈጽምባቸዋል ሲል ኣምነስቲ ኣጋለጠ።


የጣሊያን ፖሊስ ወደ ሃገር የሚገቡ ስደተኞችን በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በድብደባ ከፍተኛ የሆነ ሰቆቃ ይፈጽምባቸዋል ሲል ኣምነስቲ ኣጋለጠ። (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ መሰረት የጣሊያ የፖሊስ ሃይሎች በሊቢያ በኩል በባህር ወደ ጣሊያን የሚገቡ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የማሰቃየት ተግባር ይፈጽማል ሲል ገልጿል። መግለጫው ከስደተኞችና ከጣሊያን ፖሊሶች ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ እንዳለው በድብደባ በኤሌክትሪክ ማሰቃያና በተለያዩ የቶርች ዘዴዎች ከፍተኛ ስቃይ በስደተኞቹ ላይ ይፈጸማሉ ሲል ኣጠንክሮ የፖሊሶቹን እኩይ ተግባር ኣውግዟል።
ይህ ከፍተኘ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊከሰት የቻለው የኣውሮፓ ሕብረት ስደተኞቹ እንዳይገቡ በጣሊያን ላይ በሚያደርገው ጫና ሲሆን እጅግ ኣደገኛ የሆኑ ቶርቾች በሰው ላይ ይፈጸማሉ ሲሉ ሪፖርቱ ያስረዳል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ዝርዝር ዘገባው ከዚህ ያገኙታል፤ 
Minilik Salsawi in Rome Italy

Wednesday, November 2, 2016

የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል።


 የወያኔ ሚኒስትሮች ምክር ቤቱ ኣሻንጉሊት ሲሆን ወሳኙ ኣካል ሕወሓት/ወያኔ እንደሆነ ይቀጥላል። የዶክተሮች ጋጋታ ከዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ጋር ፉክክር ኣድርጎታል። 
Image may contain: one or more people and text
 በኢሕአዲግ ኣገዛዝ የሕወሓት የበላይነት የሚቆመው ሕወሓት ስልጣኑን ለሕዝብ ሲያስረክብ ብቻ ብቻ ነው፤ ኣሻንጉሊቶች መሰብሰብ የለመደው ሕወሓት የፓርቲና የመንግስት ስራ ቀላቅሎ ሕዝብን ሰላምና ፍትህን ኣሳጥቶ በመግደል በማሰር ላይ ይገኛል። ሃገራችን በወታደራዊ ኣገዛዝ በኣስቸኳይ ጊዜ ኣዋጅ ስር ባለችበት በዚህ ወቅት ላይ ሲቪል ሚኒስትሮችን ያዉም ታማኝ ባሪያዎችን መሾም ማጭበርበር ነው።። በፖለቲካ ማጭበርበር ደሞ ወያኔ የተካነበት ስራው ነው። ሃሰትን ማራባት ኣራብቶ ማሰራጨት የወያኔ ስራው ነው።
ወያኔ የምሁራን ስብስብ እንዲባል ዶክተር ፕሮፌሰር እያለ ሚኒስቴር መሾሙ ሳቅ ለመፍጠር ካልሆነ በስተቀር ለሕዝብ የሚፈይደው ኣንድም ነገር የለም። ዲያሶፖራ ካሉ ተቃዋሚዎች ጋር ዶክተር ፕሮፌሰር እያሉ ከመሾም ይልቅ ለሕዝብ ጥያቄ መመለስ በጣም ቀላል ነው። ይህ ግን ወያኔ ለማድረግ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ሕዝብን በማታለል መቀጠሉን ለማሳየት ታዛዥ የሆኑ ከብቶች በሚኒስትርነት ሾሟል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ያውም ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ። የሚኒስትሮን መለዋወጥ ከጉልቻ መለዋወጥ ኣይለይም ኣንዳጁ ኣካል ስልጣል ሲለቅ ነው የሚነደው ኣካል እፎይ የሚለው እሳቱ ስልጣን ሲለው የኣምባገነኖች ነበልባል ስልጣን ሲለቅ በእሳት የሚለበለበው ሕዝብ ሰላም ያገኛል። ተሿሚ ሚኒስትሮች ራሳቸውን በምቾት በማኖር ለሆዳቸው ከማደር ውጪ በሃገር የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ምን ኣይነት ለውጥ ኣያመጡም።ይህ ለይስሙላ የሚደረግ ተግባር የሕዝብን ትግል ኣያቆምም። ትግሉ ይቀጥላል።

የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ:: የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል።


የአማራ ወጣቶች በባሕር ዳር እርምጃ ወሰዱ፤  

ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት ( ከተማ አተዳደር) በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል።
የህዝብን ጥያቄ ወደ ጎን በማሸሽ መልስ የማይሰጠው ወያኔና ብአዴን ትምህርት የሚወስዱበት እርምጃ በባህር ዳር ወጣቶች ተወሰደባቸው። ከቀናቶች በፊት የተለያዩ የማህበር ክፍሎችና ነጋዴዎች ከእስር እንዲለቀቁ የጠየቁት ወጣቶች ለ5 ቀን የሰጡት ማስጠንቀቂያ ምላሽ ባለማግኘቱ እርምጃ መወሰዳቸውን አስታወቁ።
እርምጃውም ቀበሌ 03 በሚገኘው የባለስልጣኖች መኖሪያ ኪቢአድ ግቢ እና የባህር ዳር መዘጋጃ ቤት( ከተማ አተዳደር) በተመሳሳይ ሰአት ከምሽቱ 2 ሰዓት የቦንብ ፍንዳታ ተፈጽሟል። ይሄንን ተከትሎ አካባቢው ላይ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት ከመንገሱም በላይ አምቡላንሶች ሲሯሯጡ ይታያል።
አሁንም ወጣቶቹ ይናገራሉ የታሰሩ ወንድሞቻችንና ነጋዴዎች እስካልተፈቱ ድረስ ይሄ ጥቃት በሰፊው እና በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚካሄድ አስጠንቅቀዋል። ከዚህ በዃላ ሊደረግ የሚገባውን እርምጃና ማስጠንቀቂያ ከቀናቶች በዃላ ያስታውቃሉ።