Monday, October 31, 2016

ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ


የተበታተነውን ትግል ለማሰባሰብ የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ \አህመን\ የሚባል ደርጅት አገር ቤት ተቋቋመ::የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)የጎበዝ አለቆች ያሉበት፣ የተለያዩ በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱት ለማሰባሰብ ፣ የአማራ ተጋድሎን በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ የተቋቋመ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ላይ የማይደራደር ደርጅት እንደሆነ ነው መግለጫው የሚጠቁመው።
ወያኔን ለማስወገድ፡ አማራን ማደራጀት – የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን) መግለጫ
ባለፉት ሥርዓቶች እንደብቸኛ ተጠቃሚ እየተደረገ የፈጠራና የውንጀላ ታሪክ ተሰጥቶን በጭቆና ስር የሚማቅቀው ወግናችን የአማራ ህዝብ መደራጀት የግድ የሆነበት ደረጃ ላይ የተደረሰው በአማራ ልሂቃን ጉትጎታ ሳይሆን ህዝቡ በራሱ ከግፉ መብዛት፡ ከጭቆናው አሰቃቂነት የተነሣ በራሱ በአማራ ህዝብ የተፈጠረ ነው።
አብዛኞቹ የአማራ ልሂቃን ዛሬም ድረስ ወገናቸው “በመደራጀት ለራሴ ቀድሜ በመቆም ነው፡ ለኢትዮጵያ ልበጅ የምችል” ቢላቸውም ቅሉ አሁንም በአንድነት ስር ካሉ ሃይሎች ጋር በመሆን ዛው የህልም ሩጫ ውስጥ መዳከር ላይ ናቸው። ያውም ምንም አይነት የወሳኝነት ሚና በሌላቸው ድርጅቶች ውስጥ በመታቀፍ ጊዜያቸውንና ሃብታቸውን ይሰዋሉ።
ይህ አካሄድ የአማራን ህዝብ ሊጠቅም አይደለም፡ እንደውም ለጥቃት ያጋለጠ ከመሆኑ በላይ እነዚህ ሃይሎች የአማራን ህዝብ ትግልና ተጋድሎ በስሙ መጥራት፡ የሚደርስበትን በደል በይፋ መናገር ሁሉ የሚያሳፍራቸው መሆናቸው ደግሞ ጉዳዮ የበለጠ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።
በርካታ ወጣት የአዲሱ ትውልድ ልሂቃን ግን በሀቀኛ መረጃዎች የተደገፉ ጥፋቶችን በማሳየት ይህንን የአማራን የተጋድሎ ንቅናቄ ፈር ለማስያዝና ወደላቀ ድል ለማድረስ በየአቅጣጫው በመደራጀትና በማንቃት ላይ ናቸው። ከዚህ ደረጃ ትግሉን ያደረሰው ህዝባዊ ንቅናቄው እንጂ የቱም ድርጅት አለመሆኑን ሁላችንም የምናውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ነገር ግን አንዳንድ የስም አንድነት ድርጅቶች የአማራን ተጋድሎ በስሙ ለመጥራት የሚያፍሩ ሆነው፡ በተጨማሪም በተረት ዓለም እንደሚኖር ምንዱብ ትግሉንና ድሉን በመድረኮቻቸው ሁሉ የራሳቸው በማድረግ ገቢ ማግኛ አድርገውታል፡ ይህም ድርብ ግፍ ነው። የሚደርስበትን ሰቆቃ በፀጥታ ከማለፍ ባሻገር የሚያደርገውን ተጋድሎ ባልዋሉበት ውለው መንጠቅ፡ ድርብ ግፍ ነው።
አሁን የሌሎችን በኛ የሚደረግ በደል የምናወራበትና የምናለቃቅስበት ጊዜ አይደለም። ዛሬ አማራ በጓዳው ያስለቅሱት የነበሩትን ሰቆቃዎች ሁሉ ባደባባይ ለመጋፈጥ ቆርጦና ጨክኖ የወጣበት ሰዓት ላይ ነን። የኛ ድርሻ መሰባሰብ፡ ዘመናዊ ስልትና ዕጣ ፈንታን መቀየስ፡ እንደአንድ ቤተሰብ መምከርና አንድ ልብ፡ አንድ ሃሳብ መሆን፡ ድሉን ከወንድምልቻችንና እህቶቻችን እኩል ለማጣጣም እንድንበቃ መቀናጀት፡ መደራጀት፡ በንድነት ትልቅና ማንም የማይቋቋመው ህጋዊ የአማራው ተወካይ ሆነን መገኘት ነው።
አማራ የሌለበት ትግል ሁሉ ፍሬ ክርስኪ መሆኑን ሌሎች ከኛ በላይ ይረዱታልና፡ የኛ መደራጀት የኢትዮጵያ ወሳኝ ዕጣ መሆኑን ተገንዝበን እስከጀነርነው ድረስ በጽናትና በሆደ ሰፊነት፡ በአማራ ባህል በሽምግልናና ዕርቅ ዳኝነት እየተስማማን፡ በጎበዝ አለቆች የሚመራውን በጠንካራ ባህላችን የተፈጠረውን ትግል፡ በዘመናዊ የፖለቲካ የትግል ስልት ደግፈን ፈጣን ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማግኘት ና ጠላቶቻችን የሚያዋርድ አንድነትና አደረጃጀት ለመፍጠር እንነሳ።
የአማራ ህዝብ መድህን ንቅናቄ (አህመን)

የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ


የወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የእሳት ቃጠሎን አጣርቻለሁ አለ  በመጪው ሳምንት ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀርባል
ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ የ22 ታራሚዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ሲሆንየወያኔ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ቃጠሎውን በተመለከተ ያደረገውን የምርመራ ሪፖርት በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያቀርባል ተብሏል፡፡
አደጋው የደረሰ ሰሞን በስፍራው ተገኝተው ሁኔታውን የተመለከቱት የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች፤ የእሳቱን መንስኤና የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ አጣርቶ የምርመራ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡  የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አባዲ፤ ምርመራውና ማጣራቱ ተጠናቆ ሪፖርቱ መዘጋጀቱን ጠቁመው፤ በመጪው ሳምንት ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንደሚቀርብ ገልፀዋል፡፡
በማረሚያ ቤቱ ላይ የደረሰውን የእሳት አደጋ ተከትሎ በወቅቱ 2 ታራሚዎች በጥይት፣ ቀሪዎቹ በቃጠሎው ህይወታቸው ማለፉ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡ ባለፈው ዓመት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሌላ በጎንደርና ደብረ ታቦር ወህኒ ቤቶችም በደረሰው የቃጠሎ አደጋ የታራሚዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም፡፡

በቀይ ሽብር ዘመን የኢሕአፓ የመረጃ ሰው ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ኣረፉ።


በቀይ ሽብር ዘመን የኢሕአፓ የመረጃ ሰው ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ  ኣረፉ። የወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ኣጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሞንጉስ ከ አባታቸው ከኣቶ ስዩም ሰሙንጉስ ተጫኔ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ኣቦነሽ በቀለ በኣዲስ ኣበባ ተረት ሰፈር በሃምሌ 23 ቀን 1949 ኣመተ ምህረት ተወለዱ፤ ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሲቢስቴ ነጋሲ ትምህርት ቤት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሽመልስ ሃብቴ ትምህርት ቤት ኣጠናቀዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ፒያሳ ከሚገኘው የኣተሻገመ የጽሕፈት ስራ ትምህርት ቤት የጽሕፈት ስራዎች ስልጠና በመውሰድ በሰርተፍኬት የተመረቁ ሲሆን እንዲሁም በኣዲስ ኣበባ የንግድ ስራ ኮሌጅ በጸሃፊነት ሙያ የሚሰጠውን ትምህርት በመከታተር በዲፕሎማ ተመርቀዋል በተጨማሪም በፍት ህ ሚኒስቴር ስር የተለያዩ የሕግ ትምህርቶችን በመከታተል እስከለተ ሞታቸው ድረስ በሕግ የማማከር እና በሕግ ኣገልግሎት ስራ ላይ ተሰማርተው ከ30 ኣመት በላይ ቆይተዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ በትግል ስማቸው በለጥሻቸው አምሐ በቀይ ሽብር ዘመን በተንቀሳቀሱበት ሁሉ የደርግ ገዳዮችን ኮቴ በመከተል ለኢሕኣፓ የመረጃ ስራ ሲሰሩ እንደነበር እና የበርካታ የሕዋስ ኣባላትን ሕይወት እንዳተረፉ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል ። ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ለተቸገሩ የነጻ የሕግ ኣገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በማህበራዊ መስክ ሕዝብን በነጻ በማገልገል ኖረዋል።
ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሞንጉስ በደረሰባቸው ድንገተኛ ሕመም ያረፉ ሲሆን የቀብር ስነስርዓታቸው ቦሌ ሩዋንዳ በሚገኘው የቅዱስ ሚካዔል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። ወይዘሮ መታሰቢያ ስዩም ሰሙንጉስ ባለትዳርና የኣምስት ልጆች እናት ነበሩ። ፈጣሪ ነብሳቸውን በገነት ያኑርልን።

ወያኔ\ኢሕአዴግ ዛሬም ይቀልዳል። የኢሕአዴግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም የኢሕአዴግ መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡


ወያኔ ዛሬም ይቀልዳል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡
Reporter : የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማስፈጸም ሒደት በኮማንድ ፖስቱና በሌሎች የሕግ አስፈጻሚ አካላት ሊከሰት የሚችል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን ለመከታተልና ዕርምጃ ለማስወሰድ የተቋቋመው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ፣ ሥራውን በይፋ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ከአስፈጻሚው አካል የሚሞከር ተፅዕኖም አያሠጋኝም አለ፡፡
በማጣራት ሥራ ወቅት በኮማንድ ፖስት አማካይነት የማስፈጸም ሥራውን ከሚያከናውነው የመንግሥት አካል፣ መርማሪ ቦርዱ ነፃነትና ገለልተኝነት ላይ ተፅዕኖ  ሊያሳድር የሚችል ሥጋት ሊኖር አይችልም በማለት የቦርዱ አባላት ገልጸዋል፡፡
ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2009 ዓ.ም. የቦርዱን በይፋ ሥራ መጀመር ለማብሰር የቦርዱ ዋና ሰብሳቢና አባላት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያ አዳራሽ  የመጀመሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በዕለቱም የቦርዱ አባላት በሕገ መንግሥቱ የተጠቀሱ ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነቶችን ዋቢ በማድረግ፣ ቦርዱ ሊተገብራቸው የተዘጋጀበትን የትግበራ ዕቅድ በመዘርዘርም አስረድተዋል፡፡
በዕቅድ ትግበራው ወቅት በክትትልና በቁጥጥር ሥራዎች ከሰብዓዊ መብት አያያዝና ከመብት ጥሰቶች ጋር ሊኖሩ የሚችሉ ክስተቶችን በግልጽ ለይቶ በማውጣት፣ ተጠሪ ለሆኑለት ምክር ቤት እንደሚያቀርቡ የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋ ገልጸዋል፡፡ ከምክር ቤቱ በተጨማሪ መርማሪ ቦርዱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠሪ መሆኑን ያስረዱት ሰብሳቢው፣ በኮማንድ ፖስቱ በኩል ሊከሰት የሚችል ኢሰብአዊ አያያዝን አጋልጦ የእርምት ዕርምጃ ማስወሰድ በሕገ መንግሥቱ ለቦርዱ የተሰጠው ሥልጣንና ኃላፊነት መሆኑንም አስታውሰዋል፡፡
ከቦርዱ ዋና ዋና ተግባራት ውስጥ ከአዋጁ ድንጋጌዎች መተላለፍ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦችን ዝርዝር፣ ማንነትና የታሰሩባቸውን ሥፍራዎች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ የሚለው ይገኝበታል፡፡
ሙሉ በሙሉ በኢሕአዴግና በአጋር ፓርቲዎች ከተወከለው ምክር ቤትም ሆነ ከፍትሕ ተቋማት የተሾሙ አባላት የተዋቀረው መርማሪ ቦርድ፣ በሥራ አስፈጻሚው በኩል ሊታይ የሚችል የሰብዓዊ መብት ጥሰትን መርምሮ ለማጋለጥ ምን ያህል ገለልተኛና ተዓማኒነት ሊኖረው እንደሚችል፣ ነፃና ግልጽ የሆነ ሪፖርት ለማቅረብም ከአስፈጻሚው አካል ተፅዕኖ ሊያጋጥመው ይችል እንደሆነ ጥያቄ ተነስቶ ነበር፡፡
ለጥያቄው ምላሽ ለመስጠት ቅድሚያውን የወሰዱት የቦርዱ ሰብሳቢ፣ ‹‹ቦርዱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አባላቱም ከምክር ቤቱ የተውጣጡ ናቸው፡፡ እነዚህ አባላት ቀድሞውንም የምክር ቤት አባል ያደረጋቸው የፓርቲው አባላትነታቸው መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ለፓርቲያቸው ፖሊሲና ስትራቴጂ ተገዥ ቢሆኑም፣ በአፈጻጸም ላይ በሚታዩ ችግሮች ልዩነት ለማሳየት አይከለክላቸውም፤›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡
‹‹በአፈጻጸም በምናደርገው እንቅስቃሴ ተፅዕኖ ሊመጣ አይቻልም፡፡ ሥራችንን በነፃነት እንደምንሠራ ሊታወቅ ይገባል፤›› ሲሉም አቶ ታደሰ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የምክር ቤት ወኪል በመሆን የተሾሙት ወ/ሮ ገነት ታደሰ በበኩላቸው፣ ‹‹የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ የቦርዱ አባላት የኢሕአዴግ አባል ስለሆንን ብቻ ለመንግሥት ጥብቅና አንቆምም፤›› በማለት ቦርዱ ሕገ መንግሥቱን መሠረት አድርጎ የሚንቀሳቀስ ስለሆነ የገለልተኝነት ጥያቄ ሊነሳ እንደማይችል ጠቁመዋል፡፡
ከፍትሕ ዘርፍ ተወክለው የተሾሙት የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛው አቶ ክፍለጽዮን ማሞ በበኩላቸው፣ ‹‹ሥራችንን የምናከናውነው ኢሕአዴግን እያሰብን ሳይሆን ሕገ መንግሥቱን እያሰብን ነው፤›› በማለት በቦርዱ ላይ የገለልተኝነት ጥያቄ እንደማያስነሳና በተፅዕኖ ሥር ሊወድቅ እንደማይችልም ገልጸዋል፡፡
ዋና መሥሪያ ቤቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ከፍቶ ሥራ መጀመሩን ይፋ ያደረገው መርማሪ ቦርዱ፣ በቅርቡም ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በተለያዩ የክልል ከተሞች እንደሚከፍት አስታውቋል፡፡
ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ከኮማንድ ፖስቱ አፈጻጸም እንቅስቃሴ ጋር ተያይዘው እንደሚከፈቱ ያስታወቁት የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ፣ በሁሉም ሥፍራዎች የኮሚቴ አባላቱን በማሰማራት ቦርዱ የክትትልና የቁጥጥር ተግባር እንደሚያከናውን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በተለይ ከሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያያዘ የሚገኙ ሪፖርቶችን ለምክር ቤቱ በማቅረብ፣ ዕርምት ያስፈልጋቸዋል ባላቸው ጉዳዮች ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት በማቅረብ ዕርምጃ የማስወሰድ ሥራ እንደሚኖርም ገልጸዋል፡፡
ኅብረተሰቡም ከመብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ጥቆማ ካለው ቦርዱ በሩ ክፍት መሆኑንም አሳውቋል፡፡ ለማንኛውም የጥቆማ አገልግሎት ኅብረተሰቡ በስልክ ቁጥር 0111-544641 እና በፋክስ ቁጥር 0111-545926 መጠቀም እንደሚችልም ገልጿል፡፡

Sunday, October 30, 2016

የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …


የማለዳ ወግ … በኢትዮጵያ “አትፈርስም ፣ ትፈርሳለች ” መካከል …
=========================================
* ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ ያማል 🙁
* መብት አስከባሪ ጠባቂ አልባ ዜጎች …
* ለስብዕና ቀናኢ እንሁን
ከቀናት በፊት እዚህ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ የደረሰኝ መረጃ ምክንያት ሆኖ ውስጤን አሞኝ ሰንብቷል ። የሀገሬ ሰው ከለንደን የተሰማውን የኦነግ ቀባጣሪ ” ኢትዮጵያ ትፈራርስ ” ቱማታ ተከትሎ ሀገር ወዳዱ ወገን ከአድማስ አድማስ ታውኮ ከርሟል ። እኔም እንደቀረው ወገን በሆነው አዝኘ ” የኢትዮጵያ አትፈርስም ትፈርሳለች ” መረጃ ስመለከትና ስታዘብ ሰንብቻለሁ ። በኢትዮጵያ “አትፈርስም ትፈርሳለች ” መካከል መካከል ከንጉስ ፉአድ ሆስፒታል ኃላፊዎች በኩል በአን ሀገር ወደድ ጥቆማ መሰረት ተጠርቸ ያየሁ፣ የሰማሁትና የተሰጠኝ መረጃ ሰቅጣጭ ነበር ።
በመንግስት እውቅና የኮንትራት ስራ ተብለው ከመጡት መካከል ያልታደሉት በውስጥ ደዌና በአዕምሮ ሁከት ተለክፈው ሲንገላቱ ህክምና በሚያገኙበት የህክምና ማዕከል ከ10 ያላነሱ በጠና ታመው ተኝተዋል ። ሶስት ያህሉ አስሰሚም አያዩም ፣ የቀሩት ከአልጋቸው መንቀሳቀስ አይችሉም ። የሀኪም ቤቱ ኃላፊዎች የመንግስታችሁ ተወካዮች ለህክምና የመጡ ዜጎቻቸውን ጉዳይ አይከታሉም የሚለውን ስሞታ በመረጃ ማስረጃ አቀረቡልኝ ። የተወሰኑትን በየአልጋቸው ሄጅ ስለመለከታቸው የተሰማኝን ሃዘን ብቻ ሳይሆን ባዶነት ነበር …ከቀናት በፊት በጠና ታሞ የጠየቅኩት ወንድም አልጋ በሌላ በሽተኛ ተይዟል ። ይህ ወንድም የት እንደሄደ ጠየቅኩ ፣ አሳዛኙ መርዶ ተነገረኝ 🙁 ወደ ማይቀረው አለም ማሸለቡን መረጃውን ከሚያቀብሉኝ አንዱ ሳውዲ ሀኪም ” እኒህ የምታያቸው እህቶች ዜጎቻችሁ ናቸው ፣ ከምንም በላይ ሰዎች ናቸው ፣ ቤተሰብ አላቸው ፣ ቤተሰቦቻቸው ይፈልጓቸዋልና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ የመንግስታችሁ ተወካዮች ለምን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲገናኙ እንዲንቀሳቀሱ አታደርጉም ? ” ብለው አፋጠጡኝ ። መልስ የለኝም 🙁
ጉብኝቴን ሳልከውን ሌላ መረጃ መዥረጥ አድርገው አወጡ ፣ በተለያየ ምክንያት ህይዎታቸው አልፎ በሬሳ ማስቀመጫ ለረዥም ጊዜ የተመጡ የዜጎቻችን ስም አጋሩኝ ። ውስጤ ታመመ 🙁 የማደርገው ባጣ ፣ ለመፍትሔው እጄ አጭር በመሆኑ አዝኘና አፍሬ ለመረጃው አመስግኘ የምችለውን እንደማደርግ ቃል ገብቸ ተለያየን!
በቀጥታ ያመራሁት ወደ ጅዳ ቆንስል መ/ቤት ነው ። የቆንስሉ ግቢ እንደቀድሞው በባለጉዳዮች አልተሞላም ። ቀዝቃዛ እንቅስቃሴውን እያስተዋልኩ ወደ ዲፕሎማቱ ቢሮ አመራሁ ። በቢሮው ኮሪደሮች አንዳንድ ባለ ባለጉዳዮች ፣ የቆንስሉ ቤተኞችና ሰራተኞች ይተላለፋሉ ። ከቤተኞች መካከል በቅርቡ አዲስ ቢሮ የተሰጣቸው የሴቶችን ሊቀ መንበር ተመለከትኳቸው ። ጉዳዬ በአልጋ ላይና በሬሳ ክፍል ውስጥ ስላሉት አብዛኛው እህቶች ጉዳይ ክትትል ማጣራት ቢሆንም በቀደመው የሻከረ ግንኙነት ባላንጣ ስላደረጉኝ እርሳቸውን መጠየቅ ከአንባጓሮ ባለፈ ፋይዳ እንደሌለው ስለተረዳሁ ልጠይቃቸው አልፈቅድኩም። እናም ወደ ሚመለከታቸው ዲፕሎማት ቢሮ አቀናሁ …
ዲፕሎማቱን እና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወንድም አገኘኋቸው ፣ ከሰላምታ በኋላ ውይይታችን ጀምርን ። በመጀመሪያ የጠየቅኳቸው በአሁኑ ሰአት በመጠለያው ከርማ ከወር በፊት ወደ ሀኪም ቤት እንድትገባ ስለተደረገው እህትና አሁን ያለችበትን ሁኔታ ማወቅ ስላለማወቃቸው ነበር ። ባለስልጣኑም ሆኑ ረዳታቸው በሆስፒታሉ ዘጠኝ ያህል ታማሚዎች በሆስፒታሉ ስለመኖራቸው መረጃ እንዳላቸው እምጅ የጠቀስኳት እህት ስለመኖሯ መረጃ የላቸውም ። ቀጥዬ ከሆስፒታሉ የተሰጠኝን መረጃ በተለይም ፖስፖርት ኮፒዋንና በቆንስሉ ለአሰሪዋ የተጻፈውን ደብዳቤ አሳየኋቸው ። መረጃው ትክክል መሆኑን ቢያረጋግጡኝም ዜጋዋ በሆስፒታሉ ስለመኖሯ በመዝገናቸው አለመስፈሩን አረጋገጥኩ ። ንዴቴ በፊቴ እየተነበበ ፣ ዝም አልኩ….
ከዚያ አከታትየ የጠየቅኳቸው ሞተው የቤተሰብ አድራሻና ማንነታቸው ባለመታወቁ አፈር መቅመስ ያልቻሉትዜጎች ጉዳይ ነበር ። ለዚህም ሲመልሱ ቤተሰብን ለማፈላለግ ማስታወቂያ እናወጣለን ቤተሰቦችን ማግኘት ከባድ ነው የሚል ምላሽ ሰጡኝ … ባለስልጣኑ ታመው የሚገቡትም ፣ የሚሞቱትም ሳውዲ ቤተሰብ አላቸው ብለው ያምናሉ ። እኔ ግን በዚህ አልስማማም ፣ ታመው ሲጨንቃቸው አምጥተው የጣሉ ሁሉ ቤተሰብ ላይሆኑ ስለሚችሉ ቢያንስ መርዶን ለቤተሰብ ለማርዳትና አፈር እንዲቀምሱ ለማድረግ አድራሻቸው ሀገር ቤት መፈለግ አለበት ባይ ነኝ ፣ ይህ ካልሆነ የፖስፖርት መምጣትን ከማየት ባለፈ ነዋሪው በማይጎበኘው በቆንስሉ ፊስ ቡክ ማስያወቂያ ለጥፎ ቤተሰብ ካላችሁ ሪፖርት አድርጉ ብሎ መናኛ ማስታወቂያ ማፈላለጉ ጠቀሜታው ብዙም እንደማይታየኝ አሳወቅኳቸው ። ደስተኛ አልሆኑም ፣ እኔ ግን ሀሳባቸው አልገባኝም !
በጫወታችን መካከል በጠና ታመው ካንቀላፉት መካከል ልክ የዛሬ ሁለት ሳምንት በአንበቱ ሀገር ቤት ስላሉ ቤተሰቦቹ ፣ ስለ ደጋፊ አልባ ልጆቹና ባለቤቱ አጫውቶኝ የነበረው ወጣት እስከ ወዲያኛው ማሸለቡን ስለተረዳሁት ወንድም መረጃ ጠየቅኩ ። ስለ ወጣቱ አትራፊ አጉዳይ ወጣት አባወራ መረጃው ያላቸው የጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች የዚህን ወንድም መርዶ ለቤተሰቦቹ አሳውቀው አፈር እንዲቀምስ የማድረጉን ሂደት አለመጀመራቸውን ግን ተረዳሁ 🙁
እኔ ሞቅ ባለ የያገባኛል ስሜት ፣ ባከስልጣኑ ” ለመፍትሔው ሁሉም ዜጋ መረባረብ አለበት ፣ መንግስት በጀት የለውም! ” በሚል ድፍን ምክንያት ውይይታችን ቀጠለ … እኛ እንደ ዜጋ መረጃ እናቀብላለን የሚቻለውን እናደርጋለን ፣ እናንተ ደግሞ አንድም እንደ ዜጋ ፣ ከፍ ሲል እንደ ከባድ የሀገር ኃላፊነት ፣ ከዚያም ወረድ ሲል ስለምትለፈሉበት ደመወዝ ስትሉ በማስተባበርና ለዜጎች መብት ልትቆሙ ይገባል ፣ ስል የሰጠኋቸው አስተያየት ዲፕሎማቱን ቱግ አደረጋቸው ! በውይይታን ብዙም አልቀጠለም ፣ ጥያቄ ለመጠየቅ ሳኮበኩም ያለወትሯቸው ያልተመቸኋቸው ዲፕሎማት ቆጣ ብለው ” አቶ ነቢዩ ጨረስን ይመስለኛል? ” አሉኝ … ጥቁት አተኩሬ አየኋቸውና መጨረሴን ገልጨላቸው እንደ ታመምኩ ቆዝሜ ከዚያ የሹሞች ቢሮ ወጣሁ … !
በሴቶች ስም ተመስርቶ ፖለቲካ የሚቆመርበትን የሴቶች ማህበር ሊቀ መንበር ቢሮ በአሻጋሪ ፣ ሊቀ መንበሯን በኮሪደሪ ሲውረገረጉ አየኋቸውና ሀዘኔ ተጨማምሮ ከራሴ ጋር እያወጋሁ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ 🙁
በበሽታ ተቀስፈው ፣ ተስፋ ቆርጠው ጨንቆ ጨልሞባቸው አልጋ ላይ ተጋድመው ያየኋቸው ዜጎች ባይኔ ውልብ አሉ ፣ ሰው ከሞት ባናመልጥም ፣ ከሞቱ አሟሟቱ እንዲሉ ማንነታቸው ሳይታወቅ ፣ ቤተሰብ መርዶ ሳይሰማ ወደ መቃብር ሊሸኙ የሚችሉትን ግፉአን እያሰብኩ በእኒህ የሆነው በእራሴ ቤተሰብ ቢሆንስ ? ብሎ የሚያስብ ጠፍቷል 🙁 ይህን ካየሁ ቀን ጀምሮ ለማትፈርሰው ኢትዮጵያ ትፈርሳለች አልፈርስም ብሎ መጦመር ለእኔ የፊዝ ነበር !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 19 ቀን 2009 ዓም
Nebiyu Sirak's photo.
Nebiyu Sirak's photo.

በአማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ወያኔ መርዛም ፕሮፓጋንዳውን እየረጨ ነው።


በአማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ወያኔ መርዛም ፕሮፓጋንዳውን እየረጨ ነው።
ምንሊክ ሳልሳዊ :- በኣማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ኣጣብቂኝ ውስጥ የገባው የሕወሓት ኣገዛዝ በውማራና በቅማንት ሕዝቦች መካከል ግጭት በመፍጠር በመሃል ሰርጎ ገብቶ ኣማራውን ለመፍጀት የሚያስችለውን እቅድ ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት ያዩ የኣይን እማኞች ገልጸዋል።
የሕወሓት ካድሬዎች ኮሌኔል ደመቀ የአማራን ጦር እየመራ የቅማንትን ህዝብ ሊያስጨፈጭፍ የነበረ ጠላት እንደነበር ለቅማንቶች እየነገሩ ሃሰተኛ መርዝ በመርጨት ኣርሶ ኣደሩን እያታለሉ እደሚገኙ በቦታው ደርሰው መርዘኛ ፕሮፓጋንዳው የሰሙ ተናግረዋል።እማኞቹ እንዳሉት ተመሳሳይ ስራዎችንም በጎንደር ዙሪያ ባሉ የቅማንት ማህበረሰብ በብዛት ባሉባቸው ቀበሌወች እንዲሁም በቆላማ ስፍራወች ጭምር አርሶ አደሩን ታርጌት አድርገው ቅስቀሳቸውን አጧጡፈውታል። የሕዝቦች ኣንድነት የሚያስበረግገው ወያኔ የሚረጨውን ክፉና ከፋፋይ ኣደገኛ መርዝ ለማክሸፍ እያንዳንዱ የኣከባቢው ተወላጅ የበኩሉን ሚና መጫወት ኣለበት ሲሉ እማኞቹ ተናግረዋል። (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ተአምር ወይስ ቅዠት ? ኢትዮጵያ የድህነትና የረሃብ ማምረቻ


ተአምር ወይስ ቅዠት ? ኢትዮጵያ የድህነትና የረሃብ ማምረቻ
ለወራቶች የዘለቀው የሕዝብ ንቅናቄ እና ተቃውሞ ኢትዮጵያን የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ከቷታል። ኦክላንድ ኢንስትቲዩት ባወጣው ኣዲስ ሪፖርት መሰረት የኣፍሪካ አንበሳ የተባለችው ኢትዮጵያ ኣፈ ታሪክ መሆኑን ኣረጋግጧል። በኢትዮጵያ ረሃብና ድህነት ማምረት ተኣምር ወይም ቅዠት እንደሆነ ባለስልጣናቱ በልማት ስም ያወጡት እቅድ ኢትዮጵያን ለድህነት ለምግብ ዋስትና ማጣት ዜጎችን ለጥቃትና ለመገለል ኣሳልፎ የሰጠ መሆኑን በግልጽ ባለስልጣናቱን ኣጋልጧል።ምንሊክ ሳልሳዊ ዝርዝሩን ከሊንኩ ያገኙታል