Wednesday, August 3, 2016

በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ክስ የተመሰረተው ኣዲስ ኣበባ ሲሆን ጎንደር ላይ የቀረበው ክስ ከሳሽ የለውም።


በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ክስ የተመሰረተው ኣዲስ ኣበባ ሲሆን ጎንደር ላይ የቀረበው ክስ ከሳሽ የለውም። Minilik Salsawi Report
በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ክስ የተመሰረተው ኣዲስ ኣበባ ሲሆን ጎንደር ላይ የቀረበው ክስ ከሳሽ የለውም።
የጎንደር ሕዝብ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተላልፎ ቢሰጥ ወዮላቹ ሲል የኣማራ ክልል ባለስልጣናትን ኣስጠንቅቋል።
በወልቃይት የኣማራ ማንነት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ እና ማነታቸውን ለማረጋገጥ ትግል ከሚያደርጉት የኮሚቴ ኣባላት ኣንዱ የሆኑት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ከትግራይ ክልል ጨለማን ተገን ኣድርገው ለኣፈና የመጡ የሕወሓት የደህንነት ሃይሎችን ተልእኮ ካከሸፈ በኋላ በሕዝብ ፍቃደኝነት በኣደራ በኣማራ ክልል መንግስት ወህኒ ቤት እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን ክስ ተመስርቶበታል ተብሎ ጎንደር ፍርድ ቤት ቤት ቢቀርብም ከሳሽ ስላሌለው ኣሁንም በኣንገረብ ወህኒ ቤት ይገኛል።
በትላንትናው እለት ከጎንደር እና ከኣዲስ ኣበባ ታፍነው በተወሰዱ ሕጋዊ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወኪሎች እና የኣማራ ማንነት ለማረጋገጥ ሲሰሩ የነበሩ ኮሚቴዎች እና ተባባሪ ኣባላት ላይ ክስ የተመሰረተ ሲሆን በኣዲስ ኣበባ ከቀረበው ክስ ላይ በኣራተኛ ተከሳሽነት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል። በዚህም መሰረት የኣዲስ ኣበባው የሕወሓት ፍርድ ቤት ኮሎኔሉ ተላልፈው እንዲሰጡት ለኣማራ ክልል ደብዳቤ ይጽፋል ተብሎ ሲጠበቅ የጎንደር ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለውም በማለት ጎንደር የተሰየሙ ዳኞች ኣራት ለኣንድ ድምጽ ሰጥተው ውጤቱ እየተጠበቀ ሲሆን የጎንደር ሕዝብ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ተላልፎ ቢሰጥ ወዮላቹ ሲል የኣማራ ክልል ባለስልጣናትን ኣስጠንቅቋል።
ከወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ ስለ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዴ በትክክል እሰከ አሁን ድረስ ያለን መረጃ የሚከተለው ነው።ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አሁንም ከዚህ በፊት እንደነበረው በህዝብ አደራ በተሰጠበት እንዳለና በየጊዜው የምንጎበኘው መሆኑን እያሳወቅን ለማዕከላዊ ተላልፎ ሊሰጥ ነው የሚሉ መላምንቶች ከእውነት የራቁ መሆናቸውን እየጠቀስን ኮሬኔል ተላልፎ እንዳይሰጥ የጎንደር ህዝብ በቂ ክትትል እያደረገ መሆኑን ታወቆ የአማራ መንግስት ከአቅሙ በላይ ቢሆን እንኳ መልሶ ለህዝብ እንደሚያስረክብ ተስማምቷል። ይህ ተጥሶ ኮሎኔሉ ተላልፎ ቢሰጥ ከፍተኛ መስዋህት ሊያስከፈል እንደሚችል ለክልሉ መስተዳደር ከወዲሁ አሳስበናል። እንኳን ኮሬኔል ሊወሰድ የተወሰዱትን ሳናስለቅቅና ወልቃይትን ሳናስመልስ እንቅልፍ የለንም። #MinilikSalsawi

Tuesday, August 2, 2016

አሁንስ በቃ ……..ትግሉ ተቃዉሞው ይቀጥላል ….. ግርማ ካሳ


Girma G. Kassa's photo.
አሁንስ በቃ ……..ትግሉ ተቃዉሞው ይቀጥላል ….. ግርማ ካሳ
Girma G. Kassa's photo.
በሕወሃቶች ጌታቸው አሰፋና ሶሞራ የኑስ በቀጥታ የሚታዘዙ የአጋዚ ወታደሮች ይህ አይነቱን ግፍና ጭካኔ እየፈጸሙ ነው። ይህ መቆም አለበት። ጣሊያን በህዝባችን ላይ ካደረሰው ስቃይ የበለጠ ስቃይ የምንቀበልበት ምንም ምክንያት የለም። ይህ ግፈኛ ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በቃህ ልንለው ይገባል።
ይህ ስርዓት ህዝብን የናቀ፣ ዜጎችን በዘር የከፋፋለ ዘረኛ የሆነ፣ በጭካኔ የተሞላ፣ የዜጎችን ደም እንደ ዊስኪ የሚጠጣ የተረገመ ስርዓት ነው። ይህ ስርዓት እንዳንግባባም እንዳንስማማ፣ ትግሬ አማራ፣ ኦሮሞ እያልን እንድንከፋፈል ያደረገ ነው። ጥቂቶችን ቱጃር ሚሊየነሮች አደርጎ ሌሎቻችንን ያደኸየ ነው። ከመሬታች፣ ከቃያችን በጫካኔ ያፈናቀለ ነው።
እንግዲህ ይህን አይነት ሰይጣናዊና ጨካኝ ተግባራትን የሚፈጽምን እንዴት ልንታገስ እንችላለን ? በጎንደር የተጀመረው ይቀጥላል። በኦሮሚያ፣ በባህር ዳር ፣ በደብረ ታቦር ሰልፎች ይደረጋሉ።፡የሕዝብ ሃይል ያሸንፋል።

የዐማራን ተጋድሎ ከእንግዲህ ማንም ሊጠልፈው አይችልም!



(ዐማራ የሚለውን ቃል የማይጠቀሙ በውስጣቸው የታመቀ ጥላቻ ያለባቸው ወይም የሚፈሩ ናቸው)
ስጋ በወደቀበት ቦታ ሁሉ ብዙ አሞራዎች ለመንጠቅ ይሮጣሉ፡፡ የዐማራውን ተጋድሎ ለመጥለፍ የሚሞክሩ ብዙ ግለሰቦች (ቡድኖች) ይኖራሉ፡፡ ይህን ማንም ያውቃል፡፡ ግን ከዚህ በኋላ አይደገምም፡፡ ማንኛውም አሁን ያለውን የአገራችን ሁኔታ የሚገነዘብ ዐማራ ትግሉን አያስጠልፍም፡፡
አንዳንዶች ከሌሎች የአገራችን ሕዝቦች ጋር ሊያጋጩን ይፈልጉ ይሆናል፤ እኛ ግን ከወያኔና ግበረ አበሮቹ ውጭ ጠላት የለንም፡፡ በራሳችን ቤት ስለራሳችን ብቻ እንመክራለን፡፡ ሌሎችም ስለራሳቸው እየመከሩ ነው፡፡ ያኔ እንደጋገፋለን፡፡ አሁን ግን የራሳችን በደል ከፍ አድርገን እንዲሰማ እንተጋለን፤ ለውጥ እስኪመጣ እንጋደላለን፡፡
ሁሉም ሰው እንዲገነዘበው የሚያስፈልገው ጉዳይ አለ፤ ይህን የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ እየመራው ያለው ራሱ ሕዝቡ ነው፡፡ ማንም የለበትም፡፡ የሕወሓትና ግበረ አበሮቹ ጭፍጨፋና ግድያ ከሕዝባችን ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስኪወገድ ድረስ የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎውን ይቀጥላል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ድምጽ ከኬፕ ቨርዲ እስከ ኬፕ ጋርዳፊ ከባብኤል መንደብ እስከ ስትሬት ኦፍ ጂብላርታር አፍሪካን ያነቃንቃል፡፡
በዚሁ ሁሉ የዐማራ ተጋድሎ ትግሉን የሚደግፉ አካላት አይነቀፉም፡፡ ግን ትግሉን ወደ ሌላ አቅጣጫ ወይም ደግሞ ‹‹አዛኝ ቅቤ አንጓች›› መሠል ሰዎችንና ቡድኖችን እኩል ከወያኔ እንዋጋቸዋለን፡፡ ምክንያቱም የዐማራ ተጋድሎ ባሕሪው ነውና፡፡ ዐማራ ይችላል፤ ትግስተኛ ነው፡፡ ዝም ይላል፤ እስኪማሩ ይጠብቃል፡፡ ግን ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው ያለው ማን መሰላችሁ? ዐማራ እኮ ነው!!
በዚህ ጽሑፍ ከዚያና ከዚህ አሁንም ሰማያዊ ፓርቲን ለመሳደብ የተዘጋጀ የሚመስላቸው ሰዎች ይኖራሉ፡፡ አያውቅንማ!! ሰማያዊ ፓርቲዎች የዐማራውን ሕዝብ ተጋድሎ አያኮላሹም፤ ያግዛሉ የሚል ጸኑ እምነት አለን፡፡ ምክንያቱም ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ያሉ ወጣቶችን በሚገባ አውቃቸዋለሁና፤ ሰማያዊዎቹ የዐማራ ሕዝብ ጠላት አይደሉምና፡፡
የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ የባለቤነት መብት ለመውሰድ ሽሚያ አይገባም፡፡ የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ ግብ በላያችን ላይ የተጫነውን መርገም፣ የመኖር ሕልውናችን የነጠቀንን ሥርዓት ማሽቀንጠር ነው፡፡ ይህንም የዐማራ ሕዝብ ያደርገዋል፡፡ ባለቤቱም ራሱ ሕዝቡ ነው፡፡
የዐማራ ሕዝብ ለምን በበላይ ዘለቀ ይምላል? እስኪ ጎጃም ሒዱ፡፡ ስንት አባት ልጁን ‹‹በላይ›› ብሎ እንደሚጠራ ታውቃላችሁ? በላይ የወንዶች ቁና!! አዎ ጎጃም ጣሊያንን ያረበደበደ፤ የወንዶች ቁና የሆነውን በላይ ዘለቀን ያበቀለ አገር ነው፡፡ ሸበል በርንታ ጫካው ይጣራል፡፡ የጮቄ ተራራ፤ የአዳማ ነፋስ፣ የጎንጅ ሰዋሰው፤ የዲማ ቅኔ የሚዘረፈው ስለነጻነት ነው እኮ!! አገው ምድር ጎጃም፣ የቻግኒና የመተከል ጫካዎች በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደልና ጭፍጨፋ ያወግዛሉ፤ ለነጻነትም ይጋደላሉ፡፡ ከቡሬ እስከ ሽንዲ፣ ከቆላ ደጋ ደጋ ዳሞት እስከ ደንበጫና ፈረስ ቤት፣ ከመንቆረር ደብረ ማርቆስ እስከ ሉማሜና ደጅን አዎበል፣ ሞጣና እነሴዎች፣ (ስንቱን ዘርዝረን እንዘልቀዋል) የዓባይ ወንዝ ብቻ ሳይሆን የነጻነትም መፍለቂያ ምድር ነው፡፡
ዐማራውን ትግል ለማኮላሸት ለሚሞክሩ ሁሉ
የዐማራው ሕዝብ በራሱ መሬት በመተከል ሲታረድ፣ በወለጋ ሲቃጠል፣ የራስ ቅሉ ሲቆረጥ፣ በወልቃይት ከነነፍሱ ሲቀበር፣ የራያ ዐማሮች በግዴታ ትግሬ ሲሆኑ፣ በበደኖና አርባ ጉጉ ቆዳቸው ሲገፈፍ፣ በጉራ ፈርዳ ጫካዎች ቀባሪ አጥተው ሲቀሩ ማን ድምጹን አሰማ? ማንም ነው መልሱ፡፡ ያኔ ድምጻቸውን ያላሰሙ አሁን የዐማራውን ሕዝብ ትግል ለመጥለፍ ሲጥሩ ማየት በሕዝባችን ላይ የተደገሰው ጥፋት መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ ለመገንዘብ አያዳግተንም፡፡
ስለዚህ እነዚህ አካላት በዐማራነታችን የሚደርስብንን ግድያና ዘር ማጥፋት ለመመከት የምናደርገውን ተጋድሎ ለመጥለፍ የሚያደርጉትን ሩጫ ሁሉ አብረን እኩል ከወያኔ እንታገላቸዋለን፡፡ ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንዲሉ እስካሁን ለአገር አንድነት ስንል የታገስነውን ከሞኝነት ከቆጠሩት ዋጋቸውን እንሰጣለን፡፡
(በባሕር ዳር እና በሎሎች የዐማራ አካባቢዎች የሚደረጉ ሰልፎችን ዝግጅት በየጊዜው እናቀርባለን)
ይህ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!

ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!!


ደብረ ታቦር ከተማ ቅዳሜ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል!!
የዐማራ ተጋድሎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው!!
የዐማራ ተጋድሎ ታቦር ተራራ አናት ላይ ሆኖ ደብረ ታቦርን እየጠራ ነው፤ ውዶ አሞራገደል፣ አፈረዋናት፣ እብናትና በለሳን፣ ከምከም ቃሮዳን እስከ መልዛ ድረስ ተነስ! ተራመድ እያለ ነው፡፡ አቤት ቅዳሜ የቴዎድሮስ አደባባይን ያየ ሰው?! ጋዜጠኞች ኢየሱስ ተራራ አናት ላይ ሆናችሁ ቅዳሜ ደብረ ታርቦርን ተመልከቱ!!
በአጅባር ሜዳ፣ በቴዎድሮስ አደበባይ የፋርጣ ፈረሶች ጌቶቻቸውን ይዘው ተሸልመው ደምቀው ይውላሉ፡፡ ዐማራነት ይዘከራል! የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል፡፡
ጨጪኾ አምባ ላይ ሆኖ ‹‹አምበሳው ጋይንት ኧረ ምነው ዝም አልክ?›› ሲል የዐማራ ተጋድሎ ድምጽ እስከ ተከዜ ወንዝ በርሀ፣ እስከ ጉና ተራራ አናት፣ ወገዳ፣ ሦስቻምና ሙጃ፣ አርብ ገበያ ቤተልሔም ድረስ ተሰምቷል፡፡ ክምር ድንጋይና ጋሳይማ የሐሙስ ወንዝን ገበሬ ይዘው ከመከሩ ከርመዋል፡፡ ሞክሸዎችን ማን ብሏቸው ለዚህማ!!
እስቴ ዴንሳ ተራራ ሥር ያለችው መካነየሱስ ከተማ ጥሪዋን ለእሁድ ካስተላለፈች ሰንብታለች፡፡ ሰባራ ድልድይ ድረስ ከተሰማ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ የባየ ግራር ሜዳ እንዴት እንደናፈቀኝ እኮ!!
መቄት ዋድላ ደላንታ ይቀጥላል፤ መርጦ ኢየሱስ ላይ የሚሆን ሰው የዋድላና ደላንታ፣ የየጁን ባላባቶች ድምጽ ከመቻሬ ሜዳ ይሰማል፡፡ ራያ ራዩማ፣ ወሎን በፍቅር ለሚይዘው እንጅ በማንነቱ የሚመጣውንማ መቼም ታግሶ አያውቅም! በወልድያ ሰርጥ አልፎ ቆቦ ማዶ ራያ ይደርሳል! ድምጻችን የወያኔን ዙፋን ያርበደብዳል!
ያች ምድር ያች፤ መርሳ አባ ጌትየን አልፋ ያለችው አዎ ውጫሌ ጣሊያን እንደሸወደኝ ለወያኔማ አልሸወድም እንዳለች ሰምቻለው፡፡
ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ የዐማራ ተጋድሎ እየተጣራ ነው፤ ኧረ ሞረሽ እያለ ነው!? ጦሳ ተራራ ላይ ሆኖ ኮምቦልቻ ብትል ሀይቅ፣ ተንታ ብትል አምባሰል ከየትኛውም ቦታ ሁሉ ጥሪያችን ከእኛ አገር ኔት ወርክ ቀድሞ ይነሳል፡፡
(የደብረ ታቦርንና የእስቴን ሰልፍ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን ይዤ እቀርባለሁ)
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!
ይህ ሁሉ ግን የመጨረሻው መጀመሪያ ነው!!

የነፍጠኞች ፖሊቲካ ( መስፍን ወልደ ማርያም )


አገር ሰላም's photo.
የነፍጠኞች ፖሊቲካ ( መስፍን ወልደ ማርያም )
ሐምሌ 2008
ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖሊቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖሊቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል፤ ለምሳሌ መፍጨትና መቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል፤ ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ይህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል ነፍጠኛ ፖሊቲከኛ ወይም ፖሊቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም፤የነፍጠኛ ትግል በተመንጃ ነው፤ የፖሊቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው፤ በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖሊቲከኛ ትግሉ በመላ ነው፡፡
የፖሊቲካ ሥልጣንን ነክሶ ይዞ ሕዝብን በሕዝብ በዱላ እያደባደቡ በማሸነፍም ሆነ በመሸነፍ የሥልጣንን ክብር ማግኘት በጭራሽ አይቻልም፤ በዱላ ትግል በሁለቱም ወገን ያሉ ወጣቶች ይጎዳሉ፤ በተሸናፊው በኩል የተሰለፉ ወጣቶች የመረረ ኑሮአቸውን የሚጀምሩት ወዲያው ነው፤ መቃብራቸውም ሆነ ቁስላቸው ክብር የለውም፤ የየግሉ አበሳና ለቅሶ ሆኖ ይቀራል፡፡
በድል አድራጊው በኩል የተሰለፉ ወጣቶችም ቢሆኑ ማርና ወተት የሚያገኙት በጣም ጥቂቶች ናቸው፤አብዛኛዎቹ ያለ ማጋነን ዘጠና በመቶ የሚሆኑት ጠመንጃ ተሸክመው በወገናቸው ደረት ላይ ሳንጃ ደቅነው እየወጉና እያሰቃዩ በየዕለቱ ከርሳቸውን ለመሙላት ያለፈ ኑሮ የላቸውም፤ ወይም እውነቱን ፍርጥ አድርጎ ለመግለጽ ዘጠና ከመቶ የሚሆነው ከአሸናፊው ወገን ያለ ወጣት አሥር ከመቶ ለሚሆነው አሽከር ወይም ሎሌ ሆኖ ወገኑን በስቃይ እየጠበሰ ለሆዱ የሚያድር ይሆናል ማለት ነው፡፡
አብዛኛውን አሸናፊንም ሆነ ተሸናፊውን የሚያዋርደው ወይም ክብርን የሚነሣው የአሸናፊና የተሸናፊ ትግልም ሆነ የትግሉ ውጤት ከአብዛኛው የአገሩ ሕዝብ ፈቃድ ውጭ የተደረገ የጉልበተኞች ግብግብ ነው፤ እንዲህ ያለ ግብግብ የሚደረገው ከሕዝቡ ጋር ሳይሆን በሕዝቡ ላይ ነው፤ሁለቱም ተደባደቢ ወገኖች የሕዝብ ወገን መስለው ለመታየት ይሞክራሉ፤ ሆኖም ተፎካካሪዎቹ እርስበርሳቸው የሚታገሉት በዱላ እንደሆነ ሁሉ ከሕዝብም ጋር ያላቸው ግንኙነት በዱላ ነው፤ የሁለቱም መሠረታዊ እምነትም ሆነ ዓላማ፣ መሣሪያም ሆነ ዘዴ ዱላ ብቻ ነው፤ እንዲያውም አንዳንዴ ዱለኛነታቸው ድንበር እየጣሰ የሌሎች አገሮችን ሉዓላዊነት ይነካል፤ በዛሬው ጊዜ በዓለም ውስጥ ዋና ዱለኛ አገር አሜሪካ ነው፤ በሱ ጥገኝነትና በሱ ጥላ ስር ያሉ አምባ-ገነን አገዛዞች በበኩላቸው ዱለኛነትን ይለምዳሉ፡፡
የሕዝብን የገነፈለ ዓመጽ ከዱለኛነት ጋር እንዳናዛምደው ጥንቃቄ ያስፈልጋል፤ አንድ ሕዝብ በማይሰማ ደነዝ አገዛዝ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ሲቆይ ተደብቆ የነበረው ሁሉ ገሀድ ይወጣል፤ በእንግሊዝኛ አንድ የአነጋገር ፈሊጥ አለ፤ የግመሉን ወገብ የሰበረው ሰንበሌጥ ይባላል (the straw that broke the camel’s back)፤ ሰንበሌጥ በእውነት የግመልን ወገብ የመስበር አቅም ኖሮት አይደለም፤ ነገር ግን ጭነቱ ተከምሮ፣ ተከምሮ በመጨረሻ የግመሉ ወገብ ሊሸከመው የማይችለው ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ የሚጨመር ሰንበሌጥ የተከመረውን ሸክም ከመጠን በላይ ያደርገውና የግመሉን ወገብ ይሰብረዋል፡፡
አበሳና ግፍም ከዓመት ዓመት እየተከመረ፣ ኑሮ እየከረረ፣ ከሞት ይልቅ ስቃይ እየመረረ፣ የግመሉን ወገብ እንደሰበረው ሰንበሌጥ ለዘመናት በሕዝብ ላይ በተከመረ ግፍ ላይ አንድ ግፍ ጣል ማድረግ የግፍ ግንፋሎትን ይፈጥራል፤ ትእግስት ይደርቃል፤ ጨዋነት ዋጋ ያጣል፤ እንኳን ሰው ድንጋይም ይገነፍላል፤ እሳተ ገሞራ የሚባለው በመሬት ውስጥ ያለው ድንጋይ ሙቀት ሲበዛበት እየቀለጠ መሬትን ሰንጥቆ ሲገነፍል ነው፤ ሕዝብም እንዲሁ ነው፤ ግፍ ሲበዛበት፣ ዙሪያው ገደል ሲሆንበት ይገነፍላል!
መገንፈል በሞት ውስጥና በሞት መሀከል መተራመስ ነው፤ ልዩ ኢላማ የለውም፤ በመንገዱ ላይ የሚያገኘውን ሁሉ ይጠብሳል፤ ሀሳብም፣ ስሜትም የለበትም፤ንዴት ብቻ ነው፤ አደጋውም ያለው እዚያ ላይ ነው፡፡

በጎንደር ሰልፍ ላይ የተጻፈ ግሩም ጽሁፍ በግርማ ሰይፉ



የጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ በእውነት ሰላማዊ ሆኖ አልፏል፡፡ መንግሰት በዚህ ጉዳይ ጠብ በመጫር ባለመሳተፉ ሊመሰገን ይገባል፡፡ ከመንግሰት የምንጠብቀው ይህንን ነው፡፡ ነገር ግን ከሰልፉ ማብቃት በኋላ መንግሰት ጠብ ጫሪነቱን ቀጥሎበታል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ የአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ሰላማዊ ሰልፍ የሚመለከተውን አዋጅ የሚያውቁት አይመሰለኝም፡፡ አዋጁ ያረጀ ያፈጀ ቢሆንም ሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ አያሰፈልገውም-የሚያስፈልገው ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ ሰልፍ እንደሚደረግ ለመንግሰት አካል እንዲያውቀው የሚደረገበት ምክንታያት ደግሞ ለሰላማዊ ሰልፈኞችም ሆነ ባጠቃላይ ለህዝብ እና ለንብረት ጭምር ጥበቃ እንዲያደርግ ነው፡፡
የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደሚሉት በስልፉ ላይ ለተንፀባረቁት ሃሳቦች ኃላፊነት የሚወሰድ አካል ለመፍጠር አይደለም፡፡ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊም ሆነ የፖለቲካ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ደግሞ መንግሰት ሊሚልሳቸው የሚችላቸው ከሆኑ እሰየው ካልቻለ ደግሞ ለሚችል እንዲለቅ ለማስገደድ ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡
የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አስቂኝ ነገሮች ተናግረዋል፡፡ ከአስቂኞቹ አንዱ ሰልፈኞች ይዘውት የወጡት ባንዲራ ትክክል አይደለም የሚል፡፡ ህዝቡ እየተቃወመው ያለው አንዱ ነገር እኮ ባንዲራችን ላይ ያልተሰማማንበት ነገር በግድ አትጫኑብን፡፡ የተሰማማው ይለጥፍ ያልተሰማማው ያለመለጠፍ መብት አለኝ እያለ ነው፡፡ ይህ እንዳይሆን ማሰፈራሪያ ህግ እንደወጣ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ይህ በማስፈራሪያ የሚሆን ነገር እንዳልሆነ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በግድ ሲሆን ማርም ይመራል፡፡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው መስማት የሚፈልጉትን ለመሰማት እኮ ሰለማዊ ስልፍ ሳይሆን እነርሱ የሚጠሩት ስብሰባ ላይ መገኘት ነው የሚያስፈልገው፡፡
ለማነኛውም የጎንደር ሰለማዊ ሰልፍ አንድ ነገር አሰተምሮን አልፎዋል፡፡ ሰልፍ እንደሚደረግ የሚነገረው አካል በተለያየ ሰበቦች የህዝብ ድምፅ ላለመሰማት ሲያሴር፣ ህዝብ ደግሞ እንቢኝ እንደሚል አሳይቶዋል፡፡ ከዓመታት በፊት ተመሳሳይ ነገር በደሴ አካሄደናል፡፡ ሰልፍ እንደምናደርግ ፕሮግራማችንን አሳውቀን እንቢ ሲሉ ግደሉን ብለን ወጥተን በሰላም ተጠናቋል፡፡ አሁን በጎንደር ይህ ተደርግሟል፡፡ የጎንደሩ የተለየ የሚያደርገው ደግሞ ሊቃወሙ የወጡት የክልሉን መንግሰት ብቻ ሳይሆን ተገፍተዋል ያሉትን ወንድምና እህት የወልቃይትና አካባቢው ህዝብ ጥያቄ ለመደገፍ ነው፡፡ የወልቃይት እና የአካባቢው ህዝብ ጥያቄውን ለትግራይ ክልል ቢያቀርብ እንደማይደመጥ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ እኔም ከሚስማሙት ውስጥ ነኝ፡፡ ህውሃት እንዲህ ዓይነት ጥያቄ ስለማይመቸው ማለቴ ነው፡፡
በተመሳሳይ ጉዳይ ትግራይ ውስጥ የወልቃይት ህዝብ ትግሬ ነው የሚል ስልፍ ወጥቶ ተመልክተናል፡፡ ይህን ሰልፍ ለማድረግ ግን የሰለማዊ ሰልፍ ጥያቄ ለማቅረብ እና ለሚፈጠረው ነገር ሃላፊነት ለመውሰድ በሚል ጥያቄ አቅርቦ የተፈቀደለት አካል የለም፡፡
ከዚህ ጋር የተያያዙ አንድ ሁለት ነጥቦች ላንሳ፡፡ በአዲስ አበባ አንድ ማርቆስ የሚባል የሰልፍ ጉዳይ የሚመለከተው ሰው ጋር ንግግር ስናደርግ ለመሆኑ እሰኪ እሰከዛሬ ኢህአዴግ ይህን ሁሉ ስብሰባ እና ሰልፍ ሲያደረግ ጥያቄ ያደረገበትን አንድ ደብዳቤ አሳየኝ አልኩት፤ ደነገጠ ለነገሩ “ጥያቄ ያቀርባሉ ?” አልኩት፡፡ መልስ የለም – መቼም እናንተም እኔም እዚህ ውስጥ ያለው መልስ ይገባቸዋል፡፡ “አንበሳ” ተበድሮ ይከፍላል ወይ? ቢባል ማን ጠይቆት ይባላል፡፡ በዋነኝነት ሰላማዊ ሰልፍ ሲደረግ ሶሰት ሰዎች መጥተው መፈረም አለባቸው የሚሉት ለማስፈራራት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ህገ መንግሰት ድንጋጌ ውጭ ነው፡፡
ሌላ አንድ ጉዳይ ልጨምርላችሁ፡፡ ምርጫ ቦርድ የሚባል አንድ ማፈሪያ ተቋም አለ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ እንዳይኖረው ተገቶ ከገዢው ፓርቲ እና ከደህንነት ጋር የሚሰራ ተቋም ነው፡፡ ሃላፊዎቹም ቢሆኑ በሚጠበቁት ደረጃ ሳይሆን ወሬ በማቀባበል የሚኖሩ ናቸው፡፡ ተቋም መስሎን አክብረነው በምንነጋገርበት አንድ ወቅት “ለመሆኑ በኢህአዴግ፣ በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ እንዲሁም በአጋር ድርጅቶች ሰብሰባ ላይ ተወካይ ትልካላችሁ ወይ?” የሚል ጥያቄ ለሃላፊው አቀረብኩ፡፡ በፍፁም እንደማይልኩ ነገረኝ፡፡
ለነገሩ በየትኛውም ህግ መገኘት አለባቸው የሚል ባይኖርም ዘወትር በተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብሰባ ላይ ተገኝተው ሂደቱን ሲታዘቡ/ሲሰልሉ ውለው፣ የፈለጉትን ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡ ወሬውን ለሚፈልገው አካልም ወሬውን ሹክ ይሉታል፡፡ የፃፉትን ሪፖርት ግልባጭ እንኳን ለፓርቲዎች አይሰጡም፡፡ በተለይ በተደጋጋሚ ለመታዘብ የሚመጡት ሁለት የምርጫ ቦርድ ሰዎች ይህን እንጀራ ብለው ሲበሉ አፍራለሁ፡፡ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች በፓርቲዎቹ ስብሰባ ላይ ባይገኙም ግን ፓርቲው መንግሰትን ተገን አድርጎ በሚሰበሰባቸው ሚስጥራዊ ስብሰባዎች ግን ይገኛሉ፡፡ የፓርቲውን አቅጣጫ ለማስፈፀም፡፡ በተደጋጋሚ የምክርቤት አባል እያለሁ የፓርቲ ጉዳይ ስለሆነ በሚል እኔ እንድወጣ ተደርጎ የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎች ግን ተገኝተው ታዝቢያለሁ፡፡ እነዚህ ናቸው ፓርቲዎችን በአንድ ዓይን እናያለን የሚሉ ማፈሪያዎች፡፡ አንድ ነገር ግን በትክክል ይላሉ – “ሆደ ሰፊነን”፡፡

በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡ የኛ ሕዝብ ትያትር ይወዳል፡፡ የወያኔው ሚኒስትርና የኣሜሪካ ምርጫ



  • በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
  • ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
  • ምንድን ነው ያልከኝ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
  • የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
  • እህሳ፡፡
  • ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
  • አላውቅም፡፡
  • በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡

[የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ቢሮ ቁጭ ብሎ የአሜሪካንን ምርጫ በቲቪ እየተከታተለ ነው፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ደወሉለት]
  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በአስቸኳይ ቢሮ ና፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ቲቪ እየተከታተልኩ ነበር፡፡
  • ስማ በሥራ ሰዓት ዛራና ቻንድራ ታይልኛለህ?
  • ኧረ ሌላ የሥራ ጉዳይ ነው እየተከታተልኩ ያለሁት፡፡
  • ምን አሁን ኢቢሲ ላይ ምን አጓጊ ነገር ኖሮ ነው?
  • አይ የአሜሪካን ምርጫ እየተከታተልኩኝ ነው፡፡
  • እኔ ጠፋሁ!
  • ምነው?
  • ዋነኛው ኒዮሊብራሊስት አጠገቤ ተቀምጦ ኖሯላ?
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • የእነሱን ምርጫ ምን ሊያደርግልህ ነው የምትከታተለው?
  • ከእነሱ እኮ ብዙ የምንማረው ነገር አለ፡፡
  • እየቀለድክ ነው?
  • ኧረ የእውነቴን ነው፡፡
  • አሁን ማን ይሙት እነሱ ከእኛ ይማራሉ እንጂ እኛ ከእነርሱ እንማራለን?
  • እነሱ ደግሞ ከእኛ ምን ይማራሉ?
  • ለምሳሌ ምርጫ መድፈን እንደሚቻል፡፡
  • ብለው ነው?
  • እህሳ? ከእነሱ ግን ምን መማር እንችላለን?
  • ለምሳሌ ባለፈው ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ጥቁር ፕሬዚዳንት ሥልጣን ይዟል፡፡
  • እኛስ ለመጀመሪያ ጊዜ 100 በመቶ ወንበር ይዘናል አይደል?
  • ከዚያም ባለፈ አሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ፕሬዚዳንት ልትሆን ትችላለች፡፡
  • እኛም እኮ በፓርላማ ባሉን ሴቶች ብዛት ከአፍሪካ አንደኛ ነን፡፡
  • ቢሆንም አሜሪካ እኮ ሴት ፕሬዚዳንት ሊኖራት ይችላል እያልኩዎት ነው?
  • ግን ያ እንዴት ሊሆን ይችላል?
  • ምን ችግር አለው?
  • ሴት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ልትሆን?
  • ለምን አትሆንም?
  • ያው ትንሽ …
  • ክቡር ሚኒስትር ሴቶች ኢምፓወር መደረግ አለባቸው እያሉ በየቦታው ሲያወሩ አልነበር እንዴ?
  • የምታወራውን ሁሉ ታደርገዋለህ ማለት አይደለም፡፡
  • እኮ እንዴት?
  • በቃ አየህ ሲያስፈልግ ዝም ብለህ ታወራለህ፡፡
  • ለማንኛውም እኔ ያልኩዎት ይኼንን ነው፡፡
  • ምንድን ነው ያልከኝ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ቴአትር አይደለም፡፡
  • የእኛ ቴአትር ነው እያልከኝ ነው?
  • እህሳ፡፡
  • ግን ለምን ቴአትር እንደሆነ ታውቃለህ?
  • አላውቅም፡፡
  • በሕዝቡ ፍላጐት ነዋ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • በየቴአትር ቤቱና ሲኒማ ቤቱ ሕዝብ እንዴት እንደሚሰለፍ አይተሃል?
  • በደንብ አይቻለሁ፡፡
  • ስለዚህ ሕዝብ ቴአትር ይወዳል ማለት ነው፡፡
  • እ…
  • አየህ ምርጫው ላይም የነበረውን ሰልፍ ታስታውሰዋለህ?
  • አዎን፡፡
  • በቃ ስለዚህ ለዛ ነው የሕዝቡ ፍላጐት ቴአትር ነው ያልኩህ?
  • የአሜሪካ ምርጫ ግን ቴአትር አይደለም፡፡
  • ነው እንጂ፡፡
  • እንዴት ሆኖ?
  • ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደረው የቲቪ ሾው የነበረው አክተር አይደል እንዴ?
  • ዶናልድ ትራምፕን ነው?
  • ታዲያስ እሱ አክተር/ፖለቲከኛ ነው፡፡
  • እርስዎ ግን ምን እንደሆኑ ያውቃሉ?
  • ምንድን ነኝ?
  • ኮሜዲያን/አክተር!
[የክቡር ሚኒስትሩ ልጅ ስልክ ደወለላቸው]
  • ዳዲዬ!
  • ወዬ፡፡
  • ና በእናትህ፡፡
  • ምን ሆነህ ነው?
  • ምን እዚህ…
  • አፍህ እየተኮላተፈ ነው፡፡
  • አንድ ጌ…ጃ… ትራፊክ…
  • ምንድን ነው የምታወራው?
  • እዚህ…
  • ጠጥተሃል እንዴ?
  • ትንሽ… ነው… የቀማመስኩት፡፡
  • ምን?
  • አንድ… ሦስት… ብርጭቆ… ዊስኪ ናት፡፡
  • የት ነው ያለኸው?
  • የሆነ የሚያስጠላ… ቦታ ነው፡፡
  • ሰክረህ ነው?
  • በእናትህ… ዳዲ… አታካብድ፡፡
  • ጠጥተሃል ወይ?
  • ትንሽ… ነው… የቀመስኩት፡፡
  • አጠገብህ ማን አለ?
  • እንካ አናግረው፡፡
[የጣቢያው አዛዥ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር ማውራት ጀመረ]
  • ሄሎ!
  • ማን ልበል?
  • ማን ልበል ነው ያልከኝ?
  • አዎን ጌታዬ፡፡
  • በእርግጥ ጌታህ ነኝ፡፡
  • ምንድን?
  • ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
  • እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ሆኖ ነው ልጄን ያሰርከው?
  • እኔ መቼ አወቅኩ?
  • ሥራህ ምን ሆነና?
  • የትራንስፖርቱን ሥርዓት ማስከበር ነዋ፡፡
  • ከዛ በፊት ማድረግ ያለብህ ነገር አለ፡፡
  • ምንድን ነው?
  • የእኔ ቤተሰቦችን ማንነትና ምንነት ማወቅ፡፡
  • እሱ የሥራ ኃላፊነቴ ውስጥ እንዳለ አላውቅም ነበር፡፡
  • ለዚህ ደግሞ ትቀጣለህ፡፡
  • ኧረ ይቅርታ ጌታዬ፡፡
  • ምን አድርጐ ነው ልጄ?
  • ጠጥቶ ሲያሽከረክር ተይዞ ነው፡፡
  • እኮ በአስቸኳይ ይለቀቅ፡፡
  • ሕግ ጥሷል ግን፡፡
  • እኔ ጠፋሁ፡፡
  • በዛ ላይ አንደር ኤጅ ነው፡፡
  • አዋልደኸዋል አንተ?
  • እንደሱ ማለቴ አይደለም፡፡
  • እኮ በአስቸኳይ ልቀቀው፡፡
  • ቤት ማን ያደርሰዋል?
  • አንተ ምን ትሠራለህ?
  • እሺ አደርሰዋለሁ፡፡
  • ከዛ እኔና አንተ እንገናኛለን፡፡
  • ምን ለማድረግ?
  • እየጠጣን ለማውራት!
[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቤት እየሄዱ ነው]
  • ምን ሆነህ ነው አንተ?
  • ጉንፋን ይዞኛል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • የክረምቱ ቅዝቃዜ ለነገሩ ከባድ ነው፡፡
  • ቅዝቃዜው ሳይሆን ሌላ ነው፡፡
  • ስማ ይኼ ክምር ምንድን ነው?
  • የቱ ክቡር ሚኒስትር?
  • ከተማው ውስጥ የሽምቅ ውጊያ ተጀምሯል እንዴ?
  • የምን የሽምቅ ውጊያ?
  • በየቦታው የከረጢት ክምር አያለሁ፡፡
  • እንደ እርስዎ ዓይነት ቀልደኛ ሚኒስትር አይቼ አላውቅም፡፡
  • እንዴት?
  • መቼም በየቦታው የሚያዩት የከረጢት ክምር ለድርቁ የተሰጠን ዕርዳታ ነው አልልዎትም?
  • ታዲያ ቀልደኛው ማን ነው?
  • እርሱ አይደል እንዴ ጉንፋን ያስያዘኝ?
  • ቀልዱ ነው?
  • ኧረ በየቦታው ያዩት የቆሻሻ ክምር፡፡
  • ለምንድን ነው ቆሻሻው የማይነሳው?
  • ያሳመመኝ እሱ ቀልድ ነው አልኩዎት እኮ፡፡
  • የምን ቀልድ?
  • የቆሻሻ ቀልድ!
[ክቡር ሚኒስትሩ የከተማው አስተዳደር አንድ ኃላፊ ጋ ደወሉ]
  • አቤት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ልትጨርሱን ነው እንዴ?
  • በምን?
  • በጉንፋን፡፡
  • ድምፅዎት ግን ጉንፋን የያዘው ሰው አይመስልም፡፡
  • ሕዝቡ በጠቅላላ ተለክፏል አይደል እንዴ?
  • በምን ክቡር ሚኒስትር?
  • በበሽታ፡፡
  • እ…
  • ቆሻሻው ለምንድን ነው የማይደፋው?
  • አልሰሙም እንዴ?
  • ባለፈው አንድ ቢሊዮን ብር ያወጣ የቆሻሻ መጣያ ሲመረቅ ጠርታችሁኝ አልነበር እንዴ?
  • እኮ መጣል አትችሉም አሉን፡፡
  • እነማን?
  • የአካባቢው ገበሬዎች፡፡
  • ምን?
  • አዎ፣ እኛ ቆሻሻ መጣያ አይደለንም አሉ፡፡
  • እኔ ጠፋሁ፣ እና ምን አላችኋቸው?
  • ምን እንላለን?
  • ነገ ደግሞ በዚህ በኩል በመኪና ማለፍ አትችሉም ቢሉስ ምን ልትሉ ነው?
  • ምን ማለት እንችላለን ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት አትችሉም?
  • ይኼ እኮ የፌደራሊዝም መዘዝ ነው፡፡
  • እኔ ጠፋሁ እና በበሽታ እንለቅ?
  • በምን በሽታ?
  • በአተት፡፡
  • እሱ እኮ ስሙ ተቀየረ፡፡
  • ምን ተባለ?
  • መተት፡፡
  • የምን አባህ መተት ነው አንተ መተተኛ?
  • አይ እሱኛውን መተት አይደለም፡፡
  • ታዲያ መተት ምንድን ነው?
  • መደበኛ ተቅማጥና ትውከት!
[ክቡር ሚኒስትሩ ቤት ሲገቡ ከሚስታቸው ጋር ማውራት ጀመሩ]
  • ሰላም ውዴ፡፡
  • እንዴት ዋልሽ ውዴ?
  • አንተን እኮ በሌላ ማዕረግ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
  • በምን ዓይነት ማዕረግ?
  • ለምሳሌ ዶክተር ብሎ መጥራት ናፈቀኝ፡፡
  • መቼም ከዚህ በኋላ ሜዲካል ዶክተር መሆን አልችልም፡፡
  • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
  • ወይም ደግሞ ፒኤችዲ አልማር?
  • በየትኛው አቅምህ?
  • ታዲያ ምንድን ነው የምታወሪው?
  • ጥያቄዬ የአንተ ተራ መቼ ነው የሚለው ነው?
  • የምን ተራ?
  • የክቡር ዶክትሬት የምታገኝበት ጊዜ ነዋ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ነኝ እኮ፡፡
  • እስቲ ክቡር ሚኒስትር ከክብር ዶክትሬት ጋር ሲሆን ያለውን ክብር አስበው፡፡
  • እሱስ ልክ ነሽ፡፡
  • የቀበሌ ሊቀመንበር ሳይቀር እየተሰጠው እኮ ነው፡፡
  • እ…
  • 12ኛ ክፍል ሳይጨርሱ በአቋራጭ ዶክተር ሲባሉ?
  • እ…
  • የሚመስለው አምስት ለአንድ እያደራጃችሁ የምትሰጡ ነው እኮ፡፡
  • ምን?
  • ታዲያ አንተ መቼ ነው የሚደርስህ?
  • በቃ ተይው መላ አለኝ፡፡
  • ምን ልታደርግ?
  • ዩኒቨርሲቲ አቋቁማለሁ፡፡
  • ምን የሚያደርግ?
  • የክቡር ዶክትሬት አዳይ!